Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

Cancer Prevention Diet Mr. Banti Qannoo Biduu

‹‹አመጋገባችንን ከተፈጥሯዊው አካሔድ ላለማራቅ መንቃት ይኖርብናል›› አቶ በንቲ ቀኖ ቢዱ፣ የፋርማሲ ባለሙያ

Wednesday, 11 April 2012 10:12

By Henock Yared

Hits: 289

ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሆኑት 78 ዓመቱ አረጋዊ አቶ በንቲ ቀኖ ቢዱ የፋርማሲ ባለሙያ ናቸው፡፡ በአሜሪካ በፋርማሲ የባችለር ዲግሪ፣ ከዓመታት በኋላም በድኅረ ምረቃ ትምህርት ከካናዳ ቶሮንቶ በሔርቦሎጂ (ባህል መድኃኒት) ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡

45 ዓመታት በላይ በሙያቸው በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ መድኃኒት ቤቶች (ፋርማሲዎች) የራሳቸውን ጭምር በማቋቋም ሲሠሩ፣ ባለፉት 10 ዓመታት በመድኃኒት አስመጪ ድርጅት ውስጥም በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡ ከሙያቸው አገልግሎት ባሻገር ኅብረተሰቡ ምግብ ተኮር የጤና አጠባበቅ መንገድን ይከተል ዘንድ የተለያዩ መጻሕፍትንና መጽሔት አዘጋጅተው በማሳተም አሰራጭተዋል፡፡ አንደኛው ‹‹ካንሰርን መከላከል›› (Cancer Prevention Diet) የትርጉም ሥራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው መጽሐፋቸው ‹‹ምግብ መድኃኒቴ›› ይሰኛል፡፡ አምስት ጊዜ ታትሞላቸዋል፡፡ ‹‹የገዛው ሁሉ ረክቶበታል›› ይላሉ፡፡ ለሕትመት የተዘጋጀው ደግሞ ‹‹ምግብ ተኮር የጤና አጠባበቅ መመርያ›› ይባላል፡፡ አቶ በንቲን በሥራቸው ዙርያ ሔኖክ ያሬድ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የፋርማሲ ሙያ ሕይወትዎ ምን ይመስላል?

አቶ በንቲ
- ከተወለድኩበት ወለጋ ክፍለ አገር አዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ ትምህርቴን በአቃቂ አድቬንቲስትና በኮተቤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 2 ደረጃ ስማር ቆይቼ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቱ ኮሌጅ ገባሁ፡፡ ፍላጎቴ ወደ መድኃኒቱ በማዘንበሉ ዲፕሎማዬን ካገኘሁ በኋላ ለከፍተኛ የፋርማሲ ትምህርት አሜሪካ ተልኬ በፋርማሲ የባችለር ዲግሪ ማግኘት ችያለሁ፡፡ አገር ቤት ከተመለስኩ በኋላ 45 ዓመት በፊት በድሬዳዋ መድኃኒት ቤት (ፋርማሲ) ከፍቼ ሕዝቡን አገለግል ነበር፡፡ ፋርማሲዎች ባልነበሩበት ጊዜ የመጀመርያ የችርቻሮ መድኃኒት ፈር ቀዳጅ ነበርኩኝ፡፡ በአዲስ አበባም ተክለሃይማኖት መድኃኒት ቤትን አቋቁሜ 25 ዓመት ሕዝቡን አገልግያለሁ፡፡ በሐዋሳና በአምቦም በተመሳሳይ ሠርቻለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ስምዎ ከመጽሐፎች ጋር ተያይዞ ይነሣል፡፡ ለሰው ልጅ መድኃኒት ምግቡ ነው በሚል መርሕ ያሳተሟቸው አሉ፡፡ መድኃኒት ከመቸርቸር ወደ ምግብ አስፈላጊነት ያመሩት እንዴት ነው?

አቶ በንቲ
- ምግብ ተኮር ስለሆነ የጤና አጠባበቅ ከማውራታችን በፊት ስለበሽታ ያለንን ግንዛቤ ማስተካከል ተገቢ ይሆናል፡፡ ሰውነት በተፈጥሮው ራሱን ከበሽታ የመከላከል ኃይል አለው፡፡ ሰውነታችን ይህንን ተፈጥሯዊ አቅሙን አጥቶ ተግባሩን ማከናወን ሲሳነው በበሽታ ተጠቃ ወይም ተሸነፈ ልንል እንችላለን፡፡ ሰውነት አለው ያልነውን ራሱን የመከላከል አቅም የሚያገኘው ከምንመገባቸው ነገሮች ነው፡፡ ስለዚህ ሒፖክራተስ እንዳስተማረው ምግብ መድኃኒት ነው፡፡ ሰውነት ተፈጥሯዊ ተግባሩን ማከናወን ሲያቅተው በበሽታ ተጠቅቷል፤ ለዚህ ደግሞ ይሰጥ የነበረው ሕክምና በበሽታ ምልክቶች ላይ ያተኮረ እንጂ የበሽታን ሥር መሠረት በማወቅ የማስወገድ ብልሃት አልታከለበትም ነበር፡፡ በበሽታ መጠቃትም ሆነ ከበሽታ መላቀቅ መሠረታዊ ጉዳዩ አመጋገባችን መሆኑን ብዙዎች ልብ ያላሉት ጉዳይ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ሚቺዮ ኩሺ The Cancer Prevention Diet በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ የሰው ልጅ አመጋገቡን ከተፈጥሯዊ ወደ ቴክኖሎጂያዊ የአመጋገብ ሥርዓት ሲለውጥ መታመም አበዛ ማለታቸውም የሕመምና የጤናችን ጉዳይ በአመጋገባችን ውስጥ መኖሩን ለመናገር ፈልገው ነው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያዊውን አብዮት በሰፊው ወደመቀላቀሉ በመሆኗ ከአሁኑ አመጋገባችንን ከተፈጥሯዊው አካሔድ ላለማራቅ መንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህም ማኅበረሰባችን በጤንነት የመቆየት ዕድሉን ሰፊ ስለሚያደርገው ከሁሉም የጥበብ ዘርፎች ይበልጥ ትኩረት ልንሰጠው ይገባናል በሚል ትኩረቴ ምግብ ላይ ሆኗል፡፡ ዘመናዊ ብለን የያዝነው የአመጋገብ ልምዳችን ጤናችንን አደጋ ውስጥ እየከተተው መሆኑን ከተገነዘብን ሙሉ ወደ ሆኑ ምግቦች መመለሳችን የግድ ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- ሙሉ ወደ ሆኑ ምግቦች መመለስ ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?

አቶ በንቲ
- ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን በማንኛውም መንገድ ያልተገፈፉ መሠረታዊ የምግብ ዓይነቶች ስናካትት አመጋገባችን ሙሉ ነው ሊባል ይችላል፡፡ እነዚህም እንደጥቅል ጐመን፣ ቆስጣና ሰላጣ የመሳሰሉት ለምለም ቅጠላቅጠሎች፣ ፍራፍሬዎች፣ እንደድንች፣ ሽንኩርትና ዱባ ያሉ አትክልቶች፣ ወተትና የወተት ተዋጽዖዎች፣ ጥራጥሬና ያልተፈተጉ እህሎች፣ ፕሮቲኖችን የያዙ እንደባቄላ፣ ኦቾሎኒና አደንጓሬ ቅባቶች ሲሆኑ፣ እነዚህን ከላይ የተገለጹትን በተገቢው ልክና ከየዓይነቱም በየዕለቱ በአመጋገባችን ውስጥ ማካተት ተገቢ ነው፡፡ ጠቃሚነታቸው እነርሱን በብዛትና በተከታታይ መመገብ ማለት እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል፡፡ ከነዚህ ጋር ፈጽሞ ሊዘነጋ የማይገባው ወሳኝ ምግብ ውኃ ነው፡፡ አንድ ሰው 24 ሰዓት ውስጥ 6 እስከ 8 ብርጭቆ ውኃ እንዲጠጣ ይመከራል፡፡

ውኃን በፈዋሽነቱ ለመገልገል የማንም ፈቃድ አያስፈልግም፡፡ ለሕይወት ዋነኛው አስፈላጊ ነገር ነው ሰውነታችን የሚፈልገውን ያህል ውኃ ባለመጠጣታችን ራሳችንን ለከፍተኛ የጤና ችግር እናጋልጣለን፡፡ ይህም አላዋቂነት ነው፡፡ ሰውነታችን ለውኃ እጥረት ሲጋለጥ አንዳንድ አካላት በሙሉ ወይም በከፊል ሥራቸውን ያቋርጣሉ፣ ይጎዳሉም፡፡ ውኃን ማግኘት ለብዙዎቻችን ቀላል ነው፤ ግን በቂ ውኃ አንጠጣም፡፡ አሁንም ሰውነታችን በውኃ እጥረት ይጨማደዳል፤ ይኮማተራል፡፡ ሰውነታችን ለውኃ እጥረቱ ሲጋለጥ ጉበትን ጨምሮ ዋና ዋና ሥርዓቶቻችን ይጠቃሉ፡፡ ጡንቻዎችና የአጥንት መገጣጠሚያዎችም ያለውኃ ምንም ሊሠሩ አይችሉም፡፡ የውኃ እጥረት ሊያመጣቸው ስለሚችላቸው ችግሮች በሳይንስ ከተረጋገጡት መካከል የነርቭ መቃወስ፣ የመርሳት ችግር፣ የጡንቻ መዳከም፣ የእጅና የእግር ሽባነት፣ ቃል የማውጣት ወይም መናገር ያለመቻል ችግር፣ የንቃት ማጣት፣ የሚጥል በሽታና አንጎላችን ጋር የተያያዙ ችግሮች ይገኙበታል፡፡ ውኃና ፈሳሽ ሁሉ አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉም ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ሰዎች ማንኛውም መጠጥ ጥማትን ያረካል ወይም ውኃን ይተካል ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ስህተት ነው፡፡ ውኃ ያልሆኑ መጠጦች ሁሉ የተለያዩ ኬሚካሎችን ስለሚይዙ ውኃነታቸውን አጥተዋልና የነርቭ ሥርዓታችንን በሚቆጣጠረው ማዕከል ይለወጣሉ፡፡

ወተት እንኳን ውኃን አይተካም፡፡ ለጥማት መጠጣት ያለብን ውኃን ብቻ ነው፡፡ በሌሎች ፈሳሾች የምናገኘው ዕርካታ በጣም ጊዜያዊ ነው፡፡ ሻይ፣ ቡና፣ ሶዳ (ለስላሳ መጠጦች) መቼም ውኃን ሊተኩ አይችሉም፡፡ ውኃ ባልሆኑ ፈሳሾች ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችን ባሕሪ ለመገንዘብ ካፌን እንመልከት፡፡ አንድ ስኒ ቡና 80 ሚሊ ግራም ካፌን ሲኖረው፣ አንድ ሲኒ ሻይ ወይም ሶዳ 50 ሚሊ ግራም ካፌን ይይዛሉ፡፡ ካፌን በሰውነታችን ውስጥ ያለው ውኃ በመቀነስ ለድርቀት ያጋልጠናል፡፡ ከመጠጦቹ ጋር ከምናስገባው ውኃ በላይ በሽንት እናስወግዳለን፡፡ ካፌን በእንቅልፍ ወቅት የአንጎልን ተግባር የሚቆጣጠረውን የሜላቶንን ተግባር ያዛባል፡፡ ውኃ ራሱ ብቻ ነውና ሊጠማን ወይም ውኃ መጠጣት በሚገባን ጊዜ ራሱን ውኃን እንጠጣው፡፡  ምግብን መመገብ ለጤናችን የሚኖረው ወሳኝ አስተዋጽኦ በመመገብ ወይም ባለመመገባችን ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ የአመጋገብ ልምዳችንም ትልቅ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህም ይህንና ሌላውን ሁሉ የሚመለከት ምግብ ተኮር የጤና አጠባበቅ ያስፈልጋል ብዬ ወገኖች አንብበውት ጤናቸውን እንዲጠብቁበት ለማድረግ መጻሕፍትን ማዘጋጀትና ለኅብረተሰቡም ማቅረብ ጀመርኩ፡፡ ‹‹ምግብ መድኃኒቴ›› መጽሐፌ በተከታታይ ለአምስተኛ ጊዜ አሳትሜ ኅብረተሰቡ እንዲያነበው ሳደርግ የገዛው ሁሉ ረክቶበታል፡፡

ሪፖርተር፡- ካንሰርን ከመከላከል አንጻር ያወጡት መጽሐፍስ?

አቶ በንቲ
- ካንሰር (ነቀርሳ) የሥልጣኔ በሽታ ነው፡፡ ከአመጋገብ ሥርዓት መበላሸት የሚመጣ ነው፡፡ ከአመጋገብ ንጥረ ነገሮች አለመስተካከልም ይመጣል፡፡ በዓለም ዙርያ ካንሰርን ለማዳን ሰዎች መብላት ያለባቸው ለምለምና ቢጫ ቀለም ያላቸውን አትክልቶችና ፍራፍሬዎች በመመገብ ከዚህ በሽታ ነፃ ወጥተዋል፡፡ ይህን በመሰለ ሕክምና የሳንባን፣ የሆድንና ሌሎች ዓይነት ካንሰሮችን ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በጃፓን አገር ጥናት ተካሒዶ አስፈሪውን የካንሰር በሽታን ከመቀነስም አልፎ ብዙ ግለሰቦች ድነው ተገኝተዋል፡፡ ካሮትን፣ እስኩዋሽን፣ ቲማቲምን፣ ሰላጣንና ቅጠላ ቅጠሎችን በመብላት ያዘወተሩ ግለሰቦች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ደረቃ ደረቅ ፍራፍሬዎችን፣ ኦቾሎኒን የመሳሰሉት እና እንጆሪ ሃባብ የተመገቡ ሁሉ ጥሩ ውጤት ላይ መድረሳቸውን አስመዝግበዋል፡፡

በተጨማሪ ግለሰቦች ከካንሰር ለመዳን በቂ ዕረፍት እንዲኖራቸው ከጭንቀት፣ ከብስጭት ከፍርሐት ነፃ መሆንና ያልተበከለ አየርን ማግኘት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ካንሰርን ለመከላከል 100 በመቶ ምግቦችን ፕሮሴስድ ሳይሆኑ (በፋብሪካ ሳይቀናበሩ በተፈጥሯዊነታቸው ለምሳሌ ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎችን፣ ካሮትን፣ ድቡልቡል ጐመንን፣ ብሪኮሊን፣ (አበባ ጐመኖችን) አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎችን፣ ጐመን /እስፒናች/ ያበሻ ጉራጌ ጐመን፣ ሽንኩርቶችን፣ አስፓራገስን፣ ቀይ ስርን፣ ዝኩኒን፣ ቲማቲምን፣ ጂንጀር ኮምፕሬስ (ዝንጅብል) ማሽላን፣ የሰሊጥ ፍሬን፣ እንጉዳይን፣ ስንዴን፣ ገብስን፣ አጃን ከነአሰራቸው ግለሰቦች እንዲመገቡ ማስቻል ወይም ቢመገቧቸው ፈውስ ያስገኛሉ፡፡
ስለዚህ ካንሰርን በምግብ መከላከል (Cancer Prevention Diet) በተሰኘውና በተረጐምኩት መጽሐፍ ኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ አድርጌያለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ በአገራችን ከየሆስፒታሉ ካሰባሰብኩት መረጃ የካንሰር ስርጭት በፊት ሦስት በመቶ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተጠናከረ ጥናት የሚታይ ቢሆንም፣ በቂ ግን አይደለም፡፡ ‹‹ክሮኒክ ዲዚዝ›› (አደገኛ በሽታ) ነው፡፡ መጽሐፉን በተረጐምኩበት 20 ዓመት በፊት በሽታው በጣም የሚያሳስብ አልነበረም፡፡ በአሁን ጊዜ ያሉን ባለሙያዎች ብዙ አይደሉም፡፡ 80 ሚሊዮን ሕዝብ በቂ አይደለም፡፡ ራሳችንን በራሳችን የማከሙ የመከላከሉ ሁኔታ ግንዛቤን ለማሳደርም ነው በመጽሐፍ ያቀረብኩት፡፡ 

ሪፖርተር፡- በባህል መድኃኒት ዙርያ የሚሠሩትስ?

አቶ በንቲ
- በድኅረ ምረቃ ያጠናሁት ሔርቦሎጂ ነው፡፡ የመድኃኒት ዕፅዋት ጥናት ማለት ነው፡፡ ይህም ዕፀዋትን በአገር ደረጃ ተክሎና አምርቶ መድኃኒትን ቀምሞ ለኅብረተሰቡ ጥቅም ማዋል ማለት ነው፡፡

ሔርባል የሚባለው በአገር ውስጥ ያሉትን ዕፀዋት መድኃኒት ቀምሞ ለሕዝብ አገልግሎት ማዋሉ የባህል መድኃኒት ነው፡፡ በተለይ ዘመናዊ የፋርማሲ ዕውቀት በመማሬም በመሥራትም ሰፊ ግንዛቤ ስላለኝ በአገራችን ብዙ ያልታወቀውን ግን 85 በመቶ የሚሆኑ ወገኖች በዚህ የመድኃኒት ክፍል እየተጠቀሙ ስለሆነ በርሱ ላይ አተኩሪያለሁ፡፡ ስለዚህ የኔ ፍላጐት ዕፀዋቱን ለመትከል መሞከር፣ ከተተከሉና ከተመረቱ በኋላ ለመድኃኒትነት ቀምሞ ለኅብረተሰቡ የማቅረብ ፍላጎትም አለኝ፡፡ ግን ያለሀብት ስለማይሆን ምናልባት ጥቂት ወገኖች በሐሳቤ ተስማምተው የሚረዱኝ ሆነው ከተገኙ በአገር ዕፀዋት አስፈላጊ የሆኑትን መድኃኒቶች በማምረት በሽታን ለመከላከልም ሆነ ለማዳን ሙከራ የማድረጉ ሐሳብ አለኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ድጋፍ የሚያደርግልዎት ተቋም አለ?

አቶ በንቲ
- የሔርባል ሳይንሱ ጉዳይ ለአገራችን አዲስ እንደመሆኑ መጠን ልምዱ አብሮ የመሥራትና የማሻሻል ሁኔታ ለኅብረተሰባችንም አዲስ በመሆኑ እስካሁን የምለፋው ብቻዬን ነው፡፡ የዕፀዋት መድኃኒቶቹን መዝግቤ አስቀምጫለሁ፡፡ መጽሐፍም ጽፌያለሁ፡፡ የተለያዩ ዕውቀቶችን በመገናኛ ብዙኀን አሳውቄያለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ጥንስሱ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ የሚቀጥል ሰው ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡

Cancer Prevention Diet

This adives give as what types of food must eat to prevent Cancer, mostly we must eat unfabricated foods, green, greins, fruits , milke etc.

The peoples must choice their food properly. Please excplain for you friends 

 

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved