Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

 

የብዙሃን ንቅናቄ ያናወጠዉ የሻጋታዎች አእምሮ ጭንቀት!

ይድረስ ለደብተራው አምሳሉ /ኪዳን አረጋው,  መጋቢት 20.2014

በፈረንጆች  አቆጣጠር መጋቢት 17.2014 .. በዕንቁ  መጽሄት ቅጽ .6 ቁጥር 113  email amsalugkidan@gmail.com

   ሰለ አኖሌ የሰማእታት ሐዉልት አስመልክተህ የጻህፍከውን አንድ ተረት ተረት ጹሁፍ በማንባቤ ይህንን መልስ ልሰጥህ ተገደድኲኝ ደብተራው አምሰሉ /ኪዳን በኦሮሞ ህዝብ  ላይ የቐጠርከርውን ዘረኛ ጥላቻህን በአሉባልታና  በተረት ተረት ደርተህ የዘላበድካቸዉን  አናበብሁ።  ጽሁፉ NEO EMMIYE ናፋቂዎች ምኞች የተንጸባረቀበት  ተስፋ መቁረጥ ያወለገደውና ከእወነተኛ  ታሪክ ርቀህ ራስህን ለውርደት ያጨህበትና ተራ ደብራነትህን ያሳየህበት የተስፋ መቁረጥ ጩሃት ያቀረብክበት ከንቱ ድርሳን መሆኑን ለማንገጋገጥ ግን ጊዜ አለወሰደብኝም   ኦሮሞ መጤና 16ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ለማሳመን ብዙም አልተቸገርክም። የግራኝ መሐመድን ወረራ ከለላ አድርጎ እንዳ ገባና 15 ዓመት በኃላ የግራኝ መሃመድ ወራር ሲቀለበስ ግን አጸ ገላዲዮስ ወደ ሸዋ ሲመለሱ አገሩ በእንግዶች ተሞልቶ አገኙት ይላል ድርሳንህ

 በአንተ አገላለጽ በአጭር ጊዜ አገርን ያደረሰው መጤ ኦሮሞን እንዳሆነ ድርሳንህ ያትታል። ለመሆኑ አንድ ከውጭ  የገባ ወይም መጤ  ህዝብ እንዴት አድርጎ በአጭር ግዜ  ውስጥ ይህንን ሁሉ አገር መያዝ ቻለ የሚለውን በዉል  ግን መተንተን አልቻልክም  የታሪክ በለሙያ ለመምለስም አቅሙም ችሎታሁም አጣህ። በሰዓሊ አቀራረብም ለማሰመን ዉሉ ጠፋብህ እንዳያው በከንቱ ጥላቻ፥ ዘረኝነት፥  ምቀኝነትና የኦሮሞን አብዛሃ /Majority/ መሆኑን ላለመቀበል ባልገሩ እርሱ መሆኑኡን ለመካድ ልክ  አይንህን ጨፍነህ መዋሸትና መርጠህ የታሪክ ድርቶ ለማቅረብ ሞከርክና ተንከራተትክ  ደብተራው አምሳሉ!

 በአንተ ምኞትና ቅዠት የአሮሞን ህዝብ መጤ ብለን ስም ካጠፋን ባላአገሮቹ አማሮች ነን ለማለት የታለመ ከንቱ የስእልም የታሪክም ስሌት ሆነብህ ሁሉ ሀሳብህና ድርሰትህ ኦሮሞን ለማጥላለት አልመህ በመነሳቱ እርስ በርሱ የሚጣረዙ ሃቅን የሸሹና የበለዙ ሆኖ አገኘሁት። እርስ በርሱ የሚጣራዝ ሃሰብክህና የዘላበድከዉን በሚከተላዉ በማስቀመጥ ላሰይህ። ሚኒልክ አገርን መለሰው አንድ ለማድረግ ሲመክሩ ኢትዮጵያዊ  አይደለንም አንገብርም ያሉትን እጅ ቢቆርጡ ጡት ቢቆርጡ ህግ ይፈቅድላቸዋል ትልና  ዘላብደህ ደግሞ ይህንን የፈፀሙት አሮሞዎች ራሳችዉ እርስ በርስ  እንጅ ሚኒልክ አይደለም ትላለህ። ምነዉ በቀረብህ ጃል!  ማለት ጥላቻህን ብቻ ገልፀህ ታሪክ ማጣቀሱን በተወከዉ። ምክንያቱም ምንም የታርክ ሃቅ ያለዉ ሀረግ ወይም አረፍተ ነገር ለማግኛት አልቻልኩምና ነዉ። ዛሬ እኮ 21 ክፍለ ዘመን እንጅ በእነ  እምዬ ሚኒልክ ዘመን  19ኛው /ዘመን ዉስጥአይደለንምና ከዋሹም  ከዘመኑ ጋር የሚመጥን ቢሆን የምራል ለማለት ነዉ ደብተራዉ።

      ደብተራው አምሰሉ የእምዬ ሚኒልክ የዘመኑ ናዚ መሆንክን አስመስክረሃል።   በከንቱ ደከምክ እንጅ እምዬያችሁና  Neo ሚኒልኮች በምንም ዓይነት መንገድ ከተጠያቅነት የሚታመልጡበት አንዳችም ቀዳዳ የለም። አንተና Neo ሚኒልኮች   ሚኒልክን ጨምሮ የኦሮሞ ህዝብና የሌሎች በሃይል በአንድነት ስም የተጨፈጨፉ፥ የተዋረዱ የተፈናቀሉና ማንናታቸዉን በሃይል የተነጠቁ  ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጠላት መሆናችዉ አትዘንጉ። ጉዳዩ የወጋ ቢረሳም የተወጋ አይረሳም ነዉና።

 የኛ ደብተራ ኦሮሞዎች ለነፃነታቸዉና ለሀገራቸዉ ክብር ሲፈለሙ ከአዉሮፓዉያን  በተገኘዉ ዘመናዉ የጦር መሳሪያ በታጠቀዉ ወራር የሚኒልክ ሰራዊት በአረመኔያዊና ዘግናኝ በሆነ መንገድ አልቐል። በኃላ ቀር የጦር መሳሪያ ጠላታቸዉ  በመበርበዳቸዉ ነዉ ይህ ሁሉ ግፍ የተፈጸመባቸዉ። እነዚህ ጀግኖቹን ለመዘከርም የአኖሌዉ ጅምር እንጅ ገና በመላዉ ኦሮሚያ ግፍ የተፈፅመባቸዉ ዜጎችና ቦታ ሁሉ የመታሰቢያ ሀዉልት ይተከልላቸዋል።ኦሮሞ ጀግኖቹን ለመዘከር የጨፍጨፍዎችን ፈቃድ አይጠይቅም። ከዚያም በላይ የኦሮሞ ህዝብ እርሱን ጨፍጭፈዉ በርሱ ልጆች ሬሳና በመሬቱ ላይ ተተክለዉ የሚታዩትን የጨፍጫፊዎችን ሃዉልቶች ነቃቂሎም በምትኩም የራሱን አርባኞች ሃዉልት እንደሚተክል ለአንድ አፍታም አትጠራጠር ደብተራዉ።

    ሌላው እናንተን የሚያስጨንቀው ትልቁ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ አብዝሃ /Majority/ መሆን ነው: ይህ ሃቅ በፍፁም  አይወጥላችሁም። የኦሮሞ ህዝብ  ማጆሪቲ በመሆኑ የበታችነት  አባዜ አይጠናወተዉም። ከዚያም በላይ ኢትዮጵያ የተባለችሁን ሃገር አማክሎ የያዘና የአገሪቱም እምብርት  ከመሆኑም በላይ አንተንና መሰል ነፍጣኞችን የሚያማልል የለም መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትም ነዉ። ከነዚህ  መስፈርቶች ሲንነሳ በማንኛውም  መመዘኛ የበታችነት ጥቃት የለውም። የኦሮሞ ህዝብ  ስስታምም ዳሃም አይዳለምና። ይህም ሆኖ  በአሮጳውያን ድጋፍ በነፍጠኞች ተወሮ የሃገር በለቤትነት፥ የእኮኖም ተጠቃሚነትን ከፓለቲካ ስልጣን ውጭ ሆኖ ቆይቶአል አሁንም  ይገኛል”።ይህንንም የጣዉን መልሶ ለመጎናፀፍ ገና ከወራረዉ ጊዜ ጀምሮ በመታገል ላይ ይገኛል። ዛሬ ይህንን ምኞቱን ለማሳካት ተቀርቦአል ያንተና የመስሎችህ ተስፋ መቁረጥና መፈራገጥም ከዚህ ሃቅ ይመነጫል። የአሮሞ ህዝብ ትግል ህልመኞችን ዳፍጥጦና ቀብሮ የብዙሃንን ጥቅም በሁሉም መስኩ ማረጋገጡ ግን አይቀሬ ሆኖ በፍጥነት እየገሰገሰ መሆኑን ላረዳህ እፈልጋለሁ ደብተራው። መረረም ጣፈጠም ይህን ሃቅ መጋትህ አይቀሬ መሆኑን ተረዳ። የጊዜ ጉዳይ ይሆናል እንጅ ጋሃዱን ጉዞ አታመልጣዉምና እስካዚያዉ ብትወራጭ አይፈረድብህም። 

 ደብተራው  አምሰሉ  አንድ  ነጥብ  ላክልልህና ለዛሬው ላብቃ። እኔ  እስካሁን ከታሪክ  እንዳየሁት የናንተ ፊዉዳል ገዥዎች በራስ መቻል መሪ ሲጉአዙ አልነበሩም። በአዉሮፓዉያን ትከሻና ድጋፍ ላይ የተመሰረቱ መሆኑን ታሪካችዉ ያሳያል። እርስ በርስ ሲጠላለፉና ሲጠፋፉ በእነዚሁ ትከሻ ላይ ሆነዉ ነዉ።

 አፀ ገላዲዮስ ከግራኝ ወረራ የመደን  ጉዳይ ከአዉሮፓዉያን ድጋፍ ዉጭ የሚታሰብ አልነበረም። የሚኒልክ ወደ ኦሮሚያና ደቡብ የማቅናት ዘመቻም በአዉሮፓዉያን ዘመናዊ ወታደራዊ ጠበብቶችና አማካሪዎች ሀመናዊ የጦር መሳርያና  ትጥቅ ላይ ተመስርቶ  እንደሆነ ገሃድ ነበር። የአዉሮፓዉያን ድጋፍ ታክሎበት ባይሆን ኖሮ በኃላ ቀርና በባሕላዊ መሳሪያ የተወጋዉን የኦሮሞን ህዝብና መሬትን መቆጣጠር በልቻለም ነበር። ይህን ሃቅ ሸፍናችዉ ያዙን ልቀቁን ማለት ከከንቱ ለፋት አይዘለም።የኦሮሞ ህዝብ የራሱን ቦታ ሲያገኝ ጌቶቻችሁን ከናንተ ከእሚዬ ናዚዎች ጭምር በፍትህ ፊት እንደሚፋረዳችሁ ተገንዘብ። 

 ሌላዉ ቀርቶ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጳጳስ የሚሾመዉ እስከ ቅርብ  ግዜ ድረስ ከግብጽ አሌክሳንደሪያ እንደ ነበር ግልጽ ነበር። እስከ ሃይለስላሴ መንግስት ዘመን ያውም 1930 ዎች አከባቢ ንጉሱ ራሳቸው  ኢትዮጵያዊ ጳጳስን በመሾም የግብጾችን የበላይነት ለመቐቐም  የሞከረው። ሀይሌ ሰላሴ በጣልያን ወረራ  ወቅትም አገር ጥሎ፡ በእንግሊዘች፡ ጫማ ስር ወድቆ  ከአምሰት ዓመት በላይ በስደት፡ ማሳለፉ  የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው። ከዚያም ጣልያኖች  በህዝብ ትግልና በእንግሊዞች  ተጽእኖ  ተገደዉ ሲወጡ ነው ንጉሱ ተመልሰዉ ስልጣን የያዙቱ  ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ምኑ ላይ ነው  ይህን ያህል ጮቤ የሚያስረግጣችሁ ጃል!

የአምባገነኑ  መንግስቱም ታሪክ በሌሎች ትክሻ  ተደግፎ በአንድነት ስም ከመነገድ ዉጭ መቼ የራስ መቻል መርህና በራስ የመተማመን መንፈስ -ኖሮ አችሁ ያውቃል? ደብተራው አምሳሉ። ወያኔም ዛሬ ከዚህ የመርህ አዙሪት  ሲወጣ  አይታይም አናንት ደብተራዎችና ነፍጠኞችም፡ ዛሬ ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ የሚዳዳችሁ  ፍት ለፍት  ተጋፍጦ ከመታጋልና እሳቱን  ከመንካት ይልቅ የምዕራባውያንን፡ ቢሮ  እያንካካችሁ ከማውገዝ በስተቀር ምንም አለመጣችውም  ማምጣትም  አትችሉምና ምእራባዉያንን ሲልጣን እንድያስይዙሃችሁ ከመለመን አላለፋችሁም ጃል።  አንድ ነገር ማለት ይቻላል። ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆንችሁ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ፥  ዘራፊና ቀረርቶዎችን  በማሰማት ግን አትታሙም ደብተራዉ ።መጥኔ ይስጣችሁ ጃል።

  ዛሬ ከናንተ  ከደብተራዎች ከንቱ ዳንኪራ ነጻ በሆነው በአማራ አርሶአዳር ውስጥ ይህን፡ የዘረኝነት መርዝ ግን በቀላሱ መርጨት ቀላል አይዳለም። ምክንያቱም የጎጃምና የጎንደር አርሶ አደሮች  ያሉት 21ኛዉ  ክፍለ ዘመን ወስጥ  እንጂ እንዳ NEO-ሚንልኮች  19ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ስላልሆኑ ጊዜ ያለፈበትን የዘረኞች ቀረርቶ የሚሰማበት ጆሮ ይኖራዋል ብዬ መገመት ያስቸግራል  ስርቶ ከመኖር በስስት የሌላዉን ሀብት ይመኛል ብዬ ማመን ያስቸግራል ታዲያ ማንን እየጋለባችሁ   ሌላሁን ለማጥፋት  እንደምትፎክሩ አይገባኝም ደብተራዉ።

  እናንት ደብተራዎች እንደሆናቸሁ የግባ በለዉ  ቀረርቶ  ከማስማት በቀር በተጨባጭ  ወደ ፊልሚያ  ሜዳው ለመግባት ከቶዉንም  አታስቡም፥አስባችሁትም፥ አልማችሁትም  አታዉቁምና የነ ሞረሽ ከአውስትራሊያ፥አንተን መሰል ደብተራዎችና የነ ዶክተር ጌታቸዉ ሃይሌ    ከአሜሪካ ዋይትና ስጋት የጥላቻ ዘመቻ  ለዳሃው የአማራ ህዝብ ብሶት ሳይሆን  ለራሳችዉ የተመቻቸና የተቀማጠለ፥ የተድላ ኑሮ ነውና። ይህ የምትረጩት  የጥላቻ መርዘም እናንተውኑ ይዞ እንደምጠፋ ላንዳፍታም ጥርጥር የለኝም ደብተራዉ። የኦሮሞ ህዝብ እንደሆን ክእንግድህ ወድያ ለነፍጠኞች ትእግስት እንደማይነረው በርግጠኝነት ልታዉቅ ይገባል።

             ይህቺን ስንኝ  እስቲ በጥሞና ተመልከት

የእብሪት ስሊቻዉ  አበቃ  ፈነዳ

ደብተራው   ተንጫንጫ ከያለበት ጉሃዳ

ጉራና ፈከራው ከእንግዲህ አያዋጣም 

በኒዮ እሚዬዎች አገር አትሰምርም

ይባቀል እባካችሁ በባዶ ቀረርቶ

አንድነት አይኖርም ነፈጣኛን ደርቶ

እሚዬዎች ይብቃ የዘረኛነት  ፉከራዉ

ከንግዲህ ተረዱ መጥቶአል ባለተራዉ

ይቅርታ መጠየቅ መዘመን ነዉና

ካሻችሁ ተማሩ ከዉድቀት ጎዳና

የጭቁን ህዝብ ክንድ እጅጉን ፈርጥሞሃል

የህልም ዓለም ጉዞ ባቃ ይቀበራል

የእሚዬዎች ኑዛዜ በከተ ገለማ

ደብተራው  ተረዳ ጆሮ ካለህ ስማ።

            እንሰርሙ ገዳ

 

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved