Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         
ጠመንጃ ያልገደለውን ታሪክ ዘፈን አይገድለውም። Wari Oromoo baleesuf yaadan of badu.
Melkamu Temesgen
 

53 / የታኅሣሥ ግርግር፣ የጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ የምርመራ ቃል፤
ብርጋዲየር ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ የክብር ዘበኛ አዛዥ በታኅሣሥ 1953 .. ስለፈጸሙት መፈንቅለ መንግሥት ተለየ ሁኔታ ለወንጀል አጣሪ ኮሚቴ የሰጡት ሙሉ ቃል የሚከተለው ነበር፡፡

እኔ /ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 25 ቀን 1953 .. ለአጣሪ ኮሚቴ ቃሌን ስሰጥ ሳልገደድ በውዴታ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በንግሥት ዘውዲቱ ሆስፒታል አልጋ ቁጥር S.A: 08: ክፍል ውስጥ የተከሳሽነት ቃሌን ሐሰት ሳልጨምርበት በእውነት እሰጣለሁ፡፡ ይህ ትክክለኛ ቃሌ በሕግ ፊት ምስክር ሆኖ እንዲቀርብብኝ እንዲሁም ወደ ፍርድ ቤት ቀርቤ በምጠየቅበት ጊዜም ሆነ ለሌላ ወንጀል መርማሪ አካል ይህንኑ ቃሌን በድጋሚ እንድገልጽ በመርማሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሌ/ኬሎኔል ታምራት ይገዙ ተነግሮኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፈጽመሃል የተባልኩት ወንጀል በኰሎኔል ደበበ ኃይለ ማርያም አማካይነት ተነቦልኝ በዝርዝር ተረድቻለሁ፡፡

መፈንቅለ መንግሥት አድርጌ በኢትዮጵያ ታላቅ ለውጥ ለማምጣት የወስንኩት ወሩን ባላስታውሰውም ከአንድ ዓመት በፊት ነው፡፡ አሁን ለተፈጸመው የመንግሥት ለውጥ ሙከራ መነሻው ብዙ ቢሆንም የበለጠ ያነሳሳኝ ግን ሐምሌ 24 ቀን 1952 .. በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት በድሬደዋ አውራጃ ድሬደዋ ከተማ፣ ሐምሌ 25 ቀን 1952 .. ደግሞ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት የየረር ጎታ አውራጃ ጉብኝት ባደረጉበት ጊዜ እኔ አብሬያቸው ተጉዤ ነበር፡፡ በዚህ ጉብኝት ላይ እቴጌ መነን፣ አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን፣ ራስ መስፍን ስለሺ ደጃዝማች ክፍሌ ዕርገቱና ከፍተኛ ባለሥልጣናትና መኳንንቶች ተገኝተዋል፡፡ ጃንሆይ ከድሬደዋ ዙሪያ ገበሬዎችና የድሬደዋ አቡጀዴ ፋብሪካ ላባደሮች ጋር ውይይት አድርገው ነበር፤ ከገበሬዎቹና ከፋብሪካ አገልጋዮች ለጃንሆይ የቀረቡ ጥያቄዎችና ሮሮዎች እጅግ ከባድ ስለነበሩ ግርማዊ ጃንሆይን አስቆጥተው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የየረር ጎታ ገበሬዎችን ጃንሆይ ማናገር ስለ አልፈለጉ ከአውራጃው ገዢዎች ጋር ብቻ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ግርማዊ ጀንሆይ በመጀመሪያው ጉብኝት ባለመርካታቸው እንደገና ከነሐሴ 15 ቀን 1952 .. ጀምሮ ሐረር ከተማንና የሐረር ከተማን ዙሪያ አውራጃ ለመጎብኘት እቴጌ መነን አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰንን ራስ መስፍን ስለሺን /ጄኔራል መርዕድ መንገሻን፣ /ጄኔራል ከበደ ገብሬን ደጃዝማች ክፍሌ ዕርገቱ እና እንዲሁም ሌሎች የክብር ተከታዮቻቸውን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናትንና መኳንንቶችን አስከትለው ጉብኝት አድርገዋል፡፡ እኔም አብሪያቸው ነበርኩ፣ በተለይ ግርማዊ ጃንሆይ የሐረርጌ ዙሪያ አውራጃ ልዩ ስሙ አማሬሳ ቀበሌ በተባለ ቦታ ከሐረር ዙሪያ ተውጣጥተው የተሰበሰቡትን ገበሬዎች ባነጋገሩበት ወቅት ገበሬዎቹ ልክ እንደ ድሬደዋ ዙሪያ ገበሬዎች ከፍተኛ ሮሮ ያለው ንግግር ከማድረጋቸውም በላይ በወቅቱ በነበሩት ገዥዎች ይፈጸምባቸው የነበረውን ግፍ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

በዚሁ የተነሣ ጃንሆይ ነሐሴ 15 ቀን 1952 .. ወደ ሐረር ከተማ ተመልሰው በማግሥቱ ነሐሴ 16 ቀን 1952 .. በሐረር ከተማ ቤተ መንግሥታቸው የሹም ሽር እርምጃ ወስደዋል፡፡ በዚህም መሠረት የሐረር ከተማ እና አውራጃ ገዥ የነበረውን ሻለቃ ብርሃኑ ደስታን ከሥልጣን አባረው በምትኩም ቀኛዝማች አስፋው ኃይለ ማርያምን የሐረር ከተማና አውራጃ ገዥ አድርገው ሲሾሙ፣ የድሬደዋ አውራጃ ገዥን ከቦታው በማስነሣት በምትኩ ኰሎኔል ተሰማ እዝነህን የድሬደዋ አውራጃ ገዥ አድርገው በመሾም ለገበሬዎቹና ለፋብሪካ ላባደሮች ደግ ነገር ያሰቡ በማስመሰል ነሐሴ 17 ቀን 1952 .. ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

ግርማዊ ጃንሆይ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት በሐረርና ድሬደዋ ከተማ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከባላገር ገበሬ ተውጣጥተው ከመጡ ገበሬዎች ጋር ጃንሆይ በቀጥታ ውይይት አድርገው ነበር፡፡ እኔም አብሪያቸው ነበርኩ፡፡ በተለይም ሐምሌ 24 ቀን 1952 .. ከድሬደዋ አካባቢ የተውጣጡ ገበሬዎች ቁጥራቸው 120 ባይበልጥም ለጃንሆይ ያቀርቡ የነበረው የመረረ ብሶት እንዲሁም ነሐሴ 15 ቀን 1952 .. ከሐረር ዙሪያ በአማሬሳ ቀበሌ የነበሩትን ገበሬዎች ሮሮ በሰማሁ ጊዜ ተወደደም ተጠላ የመንግሥት ለውጥ በኢትዮጵያ እንደሚያስፈልግ ወስኜ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ቆርጬ ተነሣሁ፡፡

ገበሬዎቹ ከተናገሩት ውስጥ ለመጥቀስ እኛ በስማችን ገበሬ እንባላለን፡፡ በመሬት ባለቤቶች ደግሞ ጭሰኞች ነው ስማችን፡፡ ይኸም ሆኖ መሬት አልባ ገበሬዎች ነን፡፡ የእርሻ መሬታችን በመሬት ከበርቴዎች በመያዙ ዓመት ሙሉ አርሰን የምናገኘውን እህል የምንከፍለው ለባለ መሬት ነው፡፡ ይኸም ሆኖ መንግሥት አያውቀንም፡፡ መንግሥት የሚያውቀን በዓመት ግብር ደረሰኝ እንጂ በሌላ አያውቀንም፡፡

ግብር አንከፍልም ብንል ደግሞ መሬት ባይኖርህም አርሰህ ትበላለህ በሚል ሰበብ ከኑሮአችን እያፈናቀሉን ለቡዙ ዓመታት ያለ ፍርድ ያስሩናል፣ ከዚህም አልፎ በግፍ ግርፋት ይፈጸምብናል፣ በዚህ የተነሣ ብዙ ገበሬዎች ወደ ጅቡቲ ወደ ሱማሊያ ተሰደዋል፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ጠመንጃ ይዘው በሽፍትነት ተሰማርተዋል፡፡ በገዛ ምድራችን ባርነት፣ በሽታ፣ ድንቁርና፣ ድህነት፣ ብዝበዛና ጭቆና ተሸክመን በመከራ ዓለም እንኖራለን ብሎ አንዱ ገበሬ ሲናገር የተቀሩት ገበሬዎች ሁሉም እምባ በእምባ ሆኑ፡፡

ሌላኛው ገበሬም ተመሳሳይ ሮሮ አሰማ፡፡ አሁን ያለነው በባርነት ዓለም ነው? ወይስ ነፃነት አለን? ነፃነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እርስዎ በንጉሥነትዎ ያውቃሉ ወይ? እኛ የሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ገበሬዎች የሚፈጸምብን ግፍና በደል ከልክ ያለፈ ነው፡፡ መሬት አልባ ሁኜ የዓመት ግብር አልገብርም ብሎ የተናገረ ገበሬ ታድኖ በፖሊሶች ተይዞ ለብዙ ዓመታት ወንበዴ ተብሎ ይታሰራል፡፡ በዚህ ምክንያት የስንት ገበሬዎች ቤተሰብ እንደ ተበታተኑ ቤት ይቁጠረው በሚልበት ጊዜ ስብሰባው ወደ ሁከት ተለወጠ፣ ባለመረጋጋቱም ተበተነ፡፡ በዚሁ ዕለት የተወሰኑ ገበሬዎችም በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ፡፡

ከጃንሆይ ጋር 1947 .. ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ ለሥራ ጉብኘት ተዘዋውሬአለሁ የጎጃም ገበሬዎች፣ የሲዳሞና ባሌ ገበሬዎች እንደራሴዎች (በጠቅላይ ገዥዎች) በመሬት ባለቤቶች (ባለርስቶች) የሚደርስባቸውን ግፍ በተለያዩ አሳዛኝ ቃላት ለጃንሆይ ዕንባ ጭምር አቤቱታ ቢያቀርቡም ጃንሆይ የሰጡት መፍትሔ የለም፡፡

ከገበሬውም በተጨማሪ የከተማዋ ነዋሪዎች አብዛኛዎቹ ቤት አልባ ከመሆናቸውም በላይ የከተማ መሬት በመሬት ባለቤቶች በመያዙ ጥቂት ሰዎች አብዛኛውን ሕዝብ በማሰቃየት ላይ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ፣ የደብረ ማርቆስ፣ የደሴ፣ የሐረር፣ የጂማ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎችና ሌሎችም የአውራጃ ከተማ ነዋሪዎች ተመሳሳይ ጥያቄና አቤቱታ ለጃንሆይ አቅርበው የተሰጣቸው መልስም ሆነ መፍትሔ የለም፡፡

ለጃንሆይ ከሕዝቡ የሚቀርቡት ጥያቄዎች በጣም ብዙ ናቸው፣ ነገር ግን የሚሰጠው መፍትሔ ግን በጣም አናሳ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ያለ አግባብ አንድም ጥፋት ሳይኖረኝ የአፈር ግብር አልከፍልም ብለሃል ተብሎ አምስት ዓመት ሙሉ ታሠርኩ፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቼ ተበታትነዋል፡፡ ሚስቴ ከሌላ ሰው ወልዳለች፣ የወረዳችን ገዥ በኩራትና በትዕቢት ተወጥሮ ከሰው ልጅ ቀርቶ ከአውሬ እኩል ይመለከተናል፣ ያለ አግባብ አሥሮ ያስገርፈናል፡፡ ወረዳውንም ለቀን እንድንሰደድ ከዚህ አካባቢ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥፉ ተብለን ዜግነት አልባ ሆነን እየተንከራተትን ነው፣ ፍትሕ የለም፣ ርኅራኄ የጎደለው ግፍ ይፈጸምብናል የሚሉና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ከተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች ለጃንሆይ ቀርበው ምንም ዓይነት መልስ ሳይሰጣቸው ታልፈዋል፡፡

ሌላው ቀርቶ ለክብር ዘበኛ እና ለጦር ሠራዊት፣ ለፖሊስ ሠራዊት ከመንግሥት የሚከፈለው ደመወዝ በጣም ዝቀተኛ በመሆኑ ወታደሩም በተለያዩ ጊዜያት የደመወዝ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ይህን ጉዳይ ለግርማዊነታቸው አቅርበን የተሰጠው መልስ ይህ ጥያቄ የቀረበው ከተራ ወታደሩ ሳይሆን በሐረር ጦር አካዴሚና በሆለታ ገነት በሚሰለጥኑ መኰንኖች በመሆኑ አርፋችሁ ቁጭ በሉ ተብለናል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሮሮዎችና አሳፋሪ ጭቆናዎች መወገድ የሚችሉት አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የዘውድ አገዛዝ ተወግዶ በሕዝብና በምሁራን አመኔታ ያለውን መንግሥት በኢትዮጵያ ለመመሥረት የዛሬ ሦስት ሳምንት የተፈጸመውን መፈንቅለ መንግሥት አድርጌያለሁ፡፡

-ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ ‹‹ገድለ መፈንቅለ መንግሥት በኢትዮጵያ 1953 ..››

(2004)

 

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved