Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

የሴት ልጅ ክብርና ኃይል !!!

Oromoon hundi adda isaa baruu qaba keesummati siirna Gada, siiqee fi qanafa. Oromoon waan in qabu iyuu adunyaf ga'aa !!!

ከዚህ በላይ በዓለም ላይ መሰልጠንስ ከወዴት አለ?!

በቅርቡ በመላው ኦሮምያ በነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ ላይ የወያኔ ጉጀሌ አጋዚዎች በህዝቡ ላይ የጥይት ሩምታ በሚያወርዱበት ወቅት የኦሮሞ እናቶች ምንም እንኳን የሴትን ልጅ ብር የማያውቁ የጫካ ሽፍቶች መሆናቸውን ቢረዱም በኦሮሞ ባህል መሰረት የሴት ልጅ ክብርና ኃይል መገለጫ የሆነውን ሲቄ ይዘው እንደወጡ ይታወሳል ይህም ሆኖ ግን አውሬዎቹ ግዳያቸውን ጥለው ያናወዛቸውን የሰው ልጅ ደም ጠጥቶ የማይረካው መንፈሳቸውን ሊገቱ አልቻሉም ነበር።

ለመሆኑ ይህ #ሲቄ ምንድን ነው?!

ሲቄና ቀነፋ የኦሮሞ ሴቶች ክብር መገለጫዎች !!

ሲቄ:- ማለት ሴት ልጅ ስትዳር ከዚያን ቀን ጀምሮ ባለትዳርና የቤት እመቤት መሆኗን የሚያመለክት በቁመቷ ልክ የተቆረጠ ከእናቷ ለሙሽሪት የሚሰጥ ቀጥ ያለ ዘንግ ነው። #ሲቄ እንደማንኛውም ዘንግ ወይም ዱላ ከብት አይነዱበትም ፤ውሻ አይከላከሉበትም፤ ገበያ ሰርግም ሆነ ለቅሶ #ሲቄ ተይዞ አይኬድም #ሲቄ ለምርኩዝነትም አያገለግልም። ሲቄ ይዘቱ ዘንግ ቢሆንም አገልግሎቱ ግን የተለየ ነው። #ሲቄ እንደ ነዋየ ቅድሳት የሚታይ የክብር እቃ ስለሆነ ሙሽሪት በትራስጌዋ በኩል ታኖረዋለች ሲቄ ለአምላክ ፀሎትና ምስጋና ፤ለእርቅ ለምርቃትና፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሴቶች ግፍና በደል ሲደርስባቸው ለመከላከል ይጠቀሙበታል። ሴቶች ሲቄ ይዘው ይወጣሉ ለምሳሌ : - በእሬቻ ጊዜ ሴቶች ሲቄ ይዘው ሰልፉን ይመራሉ ፤ለአምላክ ምስጋና ያቀርባሉ በተፋፋመ ጦርነት ውስጥ ሴቶች ሲቄ ይዘው እልልል እያሉ ከገቡ ጦርነቱ ወዲያው ይቆማል ማንም ኦሮሞ የፈለገው ዘመዱ ቢሞትበትም ሲቄን ተራምዶ አይዋጋም የኦሮሞ ጦር ለጦርነት ሲሰማራ ሲቄ የያዙ ሴቶች ግራና ቀኝ በመቆም ሲቄያቸውን ከፍ አድርገው በመያዝ ዘማቸን ጦር ከስሩ በማሾለክ #ሳታጣራ_አትወርውር  #በውሸት_አትፎክር  #በድል_ይመልስህ ብለው ይመርቃሉ። ዱሮ የኦሮሞ ጦር ሲቄ በያዙ ሴቶች ሳይመረቅ ወደ ዘመቻ አይሄድም ነበር።ከሄደም እንደ አርበኛ ሳይሆን እንደህገ ወጥ ይታይ ነበር ላስገኘውም ደል ክብር የለውም፤ እርሱም ቢሞት ጉማ የለውም ነበር። ሌላው የሲቄ ተፈላጊነት ሴቶች በባሎቻቸው ወይም በባሎቻቸው ወገኖች የመረርው በደል ደርሶባቸው መኮብለል ከፈለጉ ሲቄያቸውን ይዘው ይወጣሉ ሲቄ ይዛ የምትሂድን ሴት ያየ ማንኛውም ሰው ከፈረስ ወርዶ ሰላምታ ሰጥቶ ከማሳለፍ ሌላ ከጉዞዋ ለመመለስ ወይም ለመከልከል አይሞክርም ከሞከረም ነውር ነገር ስለፈፀመ በገዳ ስርዓት ይደርስበት የነበረው ቅጣትና ማህበራዊ መገለል ከባድ ነበር።

ቀነፋ :- ማለት ከጠንካራ እንጨት ተፈልፍላ በቀጭን የቆዳ ጠፍር በወላድ ሴቶች ግንባር ላይ ከወለዱ ቀን ጀምሮ እስከ 5 ወር ድረስ የምትታሰር የወላድ ሴት የክብር ምልክት ናት። ቀነፋ ያሰሩ ሴቶች በሄዱበት ቦታ ክብርና እንክብካቤ ያገኛሉ ሸክም አይሸከሙም ረጅም መንገድ አይሄዱም፤ በመንገድ ሲሄዱ ያገኛቸው ማንም ሰው ከፈረስ ወይም ከበቅሎው ወርዶ ያስቀምጣቸዋል፤ #ቀነፋ ያሰሩ ሴቶች ከቤትህ ከበሉና ከጠጡ እንደ መልካም ገድ ስለሚታይ ከመንገድ ያገኛቸው ሰው ወደ ቤቱ ወስዶ ምግብና ወተት ይጋብዛቸዋል #ቀነፋ ያደረጉ ሴቶች ታርሰው መጠንከር ስላለባቸው ቀነፋው በክብር እስኪወርድ እስከ አምስት ወር ድረስ የግብረ ስጋ ግንኙነት አያደርጉም #ቀነፋው ከወላዷ ግንባር የሚወርድበት ቀን ራሱን የቻለ ስርዓትና ድግስ አለው።

እናቱን ወይም በእናቱ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶችን የመታ፤ ወይም ሚስቱም ብትሆን በግንባሯ ላይ ቀነፋ ያላትን ሴት የመታ ወይም ልተኛሽ የሚል ወንድ ከተገኘ የሰፈሩ ሴቶች ሲቄያቸውን በመያዝ በነቂስ በመውጣት እየጮሁ ጥፋተኛውን ይከቡታል። ጥፋተኛው ቢያንስ ከሁለት የቅርብ ጓደኞቹ ጋር በመሆን ጥፋተኝነቱን አምኖ ፤ጦሩን አጋድሞ በሴቶቹ እግር ስር ወድቆ ይቅርታ ይጠይቃል፤ ለተበደለችውና ለከበባው ከመጡት ሴቶች ውስጥ ስምንቱን አዲስ ልብስ ያለብሳል ለከበባው ለመጡት ሴቶች ሁሉ የሚበቃ ምርጥ ከብት አርዶ ስጋ ያበላቸዋል። ጥፋተኛው ይሄን ካደረገ ሴቶቹ አጥፊውንና ተጎጂዋን አስታርቀው እየዘፈኑ ወደየቤታቸው ይመለሳሉ። በስርዓቱ አልጠይቅም ወይ ሮጬ አመልጣለሁ ብሎ ከሞከረ  #ሀደ_ጫጩ የምትባል የሴቶች አለቃ #ፋጋ የሚባል ጡሩምባ ትነፋለች። የጥሩምባው ድምፅ እንደተሰማ በአካባቢው የሚገኙ እድሜያቸው 16 -24 ዓመት የሆናቸው #ፎሌ የሚባሉ ወጣቶች ሰውዬው የገባበት ገብተው ፈልገው በማሳደድ ልብሱን እየተረተሩ እንደባንዲራ ዘንጋቸው ላይ አስረው በማውለብለብ እስከ 15 ቀን ድረስ እየሰደቡትና እየገረፉት ገበያ ለገበያ አገር ለአገር በማዞር ይዘፈንበታል። #ፎሌ_አብሳላ የተዘፈነበት ሰው ደግሞ በማንኛውም ጉዳዮች ከሰውነት ክብር ደረጃ ይወጣል፤ በገዳ ስርዓት አይካፈልም በአምልኮ ቦታዎች ላይ አይመርቅም ለዋስትናም አይበቃም።

#የኦሮሞ_ማንነት_ታሪክ !

Kitaaba kana wara itti arganu yoo nu ergitan akka Oromoo heedun bitatu beekisfnaf

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved