Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኛ ሠላም ብናጣም ለእናንተ ሠላም ይሁን!

 

 የኢትዮጵያ ሚዲያ እና….መቼ ለእውነት ይቆማሉ!

1 ቀን 27/03/2008 .

ይህ ጽሑፍ ለመሞጫጨር ያስገደዱኝ የኢትዮጵያ ሚዲያ፣ የገዥው ፓርቲ፣ ደጋፍዎች እናሁሉምን ነገር አሸባሪ፣ ጠባብ እና ትምህክት አድርገው ማቅረብ የተለመዳ ቢሆንም ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ይህን ጉዳይ በሚገባቸው ቋንቋ እንዲረዱ ለማሳማት ነው፡፡ በመጀመሪያ ለፊደላት እና ቃላት ግድፈት ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

ለመግቢያ የተጠቀምኩት የአስር ዓመት የከተማ ልማትና ቤቶች / (2008-2017) የዘርፍ ዕቅድ ነው፡፡ በሦስተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ፕሮግራምን በተመለከተ ፈርጃቸውን መሠረት ያደረገ ፕላን ከሀገራዊ የከተማ ስፓሺያል ፕላን ጋር በተቀናጀና በተናበበ ይሰራል፡፡ በፕላን በጸደቀው የመሬት አጠቃቀም 30 በመቶ የመንገድና መሰረተ ልማት፣ 30 በመቶ የአረንጓዴና ለሕዝብ የጋራ አገልግሎት የሚሰጥ ክፍት ቦታ እና 40 በመቶ ግንባታ ምጣኔ መሰረት ተግባራዊ መሆኑ ያበስራል፡፡

 የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ማሻሻል ፕሮግራምን በተመለከተ 300 ሺህ / እና ለኢንዱስትሪ ፓርክና ዞን እንዲሁም ለተለያዩ የልማት ስራዎች የሚያስፈልግ የለማ መሬት ተዘጋጅቶ ይቀርባል ይላል፡፡ የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ዋጋን ማረጋጋት የሚችል፣ አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለው ሥርዓት እንዲኖረው ይደረጋል ይላል፡፡ ከዚህ ውስጥ የአዲስ አበባ ስንት ሺህ / እንደሆነ በግልጽ ባያስቀምጠውም 300 ሺህ / ውስጥ ወደ120 ሺህ / እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በጣም የምገርመው ግን 130 ዓመታት አዲስ አበባ እሰከ ዛሬ 2008 ዓም 52 ሺህ / ብቻ ነች፡፡ ይህ ሁሉ መሬት ከየት ሊገኝ ነው? የዛሬዋን አዲስ አበባ ሁለት እጥፍ በላይ ለመፍጠር ታሳቢ ተደርጓል፡፡ 8ሚልዬን ህዝብ ከየት ሊመጣ ነው?

ልማት ሰውን ፈልጎ ሄዶ አያውቀውም፡፡ ሰው ግን ልማት ይምጣልኝ ብሎ ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ሰው ጉልበቱን፣ አእምሮውን፣ ጊዜውን እና ሀብቱን በማፍሰስ ልማትን ያገኛል፡፡ ልማትን የሚጠላ ሰው እስከ ዛሬ አልተፈጠረም፡፡ ሰው እስከ ሆነ ድረስ ለወደፊትም አይፈጠርም። በዚህ 2 ምክንያት የልማትን ዕቅድ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ይደግፈዋል። የኦሮሚያ ወጣቶች ግን ይህን ዓይነትልማትየተባለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ክፉኛ እየተቃወሙት፣ እየሞቱ ነው፡፡ ለምን ሲባል የኢትዮጵያ ሚዲያ፣ ገዥው ፓርቲ እና ደጋፍዎች ልማቱን አለወቁም እየሉ ነው፡፡ በእውነት አለወቁምን? ሲያስፈልጋቸው ደግሞ በሌሎች ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ባለቸው ሰዎች ተገፍተው ነውን? አያውቁም ሲባሉ የአእምሮ ዝንፈት ሰለባዎች ናቸው ለማለት ተፈልጎ ይሆን? በቁልፍ የስልጣን ቁንጮ አይበቁም ያላችሁት ኦህዴድን እንጂ አጠቃላይ የኦሮሚያን ወጣቶች እንዳልሆን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ በኦህዴድ መስተታውት ሌሎችን ባትመለከቱ መልካም ነው፡፡

ይለማሉ የተባሉት ኣከባቢዎች ገበሬዎች ከረጅም ዓመታት ጀምሮ በተለይ ከሃያ ዓመት ወዲህ ያለ ካሳ፣ በትንሽ ካሳ፣ ያለ በቂ ዝግጅት ከመሬታቸው በማፈናቀል የኑሯቸው መሰረት ከሆነ ማሳቸው አፈናቅሎ በገዛ መሬታቸው ድሆች እንዲሆኑ በማስገደድ ዘበኝንት፣ጉልበት ያለው ለቀን ሠራተኛነት፣ እናትና ሴት እህቶቻችን ለቤት ሠራተኛነት፣ለሴተኛ አዳርነት፣ቻሉት ደግም ወደ ስደት ኑሮ እና አቅም ያጡ አባቶችና እናቶች ወደልመና አሠማርቷል። ይህን ክስተት ያላየ የኢትዮጵያ ሚዲያ እና ህዝቦች አላችሁን? የኦሮሚያ ወጣቶች መጮኸ አግባብ አይደለም የሚንላው ምን መሠረት ይዘን ነው?

ዛሬ የአዲስ አበባ ስፋት 52 ሺህ ሄክተር ደርሷል፡፡ የነባር ህዝቦች ባህል፣ቋንቋ እና ሰዎቹ ራሳቸውን ከአዲስ አበባ ወረዳዎች ውስጥ አንድም ቦታ የሉም፡፡ ጠራርጎ ማፈናቀል ይህ ነው፡፡ በወረራ የተያዘ ሀገር ላይ እንኳን ይህ ዓይነቱ ግፍ አልታየም፡፡ ግን ገዥም ተገዥም አንድ ሀገር ህዝቦች ነን ማለታችንን ቀጥለናል፡፡ እንዴት ይሆናል? ተፈናቀዩን የኦሮሚያ ገበሬዎች ወደ ጎን እየተገፋ መድረሻ ማሳጣቱን በዕውን እያየን አይደለንም? የኦሮሚያ ወጣቶች መጮኸ አግባብ አይደለም የሚንላው ምን መሠረት ላይ ቆመን ነው?

ኢህአዴግመሬት የህዝብና የመንግስት ነውየሚል ፖሊሲው በህገመንግስቱ ጭምር ማስፈሩና መሬቱን በልማት ስም እንደፈለገ በማድረግ ላይ ይገኘል፡፡ አንዳንዴም መንግስት ማለት ህዝብ ነው ይላል። ስለዚህ መሬት ሙሉ በሙሉ የመንግስት ነው እንደማለት ይሆናል። ለዚህ ማረጋገጫ መሬትን ማስተዳደር ያለበት መንግስት ነው ይላል፡፡ ሌላኛው የችግር ምንጭ የሊዝ አዋጅ ሲሆን ገጠር ቀበሌዎች ወደ ከተማ ሲገቡ ዋነኛ መተዳደርያ ሃብታቸው የሆነ ማሳቸውን በአነስተኛ ዋጋ ጣራና ግድግዳ ብቻ ይከፈላቸዋል፡፡ አንዳንዴም ከቀበሌ አመራሮች ጋር በመመሳጠር ያለ ካሳ መሬታቸውን ይነጠቃሉ። በመሬት ጉዳይ ላይ የህግ የበላይነትና ፍትህ በካድሬዎች እጅ ብቻ ተጠቅልሎ ከገባ ዘመናትን አስቆጥሯል። የዚህ በሽታ ተጠቂ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆንም የኦሮሚያ ገበሬዎች በተለያ ሁኔታ በመጠቃት ላይ 3 ይገኛሉ፡፡ ምክንየቱ ብዙ ቢሆንም ዋነኛው መሠረት ግን ለአዲስ አበባ ቅርበት ላይ በመሆኑ፣ መሃል ሀገር በመሆኑ እና ዲቃላ የተዳቀለ ኦህዴድ እየመራው በመሆኑ ነው፡፡ ባለፉት 125 ዓመታት በተለይም 15 ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ስር የሚተዳደሩ ገጠር ቀበሌ ነዋሪዎች ከልማቱ ተጎጂዎች እንጂ ተጠቃሚ ኣለመሆናቸው የኢትዮጵያ ሚዲያ እና ህዝብ ጠንቅቃው ያውቃሉ። የኢትዮጵያ ሚዲያ እና ህዝቦች ምን አላችሁ? የኦሮሚያ ወጣቶች መጮኸ አግባብ አይደለም የምንለው ምን መሠረት ይዘን ነው?  

እንደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ሪፖርት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት 5 ዓመታት ለአንቀሳቃሾች የተደረገ ድጋፍን በተመለከተ 15,745 ሄክታር ቦታ፣ 567 ህንፃዎች እና 16,753 ሼዶች ተዘጋጅተው አገልግሎት ላይ መዋሉንና ከተጣለው ግብ በላይ ተፈጽመዋል ይላል፡፡ ሁሉም የተቋቋሙ ማህበራት አትራፊ መሆናቸውን በሀገር ውስጥ ሚዲያ አታካች ወሬ ሆኖብናል፡፡ ሆኖም ግን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ወደ 299 በማህበራት የኦሮሞ አርሶአደሮች ከአዲስ አበባ ዙሪያ ለኮንዶሚኒየም ግንባታ ሲፈናቀሉ ለጀሞ123 ለአዲስ አበባ ቆጣሪ፣ ለአያት እና የካ አባዶ ብቻ ተደራጅተው ነበር፡፡ ዛሬ አንዳቸውም የሉም ለምን? አድባሯ ነው ይህን ህዝብ የገፋce ወይስ ረቂቅ ሴራ? ለቀጣዩ ተፈናቃዮች ምንም ዋስትና መስጠት አይቻልም፡፡ እንደሌሎች ሀገራት ስትራቴጂ ነድፌን እዚሁ አዲስ አበባ እነቆያለን ሴራ ማንም አይታለልም፡፡ የኦሮሚያ ወጣቶች መጮኸ አግባብ አይደለም የምንለው ምን መሠረት ይዘን ነው?

 በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ማግኘት አለበት ይላል፡፡ 21 ዓመታት ምንም ዓይነት ጥቅም leገኘችም፡፡ ይባስ ብሎ አደገኛ መርዛማ ቆሻሻን ወደ ኦሮሚያ ገበሬዎች በማፍሰስ ጅምላ ፍጅት በማካሄድ ላይ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በመጠየቃቸው ከዛሬ 10 ዓመታት በፊት ጀምሮ የኦሮሚያ ወጣቶች ሲገደሉ ሁሉም ዝምታ ለምን መረጠ? ሕገ መንግሰት የማስከበር ሀላፊነት የሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም?

የኢትዮጵያ ሚዲያ እና ህዝቦች ምን አላችሁ? የኦሮሚያ ወጣቶች መጮኸ አግባብ አይደለም የምንለው ምን መሠረት ይዘን ነው? የኢትዮጵያ ሚዲያ፣ የገዥው ፓርቲ፣ ደጋፊዎች እናሁሉምን ነገር አሸባሪ፣ ጠባብ እና ትምህክት አድርው ማቅረብ የተለመዳ ቢሆንም ከዚህ በታች ያሉት 10 ጥያቄዎች ላይ በትንሹ እንሰብ በሌላ ጊዜ መነጋገር እንድንችል፡፡

1. 5ኛ፣ 8ክፍል ተማሪዎች ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው ሰልፍ በመውጣታቸው በጥይት እሩምታና በድብደባ ገለው የአሸባሪ ሬሳ ነው እንዳይነሳ ተብሎ መንገድ ዳር ማዋል ምን ማለት ነው? እውነት የሚያሰብ አእምሮ፣ ህሊና አለቸውን? ማነው አሸባሪ ሞቾቹ ወይስ ገደዮቹ?

Body of Ebisa Gutu ( name corrected) who was murdered by Agazi at Fincha Sugar factory on Monday December 7, 2015

2. አዲስ አበባ ማስፋት 125 ዓመት የተጀመረው በተለይ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ተፋፍሞ 15 ዓመት ወዲህ ከአዲስ አበባ ዕምብርት እየፈናቀሉ ዛሬ በአዲስ አበባ ዙሪያ የተኮለኮሉ እና የተለያዩ ኦሮሚያ ዞኖች ባሉት ሰዎች ላይ የተፈጸመው ጅምላ ግድያ ተጠያቂው ማነው?

3. እግዚኣብሔር በሰጠቻው መሬታቸው ተገለው አንዱ የሚከብርባት ሀገር እውነት ሀገር ነች? እውነት ኢትዮጵያ ማለት ይህን ዓይነት ባህል አድርጋ የምትኖር/የምትቀጥል/ ነች?

4 4. 5ኛ፣ 8ክፍል የኦሮሞ ተማሪዎች ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው ሰልፍ በመውጣታቸው በጥይት እሩምታ ተደብድበው ሲወድቁ የኢትዮጵያ ሚዲያ፣ የገዥው ፓርቲ አመራሮችና አባሎች፣ ደጋፍዎች እና ሌሎች ብሔርሰቦች የደስታ ፈንጠዝያ ከበሮ መምታት ኢትዮጵያዊያን ወንድማማቾች ነን? የተቀሩት ደግሞ ገለው አስገድለው የአዞ ዕምባ ማንባት ምን ይባላል?

5. በህወሃት ተወናዮች ሀላፊነቱን ከገዥ ፓርቲ አካል ከሆነው ለኦህዲድ/ሙሰኞች/ ብቻ መስጠት ምን ማለት ነው? ማስተር ፕላን ሥር ከልገባችሁ የመኪና እና የባቡር መንገድ አታገኙም ማለት የተፈናቀሉ ሰዎች መች የዚህ ተጠቃሚ ሆነው ያውቀሉ? ልማት ማለት ሰውን፣ ባህሉን፣ቄውን፣ሐይማኖቱን፣ ማንነቱን፣ አንጡራ ሀብቱን ማቃወስ ነውን?

6. ገዳዮች የኦሮሚያ ፖሊሶች/ አገዚ ጦር/ ነው መባባል ምን ማለት ነው፣ ከፌዴራል እስከ ቀበሌ የህወሃት ሲቪል ለባሾች እየመሩ አይደለም? 7. አዲስ አበባ ውስጥ የለውን መሬት ተከፋፍለው የጨረሰው፣ ሀብት ያፈሩበት የህወሃት ባለስልጣኖች አይደሉም?

8. እጅግ ግዙፍ የሪያል ስቴት፣ የአግሮ ኢንዱስትሪ ካምፓኒ፣ የተለያዩ ፋብሪካዎች የነማን ነው?

9. ከቱርክ፣ ኢምሬትስ ቻይናባለሃብቶች የተገነቡ ፋብሪካዎች ለተፈናቃይ ገበሬዎች ምን ፈየዱ?

10. አዲስ አበባ ከተቆረቆረች ጀምሮ በተለይ 15 ዓመት ወዲህ በኢንዳስትሪ መስፋፈት ምክንየት በሚወጡ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ጅምላ ግድያ በኦሮሞ አርሶአደር ላይ ሲፈጸም የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን ዝምታ መረጠ?

እኛ ሠላም ብናጣም ለእናንተ ሠላም ይሁን!

Bareeduu Oromoo

Bakka Jirtuu irraa

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved