Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

የህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አሁን ካለው በላይ እጁን ለማጠንከር እየሰራ ይገኛል።

 

ኦፌኮ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተወሰኗል፣ ኦፒዲኦም በእሬቻ በዓል ጉዳይብሎ "ሃጢያታቸውን" ዘረዝሮ ከአበቃ በሃላ በአማራ ክልል የነበረውን ግን እንዲህ ስል ይደመድማል "…ይሁን እንጂ በአማራ ክልል ለነበረው ግጭት መነሻው የመልካም አሰተዳደርና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች መሆናቸውን ኮሚሸኑ በዋና መንሰኤነት የጠቀሰና የወልቃይት ጉዳይ አባባሽ በመሆኑ የሁለቱ የክልል አመራሮች በህግ ሊጠየቁ እንደማይገባ ኮሚሽነር / አዲሱ /እግዚአብሄር እና  የመንግሰት ተጠሪ ሚንሰቴሩ አቶ አሰመላሽ ወልደ ስላሴ ጉዳዩን አሰመልክቶ ፖርላማ ውሰጥ ለተነሳው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥቷል።"

 ሀገር ውስጥ እየኖሩ ወያኔን በተግባር ከሚጋፈጡ ዜጎች የቀረበ ጥሪና የአላማ ማሳወቂያ

 ህወሀት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ፓርላማ የህውሐት አንዱ ክንፍ በሆነውና "የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን" ተብሎ በተሰየመው ቡድን "የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት" ተብሎ በቀረበው ዘገባ ውስጥ ህዝብን የናቀ፣ የጥቂት አምባገነኖችን ግልፅ ፍላጎትና አላማን ያሳየ፣ ሀገሪቷ በህወሀት አምባገነን አመራር ግትር አቋም ምክንያት ለወደፊት ሊመጣባት ያለውን አስከፊ የሰቆቃና የእልቂት ዘመን ለመገመት የሚያስችል የህወሀት ኢህአዴግ የአቋም መግለጫ የሚመስል ሪፖርት በማየታችን ሀገርቷን ለመታደግ ይቻል ዘንድ ሀሳብ አስተያየታችንን ለሀገርቷ ህዝብ የህወሀት ኢህአዴግን እኩይ አቋም በመረዳት ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በአንድነት በመቆም ህወሀት ኢህአዴግ ያለመውንና ያቀደውን ጥፋት ሳይፈፅም ከስልጣን ወርዶ እንዲጠየቅ ለማድረግ በህብረት ለመስራትና ለኢህአዴግ መውደቅ በተለያዩ መንገዶች የሚታገሉትን በመደገፍ እንድሁም ህዝብ መሀል ሆነው የህዝብ ትግልን የሚያደናቅፉትን ያለምንም ርህራሄ ከህዝብ ለመነጠልና የህወሀት ኢህአዴግን ውድቀት ለማፋጠን ይቻል ዘንድ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበውንና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቀው ሪፖርት ውስጥ

1) የመንግስት ባለስልጣናት "በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የህዝብ አመፅ መነሳቱንና ፈጣን ምላሽ ባለመስጠታቸው ደግሞ መባባሱን" ባመኑበትና መታደስ አለብን ብሎ ጥልቅ ተሀድሶ በገቡበት ወቅት በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ባዶ እጁን በመውጣት በአስተዳደሩ ላይ ያለውን ተቃውሞ በሰላማዊ ሰልፍ የገለፀው ህዝብ በጥፋተኝነት መፈረጁን በመቃወም።

 2) በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ ለመግለፅ ባዶ እጁን ወደ ላይ በማንሳት ለተቃውሞ በወጣው ህዝብ ላይ መሳሪያ ተኩሶ የገደሉ ባለስልጣናትንም ሆነ ታጣቂዎችን እንዲሁም ተኩሰው እንዲገድሉ ያዘዙና ያወጁ ባለስልጣናትን ተጠያቂ በማያደርግ መልኩ መቅረቡን በመቃወም።

3) በከፍተኛ የህዝብ ንቀት ተሞልቶ በመንግስታቸው ቁጥጥር ስር ባለው የብዙሀን መገናኛ ብቅ ብለው ህዝብን በመዝለፍና በመስደብ በተቃውሞ ውስጥ የነበረውን የህዝብ ስሜት በማባባስና ህዝብን በማስቆጣት እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ምላሽ መስጠት እየተቻለ የታጠቁ ኃይሎች እንዲገድሉና የፈለጉትን እርምጃ እንድወስዱ ገደብ የለሌው ስልጣን በመስጠት በንፁሀን ህዝብ ላይ ከፍተኛ እልቂት እንዲፈፀም እና ህዝቡም በንዴት በመነሳሳት ወደ ከፋ የጥፋት እርምጃ እንዲሸጋገር ያደረጉ ከፍተኛ የሀገሪቷ ባለስልጣናትን በማያስጠይቅ ሁኔታ መቅረቡን በመቃወም።

4) በአገሪቷ ህግ መሰረት ተቋቁሞ በስልጣን ላይ ባለው መንግስት የሚደርሰውን ግፍና በደል ለመቃወምና ህዝብም በመንግስትና በመንግስት ባለስልጣናት በሀገር ሀብት ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ጥፋት እንዲያውቅና አውቆም እንዲቃወም ህዝብን ለማደራጀት ለማንቃትና መብቱን እንድያስጠብቅ ለማድረግ በህወሀት መራሹ ዘመነ መንግስት በአገሪቷ ውስጥ ባለው ጠባብና ለአደጋ እንደሚያጋልጥ በግልፅ በሚታወቅ የመደራጀት እድል ተጠቅሞና ህጋዊውን መስፈርት አሟልቶ ለህዝብ በገባው ቃል መሰረት በሰላማዊ መንገድ ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ በአመራር አባላቱ፣ በአባላቱ፣ በደጋፍዎቹና በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ እስራትና ሰቆቃ በመቻልና በመታገስ በሀገርቷ ውስጥ በህዝብ ይሁንታ የሚገነባ መንግስት እንድኖር እየሰሩ ያሉ ጥቂት የህዝብ ድጋፍ ያላቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህወሀት ኢህአዴግ በስልጣን መቆየት ያመች ዘንድ እንዲጠፉ የሀሰት ምስክርነት በመስጠት እንዲጠየቁ በሚል ያቀረበውን የሪፖርት ሀሳብ በመቃወም።

5) "የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ፓርላማ" ለህወሀት ድምፅ ለመስጠትና ለማጨብጨብ ብቻ በተቀመጡ የፖርላማ አባላት ከአላማውና በህግ ከተሰጠው ተልእኮ ውጪ የቀረበውን ሪፖርት ያለ ምንም ተቃውሞ በሙሉ ድምፅ ስያፀድቁ ዛሬም የያዙትን የህዝብ ድምፅ በሙስናና በወንጀል ለተጨማለቁ ጥቂት የህወሀት አምባገነን አመራር አባላት በመስጠት "የወከሉትን ህዝብ" እና እንሰራለታለን የሚሉትን ሀገር የጥቂቶች መንደላቀቂያና ብዙሀኑ ህዝብ የስቃይ ገፈት የሚጨልጡበት እንዲሆን መወሰናቸውን በመቃወም።

6) ከቆሙለት አላማና የሀገርቷ ህግ ከሰጣቸው ህጋዊ ስልጣንና አደራ ውጪ ህዝብ እየተቃወማቸው ያሉትን አምባገነን አመራሮች ስልጣን ለማስጠበቅ የተቀጠሩ በሚያስመስል ሁኔታ ከህዝብ አብራክ የወጡት ነገር ግን ወያኔ የሀገርቷን ዜጎች ለመምታት እንደ መሳሪያ የሚጠቀምባቸው የሀገርቷ የሰራዊት አባላትና አዛዦች የመንግስትን ብልሹ አሰራር ለመቃወም ባዶ እጁን በወጣው ህዝብ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያዘዙ ኃላፊዎችና ትዕዛዙን ተግባራዊ ያደረጉ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ግድያና በወሰዱት እርምጃ በህግ ተጠያቂ እንድሆኑ አለመጠየቁን በመቃወም

1) ለኢትዮጵያ ህዝብ፣

2) ለደህንነት አባላት፣

3) ለፖሊስ ሰራዊት አባላት፣

4) ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣

5)በየትኛውም ደረጃ ላሉ ምሁራን ዜጎች፣

6) በሀገሪቷ ሰርታችሁ ሀብት ላፈራችሁ ባለሀብቶች እንዲሁም።  

7) በወያኔ አላማና ተግባራት ሙሉ በሙሉ ሳያምኑ ነገር ግን በፓርቲ አባልነት ስም ከህዝቡ በተቃራኒ ቆመው ህዝብንና ራሳቸውንም እየዋሹ ላሉት ለኢህአዴግ ፓርቲ አባላት በሙሉ ይህንን ሀገር የማዳን ጥሪ እናቀርባለን።

ህዝብ ያሸንፋል!!!!!

ህዝብን በመግደል፣ በማሰርና በማሰቃየት ሀብቱን መዝረፍ ያብቃ!!!!

ህዝብን ማጋጨት ኪሳራ እንጅ1 ትርፍ የለውም!!!!

የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ለመጣል በእንድነት ይቆማል!!!

ሚያዚያ 15/2009 / አዲስ አበባ

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved