Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

የራያና አዘቦ የማለዳ ጥሪ

  

ሞቲ ቢያን አፋልጉን- 

Degebassa Feyissa


-
ኦሮሞ ለነጻነቱ ከማን ጋር ማበር እንደሚኖርበት ታሪካዊ ትምህርት የተቀሰመበት ወቀት ( 1928-1930)
በዛሬው የሳምንታዊ የሞቲ ገዳን አፋልጉን ጽኁፍ፤ በተሌያዩ ጊዝያት የተደረጉ የኦሮሞ ህዝቦች አመጽን በተመለከተ በኦሮምያን በፈረቃ ላይ ከተጻፋው ውስጥ ‹‹ የህዝቦች አመጽ ቀልድ አይደለም›› ከሚለው አርእስት ስር አለፍ አለፍ በማለት ራያና አዘቦን የማለዳ ጥሪ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡
ሞቲ ብያ ይህን የህዝቦች አመጽ ሲዳስስ ሰፊ ትናቶችን ያደረገበትና በአራት አበይት ክፍሎች ማለትም፡
1.
የራያና አዘቦ የማለዳ ጥሪ
2.
በምእራብ ኦሮምያ የመንግስት ምስረታ ንቅናቄ
3.
ከዳግማዊ አዘቦና ራያ ወደ ቀዳማዊ ወያኔ እና
4.
ባሌ ለነጻነት የሚፋለሙ የአንበሶች ሃገር የሚገኙበት ሲሆን የዛሬው ጽኁፍ በቁጥር 1 ከተጠቀሰው ብቻ የተወሰደ ነው፡፡
የሞሉትን ወንዞች በመሻገር ጫካዎችንና ቁጥቋጦዎችን በማቋረጥ በመጓዝ ላይ ያሉት ልጆቼ ናቸውደቡብ አፍሪካዊው ባለቅኔ በሀገሩ ለነፃነት የተሰማሩ ታጋዮችን ‹‹ልጆቼ›› በማለት ጠርቷቸዋል፡፡ አዎን ወጣቶች/ቄሮዎች/ በጉዞ ላይ ነበሩ፡፡ ወደ ነፃነት እየተጓዙ ነበር፡፡ ውጣ ውረድና ፈተና በበዛበት መንገድ እየተጓዙ ነበሩ፡፡ የነጻነት መንገድ ባህሪው ይህ ነው፡፡ እርግጥ ነው ነጻነት በነጻ አይገኝም፡፡ ከተገኘም በዋዛ አይጠበቅም፡፡ የህይወት ዋጋ የሚጠይቅ ነው፡፡ በህይወት ቤዛነት የሚገኝና የሚጠበቅ የሰው ልጅ አቻ የለሽ ሃብትም ነው፡፡
አዎን፤ ጭቆናዎቸ ትግልን ይወልዳሉ፡፡ ትግሎች መስዋእትነትን ያስከፍላሉ፡፡ ለነጻነጽት የሚከፈለው መስዋእትነት ወደ ነጻነት ይወስዳል፡፡ ይህ አጠቃላይ እውነት ነው፡፡ በጊዜና በዘመን የማይወሰን እውነት ነው፡፡
በኢትዮጵያ በነፍጥ ሃይል በኢምፓር አገዛዝ ስር የተቀላቀሉ ህዝቦችም ለነጻነት ጉዞ ከጀመሩ አመታት አልፈዋል፡፡ ለነጻነት በጫካዎች በቁጥቋቶዎች፤ በበረሃዎች በረግረጋማ ቀጠናዎችበአጭሩ በሁሉም አይነት የምድርና የተፈጥሮ ሁኔታ ክልሎች መጓዝ ከጀመሩ ዘመናት አልፏቸዋል፡፡ ሆኖም ህዝቦች ‹‹ጉዞ›› ብቻ አልተወሰኑም፡፡ ጀግንነትንም ፈጽዋል፡፡ በላባቸው በደማቸውና በሕይወታቸው እጅግ ውብና አኩሪ ታሪካቸውን አስመዝግበዋል፡፡ /የእነዚህ የኦሮሞ ታጋዮች/ ታሪካቸው ግን በብዙዎች እጅ አይታወቅም፡፡ በሚያውቁትም ዘንድ አይጻፍም፤ወይም አይነገርም፡፡ የሚናገሩ ወይም የሚጽፉ ቢኖሩ እንኳ የጭራቅ መልክ እየሰጡት ነው፡፡/ይህን በተለያዩ ተግባራታቸው መረዳት የሚቻል ሲሆን በሰሞኑ የገዳ ስርአት በአለም ደረጃ የማይጨበጥ ቅርስ ሆኖ እነደዳይመዘገብ የተደረገው ጥረት የሃበሶችን ጥልቀት ለው ቅናትና እብደት ያመለክታል፡፡/ ይህ የታወቀ ነው ገዢዎች የሚገዙትን ህዝብ ታሪኮች በበጎ ስሜት አያዩም፡፡ ሌላው ቀርቶ ታሪክ እንዳላቸው አይቀበሉም፡፡ በራሳቸው ግፈኛ አገዛዝ ላይ የተካሄዱ አመፆችን እንደ ታሪክ አይመለከቱም፡፡ እንደ ውንብድና እንደ ተራ ሽፍትነት፤ ጥጋብና አመጽ ማየቱ ግን ሁለንተናዊ የጨቋኝ ገዢዎች ስራ ነው፡፡ በታሪክ ውስጥህዝብ ጠላኝ ወይም እኔ ጨቋኝ አምባገነን ነኝ›› የሚል መሪ አይገኝም፡፡/ በኦሮምያ ውስጥ በኦሮሞ ህዝብ እየተከናወነ ያለው ለገዢው መደብ ለወያኔ ባለስልጣናት፤ የሕጻናት ጨዋታ ነው፡ የጠገቡ ስርአተ አልበኞች ስነሱት ብጥብጥ ነው፤ ስለዚህ ልክ ማስገባትና መግራት ስፈልጋል፡፡ ከትምህርት ገበታቸው የተባረሩ ተማሪዎች ጉዳይ፡ የሞተው የኦሮሞ ህዝብ በጭራሽ ታሪክ አይዘክረውም፡፡ በሰይጣን የሚመሩ አጋንንቶች በፈጠሩት ረብሻ ሽበብ የሞቱ ናቸው፡፡ በጭራሽ ሂደቱና ታሪኩ ተመዝድቦ ኤቀመጥም፡፡ ቢቀመጥም መንስኤውና እውነታው ተገልብጦ መጪው ትውልድ ሊደናገር በሚችልበት መልኩ ነው፡፡/
በየትኛውም የታሪክ ዘመን በባእድ በውዴታ የተገዛ ህዝብ የለም፡፡ በሮች ባርያ መሆናቸውን እወቁና እመኑ ሲያመቻቸው ነጻ ለመሆን ጦር አንስተዋል፡፡ ‹‹ባርያ መባላቸው የነጻነትን ስሜት አልገደለባቸውም፡፡ ባርነት በፀጋ አልተቀበሉም፡፡/ እኛም ኦሮሞዎች አተገኘው አጋጣሚና ጊዜ ወድ የኦሮሞ ልጆች ራሳቸውን ከኢትጶፕያ ኢምፔርያል ስርአት ነጻ ለመውጣት በተለያዩ ጊዚያት መስዋእትነትን ከፍለዋል፡፡ ከነዚህ ትግሎች ውስጥ የዛሬው የራያና ኦሮሞ ተቃውሞ ነው፡፡/
ራያና አዘቦ ከወሎ ኦሮሞዎች ጋር ኩታ ገጠም ነው፡፡ ኦሮሞ ነው፡፡/ወሎ ሲባል የታወሰኝ ሰሞኑን በሶሻል ሚድያ ላይ ያገኘሁት በሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን የቀረበውንና የሰማሁትን ነው፡፡ ግጥሙ 1964 አም መጻፉን ሰሰማ ለካስ እኔም ሳልገነዘበውና ሳላውቀው የኦሮሞነት እርሾ በነጸጋዬ ገብረመድህን ደህና አድርጎ ይዘጋጅ እንደ ነበር ተረዳሁ፡፡/ ራያና አዘቦ ኦሮሞ ነው፡ በስተምስራቅ ከአፋር በሰተሰሜናዊ በምእራብ ከትግራይ በስተደቡብ ከወሎ ጋር የሚዋሰን ህዝብ ነው፡፡
ይህ ህዝብ በተለያዩ ዘመናት ከትግራይና ከአማራ መሳፍንት ወራሪዎች ጋር በግንባር መስመር ላይ ሆኖ ሲፋለም ኖርዋል፡፡ በኦሮምያ ሰሜናዊ ጫፍ ታዋቂውን የየጁ ኦሮሞ ስርወ መንግስት መስርተው ከኖሩ ህዝቦች መካከል አንዱ ነው፡፡
አጼ ምኒሊክ የኢምፓየር ግዛታቸውን ለልጅ ልጃቸው ተናዘው እንዳለፋ በመሃሉ በተፈጠረ የፖለቲካ ውጣ ውረዶች ምክንያት ልጅ እያሱና በኋላም ልጃቸው ንግስት ዘውዲቱ ምንም ያህል ሳይገዙ ዘመነ ተፈሪ መግባቱ ታወቃል፡፡
ራስ ተፈሪ እያሱን በሴራ ፤ዘውዲቱን በግድያ ከተገላገሉ በኋላ 1928 . ወደ ንጉሰ ነገስትነት ተራምደዋል፡፡ በዚህ የሽግግር ወቅት ጠንከር ያሉ ተቃውሞዎች ገጥመዋቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ተቃውሞዎች አንዱ የራያና አዘቦ እነዲሁም የዋቅጅራት ኦሮሞዎች ትጥቃዊ አመጽ ዋነኛው ነበር፡፡ 1928 . የበልግ ወራት የኦሮሞ ታጣቂዎች በክልሉ ባሉት የመንግስት ተቋምና በአንዳንድ ጎረቤቶቻቸው ላይ የጥቃት እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ታጣቂዎቹ ወደ ደቡብ ምስራቅ በመንቀሳቀስም በአፋር ህዝብ ላይ ጥቃትን ሰነዘሩ፡፡ አንገዛም የሚል ጉልህ ተቃውሞ ለመንግስት ይፋ አደረጉ፡፡
የራያና አዘቦ ኦሮሞዎች ዘመናዊ የነፍጠኛ መንግስት በተጠናከረ መልኩ ራሱን በማዋቀር ላይ እያለ በዝምታ ሊታገሱት አልፈለጉም፡፡ የራያና አዘቦ ኦሮሞ ህዝብ ስጋቶች የመጀመሪያው መንግስት ጥንታዊ ባህላቸውን፤ ማህበራዊ ስርአታቸውንና የፖለቲካ አስተዳደራቸውን ለማፍረስ ይከተል የነበረው በስልት የተቀነባበሩ ግፊቶች ነበሩ፡፡ የራያና አዘቦ ኦሮሞዎች ሀገር በለምነቱና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚነቱ ጭምር የሚፈለግ ነበር፡፡ 
እነዚህ አጠቃላይ ሁኔታዎች ቢሆኑም የጻረ መንግስት አመፆች እንደሚገመቱት ሁሉ የወቅቱ ግጭት መነሻ የግብር ክፍን ጉዳይ የሚመለከት ነበር፡፡ 1928 የራያና አዘቦ ኦሮሞዎች የሃይለስላሴን ንግስና በመቃወም መንግስቱን ለማዳከም በክልሉ ገዢ ለነበሩት ለትግሬው ተወላጅ ለራስ ጉግሳ አርአያ ግብር ሳይከፍሉ ይቀራሉ፡፡ በዚህ እርምጃቸው ሳቢያ ጥቃት እነዳይደርስባቸው ሳይቀደሙ ለመቅደም በአካባቢው ወደ ሰሜንና ደቡብ መገናኛ ምነገዶችንና ቁልፍ አካባቢዎችን ይቆጣጠራሉ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በራስ ጉግሳ አርአያ በኩል ኦሮሞዎቹን እነደወጉ የተጠየቁት የትግሬና የአማራ ወታደሮች ክተቱ ሲታወጅ ፈቃደኛ አልሆኑም፡ የኦሮሞን ጀግንነትና የውግያ ብቃት በየአጋጣሚው ስላዩና ስለሚያውቁ ሊገጥሙአቸው አልደፈሩም፡፡
ይሄኔ ነው አጼ ሃይለ ስላሴ ለበጌምድር ገዢ ለዋግሹም ከበደና ለደጃዝማች አያሌው ጥብቅ ትእዛዝ የሰጡት፡፡ ሁለቱም ወታደሮቻቸውን አቀናጅተው ሳይውሉ ሳያድሩ ችግሩ ወደአለበት ቦታ እነዲያቀኑ ይነገራቸዋል፡፡ /በዚህ አጋጣሚ/ ራስ ጉግሳ ወሌ አመጹን በመግታት ስም ወደ ክልሉ ይመጣና ከአማጽን ገበሬዎች ጋር እጅና ጓንት በመሆን በፊንፊኔው መንግስት ላይ ጀርባውን የዞረው፡፡ በኦሮሞነቱ ከኦሮሞ ወገኑ ጋር ይቆማል፡፡ /ለዚህ ነው የዛሬው ከጠላት ከወያኔ ሰራዊት ጋር የተሰለፈና በኦሮሞ ወንድሞቹ ላይ ግፍና በደል ሲደርስ እያየ የሚያልፍ የኦሮሞ ወታደርን አሳፋሪ የምንለው፡፡ የኦሮሞ ጀግና አጋጠሚዎችን ተጠቅሞ ጥቃትን ከወገኖቹ ይከላከላል፡፡/
የኦሮሞ አመጽ የራስ ጉግሳ ወሌን አመራር ሲያገኝ እጅግ ጠነከረ፡፡ ራስ ጉግሳ የፖለቲካና የትብበር ስራዎችን በተለያ ደረጃዎች በማድረግ የማእከላዊ ምነግስትን ላመቋቋም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በዚህ መካከል ሁለቱም ማለትም መንግስትና ኦሮሞ ተፋላሚዎች በተሟሟቀ ዝግጅት ላይ ነበሩ፡፡ መንግሰት ለተጠናከረ ጥቃት የራሱን ሃይሎች እያከማቸ ነበር፡፡ የኦሮሞ ተዋጊዎችም በራስ ጉግሳ ወሌ መሪነት የሰሜኖቹን ሃይሎች በማስተባበር ለወታደራዊ እርምጃ ቁልፍ የሆኑ ስፍራዎችን በመቆጣጠርና የትጥቅ አቋማቸውን በማደራጀት ለውጊያ እየተደራጁ ጥቅምት 1929 አይቀሬው ውግያ ተጀመረ፡፡ ኦሮሞዎች በሚያስደንቅ ጀግንነት ተዋጉ፡፡ ለሁለተኛው ዙር ባርያ ሊያደርጋቸው ከመጣባቸው ግዙፍ ዘመናዊ ሰራዊት መካከል በመጀመሪያው ውግያ ብቻ ብዛት ላቸውን ደምስሰው 2000 የሚሆን ምርኮ አደረጉ፡፡ 12ሺኅ የሚሆኑ የተለያዩ ማሳሪዎችን ማረኩ፡፡
ይህን ድል ያገኙት ከጎናቸው የሚቆም መስሎ ከካዳቸው ከትግሬው ራስ ጉግሳ አርአያ ሰራዊት ጋር ገጥመው በርካታዎችን ከደመሰሱና ከእነሱም መካከል 1000 የሚሆኑ ወገኖች ከወደቁ በኋላ ነበር፡፡/ ታሪክ ራስዋን ደግማ እኛ ኦሮሞዎች ከታሪክ መማር ተሰኖን ዳግም 1991 ትገሮዎችን አምነን ሰራዊታችንን ካምፕ አስገብተን አስከብበን ለእልቂት አጋልጸናል፤ ከሃበሻና ከእባብ አብረው ቢመጡብህ የቱን ቀድመህ ትገላለህ ቢሉት ሀበሻን አለ ሱዳናዊው፡፡ ትግሬዎችን ከዳተኝነት የአማራዎችን ማሽንክነት ላልተረዳው ኦሮሞ ለዘለአለም የሚሆነውን ትምህርት የተሰጠው ራስ ጉግሳ ወሌ ላይ በደረሰው ክህዳት ነበር/ 
በራስ ጉግሳ አርአያ ጋር ተዋግተው በተጉዱ በሳምንቱ ከአጼ ሃይለ ስላሴ ጦር ዘምቶባቸው ድል አደረጉት፡፡ ነገር ግን አጼ ሃይለ ስላሴ ራስ ሙሉጌታን ጦር እነደሁም ከደቡብ የተለያዩና በሰለጠነ ጠብመንጃ የታጠቁ ጦር በአውሮፐላን ጭምር ስለላን በማደረረግ ራስ ጉግሳ ወሌ ጦር ላይ የስነልቦና ጨናን ለመፍጠር ሞከረ፡፡ ለራስ ጉግሳ ወሌ አብሮ የመንግስትን ጦር ለመውጋት ወስኖ የነበረው የሰሜን ራሶች ጦር አማራው ራስ ሃይሉም ጦር በስተመጨረሻው በውግያው ሣይገኝ ቀረ፡፡
የራስ ጉግሳ የኦሮሞ አርሶአደሮች ጦር ከዘመናቸውና ከአካቢያቸው በላቀ የተገራጁ ነበሩ፡፡ ከአማራ አምፓየር የጦር ጠቅላይ አዛዥ ከራስ ሙሉጌታና ከሌሎች ወታደራዊ ትጥቅ እስከ አፍንጫቸው ከታጠቁ በዘመናዊ ወታደራዊ ሙያ ከሰለጠኑ ሃይሎች ጋር በጠራ ሜዳ ገጥሟል፡፡ መንግስት ባለው ግዙፍ የሰውና የመሳሪያ ሃይል ተጠቅሞ ጥቃቱን ቢቀጥልም ኦሮሞዎቹ ጀግኖች እጃቸውን አላላሉም፡፡ እነዲያውም ሃይለቸውን ይበልጥ በማጠናከር በላስታና የጁ መንገድ ላይ የሚገኘውን ደሊዲ የተባለ የንግድ ማእከል አጋይተዋል፡፡ ጉግሳ ወሌ ከኢምፓየሩ ወታደሮች ጋር ሲገጥም የጦሩ አሰላለፍ ሶስት ለአንድ ነበር፡ የመንግስት ሶስት የኦሮሞ አንደ ማለት ነው፡፡ የሃይል ሚዛኑ የተመጣጠነ ባይሆንም ጉግሳ ወሌ ለጠላት የመኝበርከክ ስሜት አላሳየም፡፡ ሕወቱን አድኖ ለነፍጠኛ አገዛዝ ማደር ቢፈልግ ኖሮ ውግያው ከመጀመሩ ከሶስት ቀናት በፊት በላሊበላ ቄሶች በኩል መንግስት ያቀረበለትን የእርቅ ሃሳብ በተቀበለ ነበር፡፡
ከረጅም ሰአታት ውጊያ በኋላ ሰራዊቱ እየተሰዋበትና ጉዳት እየደረሰበት ቢቀጥልም ራስ ጉግሳ እስከመጨሰሳው ሰአት በጽናት ተዋግቷል፡፡ በመጨረሻም ራስ ጉግሳ በውግያ ላይ እያለ በእሩምታ በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ወደቀ፡፡
ራስ ጉግሳ ወሌ በጦር ሜዳ እነደ ወደቁ፤ አሸናፈው የኢምፓየሩ ሰራዊት እያቅራራ እየፎከረ ደብረታቦር ከተማ ገባ፡፡ ከራስ ጉግሳ ቢሮ ሰሜን ራሶች በሃይለስላሴ ላይ ለማበር ያዘጋጁትን ሚስጥራዊ ሰነዶችና የጦር መሳሪያዎችን አገኘ፡፡ ሆኖም የሰሜን ገዢ ራሶች በተግባር ከራስ ጉግሳ ጎን ባለመሰለፋቸው ብቻውን ትተዉት በመሞቱ የሃገሮው ህዝብ እንዲህ ሲል ገጠመላቸው፡፡
አባ ደልድግ ጉግሳ
አንተ ብቻህን ነህ
ሸዌዎች ብዙናቸው
ይረዱኛል ብለህ ነው የተቀላቀልካቸው፡፡ (ደልድል የፈረስ ስማቸው ነበር፡፡)

አባባሉ ቅኔ አዘል ነበር፡፡ ሸዌዎች ብዙ ናቸው ሲባል ሸዋ በራሱ በዝቶ ሳይሆን ‹‹ትግሬም ፤ጎጃሜም፤ ጎንደሬም የተለያዩ መሰሉህ እንጂ አንድ ናቸው›› ለማለት ነበር፡፡ የኦሮሞ ጥያቄ ሲነሳ ሁሉም አንድ ይሆናሉ፤ አንድ ሁነውም ይነሱበታል፡፡ ለማለትም ነበር፡፡ ስለዚህ ለምን አምነህ ተቀላቀልካቸው የሚል ነበር፡፡ ፡፡ የራያና አዘቦ የቦታ ርቀት፤ የመገናኛ ችግር ባለማወቅና በተለያዩ ሁኔታዎች ምክንያት ሆኖ እንጂ ራስ ጉግሳ ቢቀላቀላቸው ተአምር የሚሰሩ እጅግ ብዙ ሚሊዮን ወገኖች ነበሩት፡፡ ሆኖም የዚያ ወቅት ሁኔታ ኦሮሞ ለነጻነቱ ከማን ጋር መቀላቀል እንደሚኖርበት ታሪካዊ ትምህርት የተቀሰመበት ነበር፡፡
ይህ የሆነው 83 ዓመታት በፊት ቢሆንም፤ አንድነትን/መድረክን ተቀላቅሎ ያልሆነለት / መረራና የሰሞኑ ጉምቱ የኦሮሞ ታጋይ ኦቦ ሌንጮ ላታና መጡብኝና መጨረሻውን ያሳምረው አልኩ፡፡

ሞቲ ብን አፋልጉን
ሳምንት እንገኛን

#Oromoprotest
#Oromorevolution

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved