Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

ዶክተር ሃይሌ ላረቦ ለምስክርነት ብቁ ኣይደሉም።

ከቃሉ ኩሳ; 21/02/2014

ይህ ግለሰብ ለምስክርነት ማን ነውና ስለ ሮሞ ጉዳይ ውስጥ ገብተው ንዲፈተፍቱ የጋበዛቸው?

ምሁር ነኝ ባዩ ዶክተር ብዙ ነገሮችን ሳያገናዝቡ ለምኒልክ ጀግንናት ወይም ደግነት ምስክር ለመሆን ቸኮሉ። ምስክር መሆን መብታቸው ነው። ከፈለጉ ጥንቱን ውጥተው በጀርባቸው Aዝላው መዞር ይችላሉ። የደራረቱት የውሸት ድርሰታቸውም የተገለበጠውኣጼ ሚኒልክና Iትዮጵያ ንድነት ከሚለው ተክለጸድቅ መኩሪያ 1983 የተጸፋና ከታተመው መጽሐፍ ውስጥ ነው። በታሪክ ንደተነገራንና በብህል የሳማን ንዳደግን ኣፄ ምኒልክም ሆኑ ኣፄ ሃይለ ስላሴጉዴላዎች ለምስክርነት ኣይበቁም በማለት ኣውጀው ነበር። ምክኒያቱም ንደነ ሃይሌ ላሬቦ የመሳሰሉ የብሔራቸው ኣሰዳቢዎችና በጣም ውሸታም ስለሆኑ ነው። በሕይዋት ያለውን ሰው ሞቶዋል ብለው ምለው ስለሚመሰክሩ ነው፣ ይህ ውሳኔ የተላለፋባቸው።

ሁለተኛው ነገር ደግሞ፣ ጌቶቹ የሚተርቱትን ተረትትንሽ ቆሎ ይዞ ወደ ኣሻሮ መጠጋት የሚለውን ብህላቸውን ይዘው፣ ትንሽ ውነት ይዘው 50 ገጽ ሙሉ ዝባዝንኬ ደረደሩልን። ኣንዱም ውሸታቸውጋላ የሚላው ስም የሁሉ ኣፍሪካዊ ስም ወይም ስላምና ክርስትያን ያልሆነ ህዝብ በሙሉ የተሰጣ ስም ነው ብለው ዋሹን። ንዳውም ምሳሌ ያቀረቡልን በሰሜን Aፍሪካ የሚገኙ በርበሮችንየበርበር ጋላ ብለው ሳያፍሩ ነግሮናል። ነገር ግን ቅድም ላይ ለመጥቀስ ንደሞከርኩኝ የዶክተር ሃይለ ላሬቦ ዘመዶችጋላ ሳይሆኑጉዴላያሉ ነበር ሐባሾቹ የሚጠሩዋቸው። ስለዚህ ይህ ሰው ታሪክን ኣያውቁም፣ ወይም ኣውቀው ደብቆዋል። ወይም ዋሽቶናል ማለት ነው። ሌላው ለምኒልክ ምስክርነት ንዲሆኑ የገፋፋቸው ነገር የምኒልኪ ናት ሳቸው ዶክተሩ ኣንደነገሩንኣይናቸው የፈጠጣ ጥርሳቸው የገጠጣ ገረድ ናቸው ያሉት ሴትዮ ኣክስታቸው ይሆኑ ይሆናል። በኣገላለጻቸውም ወደዚየው ጠጋጠጋ ያሉ ነውና።

ንግዲህ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ የታሪክ ዶክተር ነኝ ባዩ የማያውቁትን ታሪክ ሲዘላብዱና ምንም በማያገባቸው ሮሞ ጉዳይ ውስጥ የገቡ ሮሞን ባህላዊ ሴቶችና ትውፍታዎችን በንቀትና በማጥላለት ነበር ብዙ ገጽ ያተቱልን። ከዶክተርነታችው በዘቀጣ መልኩ፣ ከሊቅነታቸው ጋር በማይመጣጠን ቃለቶችቅሌታም፣ ወረዳ፣ ዝቅጠት፣ተልካሻ ያሉ ሲዘላብዱ ትንሽ ንኩዋን ኣላፈሩም። በተለይ በብዙዎቹ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ ተደናቅነት ያለውና ለብዙና ረጅም ኣመታት በዲሞክራሲነቱ የጸነና ኣሁንም ተወዳደሪ ያልተገኛለትን ሮሞን የገዳ ስርዓትን በማንቆሸሽና ትርጉም የለሽ ሐተታ ኣቅርባዋልም። ነገር ግን የቀደሙት ሊህቆች ዶክተር ላጵሶ ዴሌቦ የገዳን ዲሞክራሲነትና ብቻኛው ሮሞ ሴት መሆኑን በመግለጽ፣ በተለይ ሮሞን የጉዲፈቻና የሞጋሳን ስርዓት በማድነቅ በቴሌቭዥንና ራዲዮ ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር። ንዲሁም ፕሮፌሳር ኣስመሮም ለገሳ፣ ገዳ ሮሞ ዲሞክራሲ በሚለው መጽሓፋቸው ሁሉን ነገር ኣብራርተው ኣስቀምጦታል።

ሌላው ኣቶ ተክለጻድቅ መኩሪያ የተበሉ ሰውየግራኝ ወረራ በሚለው መጽሓፋቸው ውስጥ በገጽ 805 ላይ ንዲህ ብለዋል።ሮሞ ነገድ ንደ ስላሞችም መሪያቸውን ሱልጣን ወይም ይማም ለዚያም ኤሚር ብለው ለዘለቄታ ይሾሙም።ንድኛም ንደ ክርስቲያኖቹ ንድ ነገድ የተሻለውን መርጠው በማንገስ የዘለቄታ ገዥ ኣያደርጉትም። ነገር ግን ንደዛሬ ዘመን የሬፑብሊክ ገዛዝ በየስምንት ዓመት ውስጥ ከየነገዱ የተመረጡ ሉባ የሚባለውን ሹመት ይዘው በየበኩላቸው ይዘምታሉ። ብሎ ነበር። ኣንዲሁም የራሺያ ተዋላጅና ከምኒልኪ ሰራዊት ጋር ወደ ደቡብ ዘምተው የነበረው ሰው ሮሞችን ይኑ ብሌን ይቶ, ጀግኖችና, ጦረኞች በተለይ በፈረስ ውጊያ በምስራቅ ፍሪካ ተወዳዳሪ ንደሊላቸው ሲገልጽ፣ Aስተዳደር ስርዓታቸው ሪፑብሊክ መሆናቸውን ደጋግመው ገልጾታል። ኣንዲሁም የታላቁ ብሪታኒያ ተወላጅ ጆን ከሜዲ የተባለው ሰውሮሞች ጦረኞች ናቸው። ነገር ግን ለጦርነት ይቾክሉም። ትክክላኛ ውሳኔ ላይ ከደረሱ በሁዋላ ነው ሁሉም ለዘመቻ የሚጣደፈው ብሎ 1878 ባሳተመው መጽሓፉ ውስጥ ኣስፍሮዋል። በተጫማሪ Aስተዳደራቸው ስርኣት (ሮሞ ማለቱ ነው) ሪፑብሊክ ነው ብሎ ነበር።

ንግዲህ ይህን በሚመስል መልኩ ብዙ ሊቃውንቶች ወቢ/ምስክር ለሆኑላት የገዳ ስርዓትን የዘለፈውና ለከት ለሌለው 50 ገጽ የዶክተር ሃይሌ ላረቦ ሐተታ ከዚህ የበለጣ የምላው የለኝም። በደረደራቸው ቃለቶችወረዳ፣ ቅሌታም፣ ዝቃጭ የሚሉትን ለመጠቀም Aልፈለኩም። ሌላው ነገር ደግሞ ስለ ሮሞ ሊህቃኖች ብዙ ብዙ ብላዋል። የተለመዳ የስድብ ውርጅብኛቸውን Aውርዶባቸዋል። ዶክተር ሰፋ ጀላታን፣ ዶክተር ነጋሶ ግዳደን ሌሎችም የዶክተር ሃይለ ላሬቦ የስድብ ሰላባዎች ሆነዋል። በነገራችን ነዚህ ሰዎች በሕይዋት ስላሉ መልሳቸውን ሊሰጡ ስለሚችሉ ብዙ Aያሳስበኝም። ነገር ግን በግለሰቦች Aሳቦ ሮሞን ህዝብ መስደባቸው ነው ተልካሻነታቸው የሚጎለው። ሌላው ዳግሞ ከላይ ንደገልጽኩኝ ሮሞ የተሰጣውን ስም የኛም ነው ብለው ሸክሙን ንደተካፈሉልን ሁሉ Aርስ ክፍለ ሀገር የኛም ነው፣ ወይም የጋራችን ነው ብሎናል። ንዲህማ ካሰቡ የኩሽ ምድር በሙሉ የጋራችን የኩሽ ህዝቦች ንጂ ከጋዛ ወይም ከኣረቢያ በተለያየ ጊዜ ተለቃቅመው የመጡ የሐበሻ (ኣቢሲኒያ) መጤዎች ምድር ልነበረችም። ንዲህ ካልን ዘንዳ ደግሞ ሮሞ Aግዛው መቆም ሲገባዎት የጥቅት ደብተራዎችን ልባወለድ ድርስት Aጠረቃቅመው ሮሞ ላይ ባልዘመቱ ነበር።

ሌላው የሚገርመው የዶክተሩ ተረት ደግሞ ከቀደምት የደብተራዎች የተረት ድሪቶ ውስጥ ቆርጣው ያስናበቡን በሚከተለው መልኩ ነው።Aሥራ ስድስተኛ ዘመነ-ምሕረት ሁናቴውን በቅርቡ ካዩት Iትዮጵያ ጸሓፊዎች ልጀምር።Aገሩበጋላ E ተመዝብሮ በረኻና ጫካ በመሆኑ Eንስሳና ከዱር Aራዊት በስተቀር ሰውም ሆነ Eርሻ በፍጹም የለበትም። ቱላማ የሚባል ጋላ መጥቶ፣መንፈቁን ጐጃም ምንም ሳያስቀር ደምስሶ Aጠፋው፤ ሴቶችንና ከብትን ማረከ። የገደለው ሰው ቊጥር ስፍር የለዉም።ጋላ ጐጃምን መውረር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ Eንደዚህ የገደለበትና የማረከበት ጊዜ ከቶውኑ የለም። ክርስቲያኑ ብቻ Aይደለም ይኸ Aይነት Eልቂትና ጥፋት ከጋላ የደረሰበት። ታዲያ ያመለጠ Iትዮጵያ ኅብረተሰብ Aልነበረም ቢባል ሐሰት Aይሆንም። ያኔ ሻንቅላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ Eከላዊው መንግሥት Aስቸኳይ Eንዲደርስለት ያቀረበው ጩኸት፣የከብትና የሰው ምርኮ ወሰደብን፤ ስፍር ቊጥር የሌላቸውን ጀግኖቻችንን ገደለብን፤ የቀሩት ጀግኖቻችን የሴት ፍርሀት ይዟቸዋልና፣ ጌታችን [ንጉሥ] ሆይ Eንዲትታደገን ፈጥነህ ድረስልን ነው የሚለው። ግድያው Aረመኔነት ሳይሆን Aውሬነት ነው። ካልሰለበ፣ ጡት ካልቈረጠ፣ ሆድ ካልዘረጠጠ፣ ቸብቸቦ ካልሰበሰበ ስሜቱ Aይቀሰቀስም። Eነዚህ ድርጊቶች የጀብዱነቱና የታላቅነቱ ዋና መግለጫውና መስፈርያው ነበሩና።

Eንግዴህ የዛሬውሮሞ የትላንትናውጋላ ነው ካልን፣ በዚህ ስም የሚጠራው ኅብረተ-ሰብ Iትዮጵያና Iትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰው ጉዳትና ጥቃት፣ የፈጸመው የሰውና የከብት Eልቂት፣ የንብረትና የታሪክ ቅርስ ጥፋት፣ በሰው Aንደበት ተገልጾ፣ በመጻሕፍት ተጽፎ Aያልቅም ማለት ይቻላል። ይላል። በወቅቱ ደብተራው ኣባ ባሕርይ ሮሞ ጠላትነት ለመግልጽ የደረሱት ሐተታ ነበር ቆርጦ ያስነበቡን። ነገር ግን ብዙ የውጭና Aንዳንድ ገር ውስጥ ጸሀፊዎች ያቀረቡት ዘገባ ከዚህ ተረት የተለያ ነው። በሴት ልጅና, በሕጻናት ላይ የሚጨክኑ ሐባሾች ንጂ ሮሞች ይደሉም። ዶክተሩ ራሳቸው ይህን ያውቃሉ። ነገር ግን ጌቶቻቸውን ስለ ፈሩ ሀበሳ/ሀበሻ ለመሆን ተንበረከኩ። ወንድ ልጅን ማሪኮ ጁን ቆርጦ Aንገት ላይ የሚያስሩ ከነIግዚብቱ ፎቶ የተነሱ የቆረጣ ሰለባዎች Aውሮፓ በተመዘክሮች ተከምረው የሚታየው

ድርጊቱ የሓበሾች መሆናቸውና ራሳቸውም ዶክተሩ የተማሩ የደጉ ሰው ናቸው። ንዲሁም የምርኮኛውን ቆዋንጃ ቆርጦ የሰውን ልጅ ባሪያ የሚያዳርጉ፣ የራሳቸው Aገልጋይ የሚያዳርጉና ሌላውን ሳልፎ ረቦች ሲቸበችቡ የነበሩ ሐባሾች መሆናቸውን ብዙ ታሪኮች ተጽፈው Aውሮፓውያን ቤተመጽሐፎችንና ቤተመዘክሮችን ያጣበቡ ይገኛሉ። በሌላ በኩል ግን ሮሞው ምርኮኛውን ተንከባክቦ በጉዲፈቻ የራሱን ልጅ በማድርግ ወይም በጅምላ ወደ ብሔሩ በሞጋሳ ስርዓት የራሱ ጎሳ በማድረግ የሰውን ልጅ ሰብኣዊ ክብሩን በመጠበቅ ብሮ ይኖር ነበር። ለዝህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የኣጼ ሱስኒዮስ ታሪክ በቂ መስረጃ ነው። ይህን ሌላ ጊዜ መለስበታልሁ።

ሌላው ዶክተሩ ራሱ ኣልፎ ኣልፎ ንደጠቀሳቸው ሮሞ ልጅ ይወዳል፣ ያንከባክባል፣ ለክብርና ለጀግንናት ያባቃል። ይህ ደግሞ ብዙ ሊቆች በብዛት ጽፈዋል። ንዲሁም ሴት ልጅ፣ ሽማግሌዎችና ልጆች ሮሞ ዘንድ በጦርነት ይካፈሉም። ከጦር ሜዳ ራቅ ይላሉ። የተቀራኒውን ጎራ የሆኑ ሴቶች ጦርነት ውስጥ ተቀላቅለው ቢገኙ ንኩዋን በምርኮ ከመውሰድ ውጪ ጁን ሴት ልጅ ላይ ይሰንስዝሩም። በሌላ በኩል ግን ሐበሾች በዋሻ የተደባቁትን ሴቶች ህጻነቶችን ሽማግሌዎችን ያርዳሉ፣ የሰቶችን ጡት ይቆርጣሉ፣ ሆዳቸውን በስላት ይዘራጥጣሉ፣ በጅምላ ሰብስባው ያቃጥላሉ። ይህ ታሪካቸው ደግሞ በውጪ ጸሐፊዎች በወቅቱ የነሱን ሰራዊት ተከትለው ሲሆዱ በኣይናቸው ያዩትን መዝግባው Aልፎዋል።

ይቀጥላል

ከቃሉ ኩሽ__

Please read  Cause of Haile Laredo    http://www.ca4.uscourts.gov/opinions/Unpublished/982234.U.pdf

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved