Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

 "Junedin Sadoo Yakka Hanga kana ga'uu uumata Oromoo irrati raawwatee Oromoo Petation malateese akka seerati dhiyatuu utuu goochuu qabuu, Oromoo Gosa fi Ganduman of jala dheekisee, siyyasa fara Oromoo ittin gegesun yakka. Warii Junedin Sado waliin dhabatan ilee Junedin Sadoo waliin yakkamtoota. " Gullaalaa.

ርዕስ ጁኔዲን ሳዶ ማን ነው ?

አቶ ጁኔዲን ሳዶንና OPDO ውስጥ የተሰገሰጉትን ከሃዲ ባንዳዎች የሚመለከት !! አቶ ጁኔዲን ሳዶ እና ማህበርተኛ የሆናችሁ የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳዎች ላለፉት 25 ዓመታት መላውን የሀገሬን ህዝብ ያለ አንዳች ርህራሄ ጭካኔ በተሞላበት በታተናችሁ ምድራችንን ርስታችንን የአባት የአያት ቅድመ አያቶቻችንን አድባራት በሙሉ ለሰሜኖቹ የድንጋይ ውስጥ ፍልፈል ወሮበላ የቀበሮ መንጋ ሽፍቶች ሸጣችሁ እኛንም ለባዕድ ወረሪ አሳልፋችሁ ሰጣችሁን

 ለከርሳችሁ ለሆዳችሁ ለምቾታችሁ ለአለፊ ጠፊ ጊዜያዊ የሥልጣን ፊላጎት ( የህወሀት አሽከርና ገረድ ) ለመሆን ስትሉ ክብራችሁን ጥላችሁ ተዋርዳችሁ እኛንም አዋረዳችሁን ምስኪኑን ህዝባችንን ፈጅታችሁ አስፈጃችሁ በናንተ የሥልጣን ዘመን ሀገራችንም ከቀድሞው ዘመን በባሰ ሁኔታ የዓለም መሳቂያ ሆነች የህገሬ ህዝብ ከአምላኩ በሆነለት ዕጣ ፋንታ በተፈጠረበት ሀገሩ ላይ በዜግነቱ መብቱ ተከብሮለት ሰርቶ የመኖር ነጻነት ተነፍጎት እትብቱ ከተቀበረበት መንደሩና አፈሩ በጭንቅ በመከራ በእንባ በግድ እየተባረረ የለውዴታው በዓለም ዙሪያ ለሚያዋርድ ስደትና ለባዕድ ጥቃት ተጋልጦ ተበታተነ

 የኦሮሞ ህዝብ ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት ቀደም ሲል ከነበረበት የአጼዎችና የሶሻሊስቱ ደርግ መንግስታት ጭቆና አንጻር ለጊዜው የእናንተ አለቆችና ጌቶች ትንሽ የሚሻሉ መስሎን ነበር ነገር ግን ውላችሁ ሲታድሩ የህዝብና የሀገር ጠላትነታችሁ የዘራፊና ከሃዲነታችሁ ብሎም የወሮበላነት ማንነታችሁ በህደት በይፋ ተገላለጠ ከናንተ በፊት የነበሩቱ እነዚያ ሌሎች ጨቋኝ ነገስታትና ሥርዓታቸው የሁሉም ከወያኔ መንጋ ቅኝ ገዢዎች መቶ በመቶ በእጅጉ ይሻሉ ነበር

ዳሩ ግን ምን ያደርጋል ? የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ ! እሳት የገባ ቅቤ አይመለስ ! ወደ ኋላ አይኖር ! ሁለተኛ መወለድ የለ ! ህይወት አንድ ዕድልም እንዲሁ አንዴ ብቻ ሆነና 100 ሚሊዮን ሚስኪንና የዋህ የሀገሬ ዜጎች በገራገርነቱ ሳያውቅ ተታሎ በናንተ በተኩላዎች እጅ ወድቆ ይኋውና በከባድ ጸጸት ቁጭት ሀዘንና ከሞት እጅግ የመርግ ያህል በሚከብድ መከራና ፈተና እየተጋፈጡ በባዕድ የጭቆና ቀንበር ስር ውለው ያድራሉ

 ለዚያውም ዛሬ ምሽት ነጌ ወይም በቀጣዮቹ ቀናት ነፍሱን በዘግናኝ ሁኔታ አጥፍታችሁ እንደ ልማዳችሁ አውሬ እስኪታስበሉ ድረስ ጥሮ ግሮ ያፈራውን ንብረቱን ይነጠቃል ተወልዶ ባደገበት ተከብሮ በኖረበት ቄዬና መንደሩ በግፍ የጫናችሁበትን ችግር ውርደትና ጥቃት እየተማገ ይገኛል በዚያ ብቻም አልበቃ ብሎት አሁንም እንኳን በየሰኮንድና ደቂቃው የብዙዎች ንጹሃን ዜጎች ብርቅዬ ህይወት በናንተ ጥይት እንደ ቅጠል ይረግፋል ደማቸው በየአደባባዩ እና በየጫካው ሁሉ በከንቱ ይፈሳል ቀሪውን ሰፊ የኦሮሞ ህዝብ አሸማቆ ለመግዛት እንዲመቻችሁ በማስደንገጥና በማስፈራራት ልብሳቸውን በማስወለቅ የተቆራረጠን የኦሮሞ ልጆች ሰውነት አካል በየጥሻውና ጫካ ውስጥ በመጣላችሁ የሰው በድን በአውሬ እየተበላ ነው ምነው ? ምነው ? ሰው በሰው ወገን በወገኑ ላይ እንዲህ ዓይነቱን ለማየትም ሆነ ለመስማት እጅግ ዘግናኝ የሆነውን አረመኔያዊ ድርጊት አለ አንዳች ጥልና በቂ ምክንያት ይህን የመሰለ ርህራሄ የጎደለው ወንጀልና ጭፍጨፋን ሲፈጽም በእውነት አግባብ ነውን ? እናንተስ ብትሆኑ ሰው አልነበራችሁም ነበር ማለት ነው ? ወይስ .....?

  ጁኔዲን ሳዶ ማን ነው ? ለመሆኑ በአቶ አባይ ፀሐዬ እና በአቶ ጁኔዲን መካከል ልዩነት አለ ? ካለ ልዩነቱ ምንድን ነው ?

አባይ ፀሐዬ ገና ሲጀመር የዛሬ 43 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን አፈራርሶ ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የትግራይን ሪፓብሊክ በሰሜን ለመመስረት የአማራን ብሔረሰብንና የኦርቶዶክስ እምነትን ለማጥፋት ጭምር ፀረ-ሀገርና ፀረ-ህዝብ አቋምና የጥፋት አጀንዳ ይዞ ደደቢት በረሃ የመሸገ የሽፍታ መንጋ መሪ ከሆኑት አንዱ ገንጣይና አስገንጣይ አረመኔ ግለሰብ ነው ።በዚህ ግለሰብና በጁኔዲን ሳዶ መካከል ልዩነት አለ ዎይ ? ቢባል መልሱ የለም ነው

ምክንያቱም አባይ ፀሐዬ ሀገራችንን በጠመንጃ ወሮ ሥልጣን ላይ የወጣ የህወሀት ዘረኛና ጠባብ የንጹሀንን ደም አፍሳሽና ሀገር አፍራሽ ከሆኑት ቅኝ ገዢ መሪዎች አንዱ የሆነ እባብና በትክክል ጠላትነቱ በግልጽ ተለይቶና ተረጋግጦ በአደባባይ የተገለጠ የውጪ ባዕድ ነው

ጁኔዲን ሳዶ ግን ምንም እንኳ በሥጋና በደም ለኛ ለኦሮሞዎች የሚዛመደን ከኛው መሃከል የወጣ ቢሆንም የነዚህን የአጥፊዎች ፖሊሲና ራዕይ ተቀብሎ ዓላማቸውን በስራ ለመተርጎም ሙሉ በሙሉ በመስማማቱ በህወሀቶች ተመልምሎ እኩይ እቅዳቸውን ለመተግበር ቃል ኪዳን ገብቶ መሃላ በማድረግ መላው የኦሮሞ ህዝብ ሳያውቅ ሳይስማማ ሳይሰማ ሳይወክለው ሳይመርጠው ኦሮሞንና የኦሮሞን ጥቅም መብት እንዲሁም የሀገሪቷን አንጡራ ሃብት ለውያኔ አሳልፎ እንዲሰጥ በትግሬ ገዢዎች አማካይነት በሀገራችንና በህዝባችን ላይ እንዳፈለገው እየፈነጨ የወያኔን ፊላጎትና የሥልጣን ጥቅም ጠብቆ እንዲያስጠብቅ በኛ ላይ የተመደበ ወገን አስጠቂ የውስጥ አርበኛ ባንዳ የኦሮም ብቻም ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላትና የጭቃ ውስጥ እሾህ ነው

እንዲህ ዓይነቱን ወዳጅ መሳይ የእንግዴ ልጅ የውስጥ ጠላት በግልጽ ከሚታወቁት ከዋናዎቹ የአደባባይ ጠላቶቻችን በፊት አስቀድመን ካላስወገድነው አንዳች ስንዝር ወደ ፊት ተራምደን ፋይዳ ያለውን ቁምነገር ለመስራት አዳጋች ነው ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መምታት አሾክሿኪውን አቃጣሪውን ነው አስጠቂውን ነውተብሎ የተነገረውን ተረት በደንብ ማስታወስ ያስፈልጋል

በአንድ ወቅት በወያኔ ወሮበላ መንግስት OPDO ካድሬና ህወሀት መራሹ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕረዝዳንት የነበረው አቶ ጁኔዲን ሳዶ ያለ አንዳች የህዝብ ድጋፍና ፊላጎት ( እውቅና ወይም ምርጫ ) ለወያኔ ባሳየው ታማኝነትና አጎብዳጅነቱ ለከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ ላይ ተቆናጦ በቆየባቸው የመንግስት ሃላፊነት ዓመታት

1. ነፍሰ-ገዳዩን የወያኔ ሽፍታ መንጋ በታማኝነት ያገለገለ

2. በሱ ሥር ተዋቅረው የነበሩትን OPDO ካድሬዎችን ፤ባለስልጣናትን አካላትንና የጸጥታ ሃይሎችን በመጠቀም የህወሀትን የዘር ማጥፋት ፖሊሲ እየፈጸመ ያስፈጸመ

3. የደረሰባቸውን ጭቆና ግፍና ስቃይ መቋቋም ተስኗቸው ብርቅዬ ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ሺህዎቹን ወገኖቻችንን በገዛ ሀገራቸው መኖር ተስኗቸው ለዘግናኙ ስደት እንዲዳረጉ ዋና ምክንያት የነበረ

4. ቁጥራቸውን ለጊዜው ለመግለጽ የሚያስቸግረውን ንጹሃን ዜጎች ከመደበኛ መተዳደሪያ ሥራቸው ያፈናቀለ ያስባረረ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩትን የኦሮሞ 2 ደረጃ /ቤትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እንዲሁም ምሁራንን ከትምህርት ገበታና የማስተማር ተግባራቸው ያስተጓጎለ ያስባረረ

5. ለብዙ ዜጎች መገደልና እስከ ዛሬ ድረስ የደረሱበት አድራሻ ጠፍቶ የወገኖቻችን ሁኔታ የውሃ ሽታ ሆኖ እንዲቀር ያስደረገ

6. ፍጹም ታማኝነቱን ለወያኔዎች በመግለጽ እነሱን አስደስቶ ከነሱ የሚንጠባጠበውን ፍርፋሪ ለመለቃቀም ሲል ስበዕናውን ሽጦና ራሱን አዋርዶ ሀገርንና የተፈጥሮ ሃብቷን በወራሪ ወያኔ ባለሥልጣናት እንዲዘረፍ ያመቻቸ

7. የአዲስ አበባባ ( ፊንፍኔ) ማዘጋጃ ቤት ካንቲባ በነበረው ከአቶ አሊ አብዶ እና ሌሎች የሱ ቢጤ የበታቾቹና የበላይ አለቆቹ ጋር የክርስቲና እምነት ቤቶችን አስፈርሶ አገልጋዮቹንና መላውን ምዕመናን አስደብድቦ አሳስሮ አስፈራርቶ በመበታተን በምትኩ የሌላ ሃይማኖት ( ቤተ-እምነት ) ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በጉልበት አስገንብቶ የሃይማኖትና የጎሳ የዘር ልይነትና ግጭት ሳይኖር ለዘመናት ተከባብሮና ተረዳድቶ የኖረውን ህዝብ እንዲቃቃርና እንዲተላለቅ በትውልድ መካከል የሃይማኖት የዘርና የጎሳ ጦርነት እንዲፈጠር ያመቻችና ጥረት ሲያደርግ የነበረ

8. መላውን የኦሮሞ ህዝብ ለወያኔ ባርነት ለማመቻቸት ሲል እንደ አለቆቹ ህወሀቶች በማስፈራራት በማሸማቀቅ ህዝቡን አንገት ያስደፋ መብትና ነጻነቱን ያስደፈረ ተደፍሮ ትውልድን ያስደፈረ

9. በሸዋ በሐረርጌ በቦረና በጉጂና ኢሉባቦር ዞኖች ህዝቡ ለልዩ ልዩ አስተዳደራዊ እና ማህበራዊ እንዲሁም የመብት ጉዳዮችን በሚመለከት እሱ ዘንድ አቤቱታቸውን ይዘው ለመቅረብ ሙከራ ሲደርጉ “ OLF ጠይቁበማለትኦነግ እያንቋሸሸ እና እየደነፋ በአደባባይ በህዝብ ላይ ይሳለቅና ይቀልድ የነበረ

10. የግል አሽከር ( ባሪያና ጌታ ) በሌለበት የቤት እንስሣ እንኳን በሚከበርበት 21ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ነፍሰ-ገዳዩ አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት በአደባባይ በህዝብ ፊት በጥፊ እያጮለው ሲጠፈጥፈው ፊቱን ጠራርጎ ዝምታን የመረጠ ቦቅቧቃና ሽንታም ፈሪ ራሱ ተንቆ የኦሮሞን ዘር ያስናቀ አሰዳቢ ቅሌታም ግለሰብ ነው

11. በአንድ ወቅት እሱ የክልሉ ፕሬዝዳንት በነበረበት ጊዜ በኦሮሞ ክልል በቦረና በባሌ በጂማ እና እሉባቦር ዞኖች (አካባቢዎች) የሚገኙት የሀገር ሀብት ደኖች ( ጫካዎች ) ለረጅም ጊዜያት ያለማቋረጥ በእሳት በመቃጠላቸው (በመጋየታቸው ) ምክንያት ሰሚና የሀገር አስተዳዳሪ የህዝብ ተቆርቋሪ መሪ ( ግለሰብም ሆነ ቡድን ) በመጥፋቱ ህዝቡና በልዩ ልዩ ዩንቨርሲቲዎች እንዲሁም 2 /ቤቶች ወስጥ በትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎችእሳቱን እናጥፋበሚል የእርዳታ ጥሪ በማሰማታቸው እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው በኦሮሚያና ፌዴራል ፖሊሶች ከያሉበት እንዲታደኑ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ህይወታቸውን ለማትረፍ ከፀጥታ ሃይሎች ሮጠው በማምለጥ ከተሸሸጉበት አብዮት አደባባይ በምገኘው የእስጢፋኖስ 5ኪሎ የኦርቶዶክስ ሲኖዶስ አጠገብ በሚገኘው በቅድስተማሪያም እና 6ኪሎ ባለው ስደተኛው የመድሐንዓለም ቤተክርስቲያናት ደብራት ውስጥ ተደብቀው የነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ታድነው የተገደሉ የታሰሩ አካላቸው የጎደለና በሺህዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለስደት እንዲዳረጉ ሃላፊነት የጎደለው የጭካኔ ሥራ ሚና ተጫውቷል

12. በአንድ ወቅት የኦሮሚያ ምክር ቤት መቀመጫ ከፊንፊኔ እንዲባረር የወያኔ ሽፍቶች እቅድ ሲያወጡ በጊዜው ሥልጣን ላይ ከነበሩት OPDO አሻንጉሊት አመራሮች መካከል ጁኔዲን ሳዶ አንዱና ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበር ያለ አንዳች የኦሮሞ ህዝብ ፈቃድና ውሳኔ የህወሀቶችን ወታደራዊ ትዕዛዝ ተቀብሎ በመደገፍ እና በማስፈጸም የኦሮሞ እምብርት የሆነችውን ሸገር (ፊንፍኔ ) ከተማ ሙሉ በሙሉ ለወያኔ አምባ ገነኖች በገጸበረከትነት ሰጥቶ የበታቾቹን ሸክፎ ወደ አዳማ ( ናዝሬት ) የሸሸ የታሪክ ተወቃሽ ግለሰብ ነው

13. እሱ ( ጁኔዲን )ከወያኔ ጋር ጊዜያዊ ፊቺ ፈጽሞ ከሀገር ከመውጣቱ በፊት አስነዋሪ ሥነምግባሮቹ በህዝብና በሀገር ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎቹ በተለያዩ የውጪና የሀገር ሚዲያዎች በማስረጃ ተድግፈው በስፋት ለንባብ የበቁ ለእይታና በሰው ጆሮ የተደመጡ መሆናቸው ይታወሳል በተጨማሪምየመለስ ትሩፋትበሚል በቀድሞው ሚንስትር በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጂራ ተዘጋጅቶና ታትሞ በሰፊው ለመላው ዓለም የተሰራጨውና በርካታ ቁልፍ የህወሀት OPDO ባንዳዎች ጥብቅ ሚስጢራት አዘልና የወያኔም ሆነ OPDO ነፍሰ-ገዳይና ህዝብን ዘራፊ ሙሰኞችን ቅሌት ያጋለጠውን ጉደኛ መጽሀፍ ለማስረጃነት እንዲረዳን እንደገና ፈልጎ ማንበብ ይቻላል

14. “Sii Tube “ TV ተዘጋጅቶና ተቀነባብሮ ሰሞኑን በመላው ማህበራዊ ድህረ-ገፆች በኦሮሚኛ ቋንቋ የተሰራጨው አቶ ጁኔዲን ሳዶን የሚመለከት ልዩ ሀተታና ዘገባ ለተጨማሪ ማገናዘቢያ ማስረጃነት ከየድህረ-ገፆቹ ሁሉ ማግኘት ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪ ጁኔዲን እና ቢጤዎቹ ብዙ ሺህዎችን አሳስረው እና ከሀገር አባረው ከፊሉን ደግሞ ዘመድ አዝማድ ቤተሰብና ዘሮቻቸው የተገደሉባቸው ሃዘናቸው ሳይረሳ እንባቸው ሳይደርቅ ስቃይ መከራቸው ሳይቀረፍ የመብትና 4 የነጻነት ጥያቄያቸው ሳይመለስ የዜጎች ፍትህና ነጻነት ሳይረጋገጥ ንብረት የተነጠቁና የተዘረፉት ለፍተው ጥረው ወደ አፈሩት ይዞታቸው ሳይመለሱ ከሥራ እንዲሁም ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ጥረው ግረው ተምረው ተመራምረው የሀገር ባንዳዎችን ትዕዛዛትና OPDO አባልነት እምቢ በማለታቸው በገዛ ሀገራቸው የዜግነት መብታቸው ተገፎ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው በማናቸውም የሀገራቸው ጉዳይ ላይ የመሳተፍ መብት አጥተው የበይ ተመልካች ሆነው ሰባአዊ ክብራቸው ተረግጦ ሰርተው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እየረዱ ሀገራቸውን እንዳይጠቅሙ የመስራት ዕድል ያጡ ተስፋ- ቢስ ቦዘኔ ሆነው ተረስተው የቀሩቱ አሁን ዛሬ ጁኔዲን ሳዶ እፊታቸው ቆሞ ቢታይ የህዝብ ውሳኔ ምን ይሆን ?

ይህ መሰሪና ሃላፊነት የጎደለው ለወገኖቹ ግድ-የለሽ የሆነው ባንዳ ግለሰብ (ጁኔዲን ) እና ግብረ-አበሮቹ ከዚህ ቀደም እንደ ቅጠል ያረገፉትን የወገኖቻችን ውድ ህይወት ዛሬም ድረስ የሲቃ ድምጽ ከትቢያ እየጮሀች ናት የፈሰሰው ክቡር ደማቸው አሁንም አልደረቀም ያኔ በአስረሽ ምቺው የሥልጣን ዘመኑ ጁኔዲን የመለመላቸው OPDO ካድሬዎችና የጸጥታ ሃይሎች ዛሬም ድረስ በያንዳንዷ ደቂቃና ሰኮንድ የኦሮሞን ወጣቶች አናት ጭካኔ በተሞላበት በጥይት በሳስተው እሬሳቸውን አውሬ እያስበሉ ናቸው

ይህ ብቻም ሳይሆን አቶ ጁኔዲን ሳዶ ያኔ በሥልጣን ዘመኑ ራሱ የሾማቸውና ያሾማቸው ካድሬዎችና ሰላይ ባለሥልጣናት እንዲሁም ሌሎች የጸጥታ ሃይላት የሀገር ሃብትንና የህዝብን አንጡራ ንብረት አሟጠው እየዘረፉ የምስኪኑን ገበሬና ከተሜ ቤት እያፈረሱ መሬት እየሸጡ አብዛኛውን የኦሮሞ አርሶ አደር ከርስቱ እያፈናቀሉ ይገኛሉ በሌላ በኩል እሱ አጅሬ ጁኔዲ ደግሞ ዝርፊያውንና ጭፍጭፋውን አጠናቀው ነገ-ተነገ ወዲያ ለሱም ጭምር ተጨማሪ በቂ ስንቅ ቋጥረው የሱን እግር ተከትለው ወደ ዲያስፖራው ለሚቀላቀሉት ሌሎች ተረኞች መደበቂያ የሚሆን ዋሻን ( ቦታን ) በዲያስፖራው መካካል አፈላልጎ እያመቻቸ እግረ-መንገዱን የዲያስፖራውን አንድነትና ህብረት በማደናቀፍ የኦሮሞን የነጻነት ትግል ለማኮላሸት ( ጉልበት ለማሳጣት ) በረቀቀ ስልት እየተንቀሳቀሰ ይጠብቃቸዋል

ይህ ግለሰብ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በአዲስ መልክ ከቀድሞ አለቆቹ ቢጤ ግብረ-አበሮቹና አትላንታ ከተማ በሚገኙት OPDO አባላትና አጃቢዎቹ ጋር ሰሞኑን ከመከረና ከዶለተ በኋላየኦሮሞን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁበሚል የማታለያ ስድብ በህዝብ ላይ እየተሳለቀ ማላዘን ጀምሯል

ይህ አካሄድ የማይመስል የማይዋጥ ውሸት ቅጥፈት ከመሆኑም በላይ ሰፊውን የኦሮም ህዝብ መናቅና መስደብ ነው ከዚህ ቀደም በሥልጣን ላይ ተቆናጦ በነበረበት ወቅት ያሳሰራቸውና ራሱ ያሰራቸውን ከሀገር አስባሮ ለዘግናኝ ስደት የዳረጋቸውን ከሱ በትርና ከወያኔ ጥይት በፈጣሪ አምላክ ቸርነትና ተዓምር አምልጠው በመላው ዓለም ተበትነው ያሉትን ወገኖቻችንን ተከትሎ አሳዶ እንደገና የመውጋት ያህል ነው

በርግጥ ይቅርታው እውነተኛና ከልብ ቢሆን ኖሮ ከሀገር እንደ ወጣይቅር በሉኝሳይል ከወያኔ ጋር እንዴትና በምን ምክንያት ጊዜያዊ ፊቺ እንዳደረገ ወያነን የሚጎዳ እና የኦሮሞን የመብትና ነጻነት የሚያጠናክር አንዳች ምስጢር፤ እና ምክር ሳያሳየን ( ሳይነግረን ) ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል የወያኔን ቀጣይ ዓላማ በሰፊው ለማስፈጸም በራሱ አጃቢዎች እና የቅርብ ዘመዶቹ ከለላ ስር ተወሽቆ ለምን ከረመ ?

ይህ ግለሰብ በሥልጣን ዘመኑ ለወያኔ ወሮበላ መንግስት ላበረከተው ከፍተኛ ታማኝነት ታዛዥነትና የህዝብ ጨፍጫፊነት ውለታው ያለ አንዳች ችግር በሰላማዊ መንገድ ከህወሀት ጋር ጊዜያዊ ፍቺ ከፈጸመ በኋላ እውነት እንዲመስል ስደተኛ መስሎ እያስወራ በራሱ ምርጫ ወያኔዎች ካመቻቹለት በኋላ ቀደም ሲል እሱ በሥልጣን ላይ በነበረባቸው ዓመታት በራሱ መልማይነት OPDO ውስጥ በአከባቢ ልጅነትና ጎሳ እንዲሁም ዝምድና አስቀድሞ ባመቻቸው ቡድን ውስጥ ገብቶ በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ከተማ ዓለሙን እየቀጨ ይገኛል

በዚያ ከተማ ብቻም ሳይሆን ባለው የግንኙነት መስመር በሌሎችም ግዛቶችና ልዩ ልዩ ከተሞች በሚኖሩት የኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ገብቶ በረቀቀ ስልትና ዘዴ ዲያስፖራውን በጎሳ በዘር በአካባቢ ልጅነት ብሎም ቀደም ሲል እንደ ለመደው በሃይማኖት ጭምር በመከፋፈል በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የረባ ዕድር ፋይዳ ያለ ኮሚዩኒቲ ማህበር እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች ኦሮሞ ተቀራርቦ እንዳይጠያየቅ ተግባብቶ እንዳይረዳዳ እንዳይደጋገፍ በሀገሩና በህዝቡ ላይ ወያኔ ስለሚያደርሰው ጭቆናና የጭፍጨፋ ኢሰበዓዊ ግፍ በጋራ መክሮ የጋራ አቋም ወስዶ ወያኔን 5 በህብረት እንዳይታገል ህዝቡን በማራራቅ በወያኔ ላይ የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል በረቀቀ ዘዴ ከኋላ ዞሮ ለማምከን ( ለማዳከም ) ስደተኛ መስለው በሰርጎ ገብነት ወያኔን ለማገልገል በቅጥረኝነት ወደ ዲያስፖራው ከተቀላቀሉትና ከዚህ በኋላም ተመሳሳይ ግዳጅ ከወያኔ ተቀብለው ወደ እኛ ከሚላኩት ድንበር ዘለል OPDO ማፊያ ባንዳዎች አንዱ ነው

ይህ ግለሰብ በአትላንታ ከተማ መሽጎ የወያኔን ድንበር ዘለል እኩይ ተግባሩን (mission & vision ) በስውር እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ለደህንነቱ ማስጠበቂያ ቀድሞ ራሱ መልምሎ ባደራጃቸው OPDO አባላትንና ቅርብ ዘመዶቹን body guard መልክ እየተጠቀመ ስለ ቀድሞ ውለታው ከወያኔ በተሰፈረለት ስንቅና ውሎ-አበል እየተዝናና ህዝብን አደናግሮ በጥቂት የዓላማው ተባባሪዎችና ጥቅሙ ተካፋይ ፕሮፓጋንዲስቶች አማካይነት በቀድሞ ወንጀሉ ተጠያቂ ላለመሆን በዙሪያው መልምሎና አደራጅቶ ባዋቀራቸው opdo ገመድ-አፍ ካድሬዎችን ቀጥሮ ቀን የጎደለበት ምስኪንና ችግረኛነቱን እያስወራ በልዩ የማታለያ ጥበብ ከአንዳንድ የአካባቢው የዋህ ኦሮሞ ተወላጆች ገንዘብ በድብቅ እየተሰበሰበለት የትናንት ሳያንስ በየሄደበት ደጋግሞ ኦሮሞን እየዘረፈ የሚገኝ አስመሳይ ተኩላ ነው

 በቀድሞ አባባልሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንዲሁምበማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝአለ ጅብ እንደ ተባለው ከዚህ ቀደም በጠመንጃ አፈሙዝ አስገድዶ ህዝብን እየረሸነ እያሰረ አሳቃይቶ በመዝረፍ ሀገርን እየሸጠና እየለወጠ ያለውን አምባ ገነኑን የወያኔ ጨካኝ ቅኝ ገዢ ወሮበላ መንግስት ቅጥረኛ ሆኖ ህገ-ወጥ የመብት ጥሰቶችን በትውልድ ላይ እንዳልፈጸመ ሁሉ ዛሬ ደግሞግርግር ለሌባ ያመቻልእንዲሉ የወያኔ ድንበር ዘለል ተልዕኮን በስውር እያስፈጸመ እግረ መንገዱን ሌላ ካባ ደርቦ አዲስ ግልብጥ ታጋይ መስሎ በአቋራጭ ምናልባት ወደ ሥልጣን ሊያስመስልሰው የሚያስችል የፖለቲካ ቁማር በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለመነገድ ዳግም ካራቫቱን አጠባብቆ የይቅርታ ፎቶ በመነሳት በድህረ-ገጾች ላይ ቆሻሻ ነገሮቹን መለጣጠፍ ጀምሯል

ይህንን የማጭበርበሪያ ስልት ተጠቅሞ የኦሮሞን ህዝብ አደናግሮ በዲያስፖራ መካከል ተደንቅሮ ስውር የስለላ መረቡን ዘርግቶ የወያኔን ጸረ-ህዝብ አፍራሽ ዓላማ ከመፈጸም ጎን ለጎን ላለፉት 4 ወራት ግፍ የገፈተራቸው ጭቆና ያስመረራቸው የቅኝ ገዢዎች ቀንበር የተጫናቸውና ብሶትና ኑሮ እጅጉን ያንገሸገሻቸው የወያኔና የባንዳዎቹ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ (genocide ) ድርጊት ሳይበግራቸው በደማቸውና መተኪያ በሌላት ውድ ህይወታቸው የበሰበሰውን የትግሬ አምባ-ገነን ጨካኝ አረመኔ መንግስት ከስሩ በመገልበጥ የኦሮሞን ህዝብ ከባርነት ጭቆና ለማላቀቅ ብቻቻእውን ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ሰርጎ በመግባት ትግሉን በማቆርፈድ የወያኔን ዕድሜ ለማራዘም ስልታዊ መሰናዶ መጀመሩን ያመላክታል

በመሆኑም ለዚህ የወያኔ ድንበር ዘለል ዓላማ መልክተኛ ለሆነው ለጁኔዲን ሳዶ የይቅርታን በር መክፈት ( የሱን የማታለያና የማዳናገሪያ ተራ ቀልድ መስማት ) ማለት .

1. ለሀገር ኪሳራ ለወገን ጉዳት ለዜጎች እልቂት ደንታ ማጣት ነው

2. ለኦሮሞ መብትና ነጻነት ሲሉ የፈሰሰውን የህዝባችንን ክቡር ደምና ውድ ህይወት ዋጋ አሳጥቶ ደመ-ከልብ በማድረግ በህዝብ ነፍስና ደም እየተሳለቁ ከነፍሰ-ገዳዮች ጋራ መደራደር የማለት ነው

3. የኦሮሞ ህዝብ ብቻም ሳይሆን በሀገር ቤት ሥልጣን ላይ ተጎልተው በአሁኑ ደቂቃና ሰኮንድ 100ሚሊዮኖችን የሀገራችን ዜጎችን እያሰቃዩ እየዘረፉ እየገደሉና ሀገር አፈራርሰው ሁላችንንም እያዋረዱን በዓለም ዙሪያ መሳቂያ መሳለቂያ እና አንገት ያስደፉንን የወያኔዎች ቅጥረኛ ባንዳ OPDOዎችን ዋስትናና እውቅናን የመስጠት ያህል ስለሆነ በወኪሎቻቸው አማካይነት ከህዝብ የነጠቁትን ከሀገር የዘረፉትን በወያኔ sponsorship ( አመቻችነትና አደራዳሪነት ) ተጨማሪ ቀለብ እየተሰፈረላቸው ልዩ የውሎ-አበል እየተሰነቀላቸው በአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ዲያስፖራዎች መካከል ተሰግስገው የሚያተራምሱን ባንዳዎችን ገላልጠን ጁኔዲና ቢጤዎቹም ከያሉበት ታድነው በበደሉት ሰፊው ህዝብ ፊት ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ የሁሉም ሰው የጋራ ሃላፊነትና ግዴታ ነው

ህወሀቶች የቀበሮ መንጋ ናቸው ወያኔ ካንሰር ናት ለማንም የማትበጁ ለማንም ሰው የማትራሩ ገዳይ እና ደም መጣጭ ናቸው። ሰላይና ባንዳ አሽከሮቻቸውም እንዲሁ ፈጽሞ ለሰው የማይተኙ ናቸው

አንድ ሰው ከሰውነቱ አካላት መካከል አንዱ በካንሰር በሽታ መጠቃት ቢጀምር ካንሰሩ ወደ ሌላው የሰውነቱ ክፍሎች ተሰራጭቶ እንዳይገድለው ( ከመሞቱ በፊት ) ህይወቱን ለማሰንበት ሲል ቶሎ ብሎ በበሽታው የተያዘውን (የተበከለውን ) ክፍል በህክምና ዘዴና ባለሙያ ቆርጦ በመጣል ለተቀረው ሌሎች አካላቱ በቂ ህክምና በአፋጣኝ በማድረግ የህይወቱን ዕድሜ ማራዘም የተለመደ ነው

የኦሮሞ ህዝብም እንዲሁ ከሱ ተፈጥረው በጠላት ተመርዘው መልሰው ኦሮሞን ሊያጠፉት ጠላቶቹ የሆኑበትን ለይቶ በማወቅ ከመካከሉ ካላስወገደ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ሀገራችንን ለባዕድ ወያኔዎች አመቻችተው የሰጡ ርስታችንን መሬታችንን አስቀምተው ጥቃት ውርደት እልቂት እስራት ሞት ስደት እንዳስከተሉብን ባንዳ OPDOዎች ጋር ዳግም ስለ ይቅርታ ማሰብና መደራደር ማለት እርም መብላትና ከካንሰር ጋር መነካካት ነውና ይታሰብበት እላለሁ

ማጠቃለያ

ከላይ ለመጠቆም እንደተሞከረው አቶ ጁኔዲን ሳዶ የበደለውን ህዝብና ሀገር በርግጥ ይቅርታ ለመጠየቅ የሚያበቃ ልባዊ ዝግጅት የህሊና ንጽህና እና ከኦሮሞ ሰፊ ህዝብ ጋር እርቅ የማድረግ ቁርጠኛ አቋም ቢኖረው ኖሮ እስካሁን ድረስ ተደብቆ የወያኔን ቀጣይ ዓላማ በስውር ማራመድ አልነበረበትም

 ይሁን እንጂ እንዲህም ሆኖ ነገሮችን ለዘብ አድርገን ሁኔታዎችን እንደገና በጥሞና እንመልከት እንኳ ቢባል ይህ ግለሰብ ችግር ገጥሞት ከህወሀት ጋር ድብቅ ስምምነትና ውል አድርጎ ወያኔን ከድቶ የበደለውን ህዝብ ለመካስ አስቦ ነው እንዳይባል በሀገር በቀል ጋዜጦች ሌሎች ሚዲያዎች ከሀገር ውጪ ባሉ ሚዲያዎች በመጽሐፍ ጭምር ታትመው የተሰራጩትና የተዘገቡት ልዩ ልዩ የሚዲያ መግለጫዎች ሁሉ ግድፈት ኖሯቸው በሀሰት እሱን ለመወንጀል የፈጠራ ታሪክ ነበሩ ለማለት በቂ የመከራከሪያና የማስተባቢያ ( ለመከላከል የሚያስችለው ) ሃቅ ካለው ንጽህናውን በማስረጃ አስደግፎ አብራርቶ የማስተባቢያ መግለጫ አስቀድሞ መስጠት ነበረበት ።ነገር ግንምን ...ያለበት ዝላይ አይችልም ...” እንደተባለው ተረት አጋጣሚ ቀዳዳ እስኪገኝለት ድረስ ዝምታን መርጦ የወያኔ ታማኝ አገልጋይ ባሪያ በመሆን እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ አድፍጦ መቀጠልን መርጦታል

ይህ ተጣርቶና በማስረጃ ተደግፎ ግልጽ ሳይደረግ ትናንት የኦሮሞን ህዝብንና ሀገርን የጎዳ የነፍሰ ገዳዮች መሳሪያና ቅጥረኛ ከነበረው ጁኔዲን ጋር በይቅርታ ስም አብሮ ማላዘን አግባብነት የለውም ይህ ብቻም ሳይሆን ከዚህ ግለሰብ ጋር የተቀላቀለ፤ የተደባለቀ የተጠጋ ያስጠጋ በስሩ የወሸቀ የሸሸገ አብሮት የተቀመጠ ከአንድ ማድ የቆረሰ ( እህል ውሃ የቀመሰ) ማንም ቢሆን በታሪክና በህዝብ ፊት መጠየቅና በትውልድ መዳኘቱ ይዋል ይደር እንጂ ፈጽሞ የማይቀር ነው ይህ ተራ ግለሰብ ከኦሮሞ ህዝብ መብት ነጻነት ደምና ህይወት ከሀገር ጥቅምና ክብር ከያንዳንዳችን የጋራ አንድነት እና ሰላም ብሎም ፍትህ ማግኘት ፈጽሞ አይበልጥምብንም ።ምክንያቱም የህዝብ ደም ህይወት መብት ነጻነት የሀገር ልዕልና ከአንድ ተራ ከሃዲ ባንዳ አይበልጥብንምና ነው

ይህ ግለሰብ ከትናንት እስከ ዛሬ የህዝብን ደም ያፈሰሱትን ነፍስ ያጠፉትን ብዙሃንን እስር ቤት አጉረው የሚያሰቃዩትን እና ዛሬም ድረስ ያንኑ ድርጊት በከፋ ጭካኔ ቀጥለውበት ካሉት ባንዳዎች ጋር ሚስጢራቸውን ላለማውጣት ቃል ኪዳን ገብቶና መሃላ አድርጎ ለሌላ ቀጣይ የህወሀት ስውር ሴራ ጸባይ አሳምሮና አምታቶን የተቀላቀለን ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ከዚህ ሰው ጋር አብሮ ለመቆም እርም ነው ቁርጡ ይሀው ነው

እኛን ያፈራ የተፈጠርንበት የተገኘንበት ምስኪን የኦሮሞ ህዝብ አሁንም እየተሰቃየ ነው ስለ መብትና ነጻነቱ በሰላማዊ መንገድ ላነሳው ተገቢ የፍትህ አቤቱታ እንደ ወንጀል ተቆጥሮበት ለመቀጣጫ እንዲሆን የመብራትና የውሃ አገልግሎት ከተቋረጠበት ወራቶች ተቆጠሩ የኦሮሞ ልጅ የወያኔ አገልጋይ ባሪያ ለመሆን OPDO ባንዳ አባል ካልሆነ ማንኛውንም  አገልግሎትና የስራ ዕድል በዜግነቱ ብቻ ማግኛት አይችልም ገበሬውና ከተሜው ርስቱን መሬቱን ተነጥቆ ከቄዬው ተነቅሎ ጣሪያና ግድግዳው ፈርሶ ለድህነት እየተዳረገ ከርታታ ዜጋ ከሆነ ሰነባበተ ባህሉ ልማዱ እምነቱ ታሪኩና ቋንቋው ተጠብቆ ከእንግዲህ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳይተላለፍ “ investment “ ስም እና “master plan “ ሰበብ በየአቅጣጫው እየተበታተነና እየተናደ ነው

ይህንን ድርጊት የተቋወሙ ወጣቶች ጎልማሶች የተማረው ምሁርና ተማሪው በልዩ ልዩ ሙያ የተሰማሩት ዜጎች ህጻናት ነፍሰ-ጡሮች እንዲሁም አረጋዊያን ጭምር ህይወታቸው እየረገፈ ደማቸውን ውሻ እየላሰውና በድናቸው ሳይቀር በአውሬ እየተበላ ነው ከፊሉ ጫካ ገብቷል አብዛኛው ተሰደዋል ወይም ባልታወቀ ስፍራ ሺህዎች ለእስር ተዳርገው ከሞት እጅግ የመርግ ያህል የከበደ ስቃይ እየተፈራረቀባቸው ቢሆንም የት እንደ ታሰሩና የነገን ዕጣ-ፋንታቸውን የሚያውቅ ማንም የለም

የትናንቶቹ እነ ጁኔዲን ሳዶ የፈጸሙት ብልግና ግፍ፤ ጭቆና እና ዘርን የማጥፋት ተግባር በዜጎች ላይ የተፈራረቀው ስቃይና መከራ መፍትሄ ሳያገኝ ለፈሰሰው ደምና ለጠፋው ህይወት ካሳ ሳይከፈል ዘመድ ቤተሰባቸውን በአሬምኔዎች የጅምላ ጭፍጭፋ በማጣቸው ከወደቀባቸው ከባድ ሃዘን ሳይጽናኑ እንባቸው ሳይደርቅ የታሰሩት ሳይፈቱ ነፍሰ-ገዳዮችና በስድብ ህዝብን ያዋረዱ ልቅ ዱርዬ ተሳዳቢዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ባንዳዎችና የወያኔ መንጋ ወሮበሎች የዘረፉት የህዝብና የሀገር ሃብት ወደ ቦታው ሳይመለስ የተሰደደው ትውልድ የት እንደገባ ሳይታወቅ ወንጀለኞችን በጉያችን ወሽቀንና ደብቀን ስለ ሌላ ነገር ማውራትና እርቅ ( ይቅርታ ) እያሉ መዘላበድ ሥራ ፈት መሆንና የህጻናት ዕቃ-ዕቃ ጫወታ ነው ይልቁንም የደም ዋጋ ደም ነውና የህዝባችን ደም በአስቸኳይ መመለስ አለበት

ይህ በሌለበት ከማንም ጋር መነካካት ወይም እርም መብላት በሀገር ልዕልናና ክብር ደንታ ማጣት ነው በህዝብ መብትና ነጻነት መቀለድ ብሎም ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲሉ ስለፈሰሰው የብዙ ሺህዎች ትኩስ ደም ላይ ቆሞ ከነፍሰ- ገዳዮችና ዘራፊ ወሮበላ ወንበዴዎች ጋር መዳራት ነው እላለሁ

 ሞት ለወያኔና ባንዳዎች

ድል ለኦሮሞ ህዝብ

ዋቁማ ጮቢ Email ; ijoolleejeldu.16@gmail.com

ግልባጭ - ለኦሮሞ ፖሎቲካ ድርጅቶች

 -ለኦሮሞ ወጣቶች (Ka’ii qeerroo)

ለኦሮሞ ሚዲያዎች በሙሉ 8

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved