Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

ሞቲ ቢያን አፋልጉን Mootii Biyya

  ኦሮምያን በፈረቃ  ሞቲ ቢያ

ለዛሬ ይዤላችሁ የምቀርበው ከሞቲ ብያ ኦሮምያን በፈረቃ ከሚለው መጽኃፋቸው፡፡ በመግቢያው ስር በአስቸጋሪዋ አለም ውስጥ የራስን እድል በራስ የመዋሰን ፈተና ምን ያህል እነደሆነ ያብራሩ ሲሆን፤ በዚሁ ርእስ ስር የሞቱትም ያልሞቱትም የሚታገሉት ህዝብ በሚል ርእስ ከከተቡት ቀንጨብጨብ በማድረግ ነው፡፡ እነደተለመደው /…./ የሚካተተው በእኔው የሚጨመር በመሆኑ የጊዜያችን ሁኔታ ለማገናዘብ የተካተተ መሆኑን ተረዱልኝ፡፡

የሞቱትም፤ ያሉትም፤የሚታገሉት ህዝብ (በሞቲ ብያ)- ከኦሮሚያን በፈረቃ መጽሃፍ የተወሰደ-ለመጨረሻው ፈረቃ የኦሮሞ ልጆች

ሞቲ ጽሁፋቸውን የሚጀምሩት ከከበደ ሚካኤል ታላላቅ ሰዎች በሚል የሼክስፒሩ ማክቤዝ ተስፋ በቆረጠ ጊዜ የተናገረውን በማጣቀስ በገጽ ፸፹ ላይ ባለ አባባል ነው፡፡ እነዲህ ይነበባል::

“… ካሁን ጊዜ ጀምሮ በሰው ልጅ እድል ውስት ቁም ነገር የሆነ ምንም ነገር አይገኝም፡፡ ሑሉም ጨዋታ ነው፡፡ ክብርና ጸጋ ሞቱ፡፡ የህይወት ወይን ጠጅ አለቀ፡፡ በጓዳ የቀረው አተላ ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ህልውናው፤ ለሰብአው ክብሩና ለነጻነቱ ለበርካታ አመታት ታግሏል፡፡ ለተፈጥሮአዊ ነጻነቱ ውድ መስዋእትነት ከፍሏል፡፡ በየዘመናቱ ሃይል ተንኮልና ብልጣብልጥነት ይዘው የመጡ ገዢዎች ተፈራርቀውበታል፡፡ በገዛ ሃገሩ የእስረኝነትና የሁለተኛ ዜግነት ህይወት አሳልፏል፡፡/ባለፉት 25 አመታትም ከምን ጊዞውም በበለጠ ተዘርፈዋል/ የግፎችና መሰሪ ደባዎች ብዛት ማንነቱን ማጥፋት ባይችሉም በነጻነቱና በኦሮሞነት ስሜቱ ላይ ስነ-ልቦናዊና ታሪካዊ ጠባሳ ጥለው ማለፋቸው አያጠያይቅም፡፡

ጨቋኝ ስርአቶች ሁሉ ክፉዎች ናቸው / የወያኔ ስርአትም ጦርነት ባልገጠሙት ሰላማዊ ኦሮሞዎችን በመግደል የክፉነቱን ደረጃ ለየት ደርገዋል፡፡/ አንድ ህዝብ የራሱን ማንነት በጥያቄ ውስጥ እንዲያስገባና ራሱን ዝቅ አድርጎ እንዲመለከት የሚያደርጉ ስርአቶች ግን ከሆሉም እጅግ የከፉ ናቸው፡፡ ይህንን አንድ የታሪክ ጸሃፊ(መሃመድ ሓሰን) እነዲህ ሲሉ ገልታጻውታል፡፡

አንድ ህዝብ ለራሱ ያለውን አክብሮትና በራሱም የመተማመን ስሜት የሚያጠፋ፤ የሰውን የመንፈስና ሰብአዊ ክብር እነዲሁም ኩራት የሚገድል ስርአት አረመኔያዊና ጨቋኝ ነው፡፡ ከሰው ልጅ ሰብአዊ የነጻነት መንፈስ፤ ኩራትና ራስ አክብሮት የበለጠ ነገር የለም፡፡ይህ ሁለንተናዊ እውነታን የሚያንጸባርቅ አባባል ነው፡፡ ስለራሱ ማንነት የተዛባ ስሜትና ንቀትን ጥላቻ እነዲያድርበት የተደረገ ህዝብ ታላቅ ወንጀል ተፈጸመበት ህዝብ ነው፡፡ ከሚጠሉት ሰው መራቅ ይቻላል፡፡ ከራስ መሸሽግን አይቻልም፡፡ /ለዚህ ነው ኢትዮጲያኒስት/ሃብሰሻ ጎረቤቶቻችንን በማንነታችን ላይ አትምጡብን የከዚህ በፊቱ ይበቃናል የምንለው/ የሃበሻ መንግስታት ማነጻጸሪያ በማይገኝለት መልኩ በግለሰብ፤ ቤተሰብና ህብረተሰብ ህልውና ውስጥ ጣልቃ በመግባት በአጠቃላይ ህዝብ ብሄራዊ ስነ ልቦናው ላይ አስከፊ ተግባራትን ፈጽሟል፡፡/እየፈጸሙም ይገኛሉ፡፡/ የስድቦች ሁሉ አናት በሆነው ‹‹እናውቅላችኋለን›› ትምክህተኛ ፖሊሲያቸው ብዙህዝቦችን ረግጠው ገዝተዋል፡፡/ዛሬም ይህ ስድብ በሰፊው ቀጥሎአል፡፡/ ኦሮሞዎች በገዛ ሃገራቸውና ቤታቸው ከሩቅ በመጡ ታጣቂዎች እጅ ተሰቃይተዋል፡፡ ከኑሮዋቸው ተፈናቅለዋል፡፡ /እነዚህ ራሳቸውን አጋዚ በሚል ባእድ ቋንቋ የሚጠሩ ዞምቢ የኦሮሞውን ወጣት ያለጥያቄ ይገድሉታል፡፡ ንብረቱን ይዘርፉታል፡፡ ሚስትና እህቱን አስገድደው ይደፍራሉ፡፡ በገዛ ሃገሩ ባእዳን የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ያውጁበታል፡፡/
ኦሮምያን ወረው የያዙና ራሳቸውን ገዢዎች አድርገው የሰየሙ ተከታታይ የሃበሻ መሪዎች ከወታደራዊ ወረራቸውና ቢሮክራሲያዊ አፈናቸው በእጥፍ ድርብ በሚበልጡ የውስጥ ለውስጥ ብህላዊ ጭቆናዎችንና ግፊቶችን ፈጽሟል፡፡ከኦሮሚያ ሃብቶች ንጥቅ ጎን ብሄራዊ ኩራቱን ነጥቀውታል፡፡/ይህ በአሁኑ የወያኔ መንግስትም በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡/ የንቀት ተራ ስድቦች፤ ታሪክን የማዛባት ዘመቻዎች፤ አዋራጅ የአነጋገር ፈሊጦች የኦሮሚያንና/ የኦሮሞነትን/ ማንነት ለማጥፋት ከብዙ ባታሊዮን ሠራዊት አውዳሚ ውግያዎች ለነሱ ጥፋቶችን ፈጥመዋል፡፡/እየፈጸሙም ይገኛሉ፡፡/ በዚህ የተነሳ በራሳቸው ኦሮሞነት የሚያፍሩ፤ የራሳቸውን ማንነት ለመደበቅ የሚቃጣቸውና የቆሰለ በሽተኛ ስሜት ያላቸው አንዳንድ ወገኞች በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ እስከመታየት ደርሰዋል፡፡ መሃመድ ሃሰን በዚህ ጉዳይ ላይ እነደህ ብለዋል፡፡

በተፈጠረባቸው ርእዮተ-ዓለማዊ ጭቆናዎች ምክንያት በስሜት የቆሰሉ የኦሮሞ ተወላጆች ስርአቱ ያስከተለባቸው የበታችነት ስሜቶችና በቋንቋቸውና ታሪካቸው የማፈር ሁኔታዎች ዛሬም ጭምር የሚታይባቸው ናቸው፡፡ይላሉ፡፡

አለም በስልጣኔ ወደፊት የተራመደችውን እርምጃ በሚፃረር መልኩ ገናና ታሪክና አኩሪ ዝና የነበረው የኦሮሞ ህዝብ የኋሊዮሽ ተመልሷል፡፡ከኋላ በመጡ ሃይሎች የተቀደም አሳዛኝ ህብረተሰብ ሆኗል፡፡ ከዚህ የተነሳ የውጭ ጸሃፊዎችም ሳይቀሩ ‹‹የተረሳው የኣፍሪካ ሕዝብ›› በማለት ጠርተውታል፡፡ በሞት መረሳት ያለ ነገር ነው፡፡ እያሉ መረሳት ግን አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ በመረሳት ውስጥ ቀስ በቀስ ሞት መከተሉ ግድ ነው፡፡/ለለመሞት መታገልና ከመሞት መዳን ግን የባለቤቱን ጽናትና ትግል፡ መስዋእትነት ይጠይቃል፡፡/ በእዳን የፈለጉትና ለዘማነትም የኦሮሞን ጥያቄውን ከውጭው አለም ለመደበቅ አቅም በቻለላቸው መጠን ሲንቀሳቀሱ የኖሩት ለዚህ ነው፡፡/የሰሞኑም የለንደን ጉባኤንና፡ የአትላንታ፡ ኮንፍረንስ የማይዋጥላቸው ዋናውና አንዱ ምክንያታቸው የኦሮም ጉዳይ በኢንተርናሽናል ደረጃ ወጥቶ መታየቱ ያስከተለባቸው ፍርሃት ነው፡፡ ለዘመናት የሸረቡት የክፋት ሴራቸው ግን መበጣጠሱ አይቀርም፡፡/

የኦሮሞ ህዝብ ያለፉት መቶ ሰላሳ አመታት ያሳለፈው በስቃይና በመከራ ብቻ ነው፡፡ የተዘመተበት /በወታደራዊ አገዛዝ ስር የሚገኝ፤ አጋዚ በሚባል ዞምቢ በተገኘበት የሚገደል/ ህዝብ ነው፡፡ ሀገሩ በወረራ የተመሰደበት ህዝብ ነው፡፡ በሃገሩ ከፖለቲካ ስልጣን የተገለለ/ በአናሳ ተጨቁኖ የሚኖር/ ህዝብ ነው፡፡ በተለይ በሃይል ተወሮ እንደተያዘ ወታደር በየቤቱና በየሰፈሩ እያሳደደ የሚገድለው ሑንዋል፡፡

/ኢግዚዮ የሚያሰኝ በደል በቁሳዊ አካሉና በህይወቱ ብቻ ሳይሆን ኦርሞነቱን ማንነቱን እንዲጥል በግልጭ ዘመቻ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ ይህን ማንነቱን ለመጠበቅ የሚደርገው ትግል ግን በአሸናፊነት እነደሚወጣው ጥርጣሬ የለውም፡፡ ኦሮሞነት በቅድሚያ የሚመጣ መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ በሙሉ አስረግጦ እያስረዳ ይገኛል፡፡ በዚህም ጸንቶ ይቀጥላል፡፡/

የመጨረሻው ፈረቃ የኦሮሞ ልጆች፤

እነኚህኞቹ ከበፊተኞቹ የኦሮሞ ልጆች የሚለዩባቸው ባህርያት አሉዋቸው፡፡ ከአባቶቻቸው የወረሱዋቸውን ቁጭት በሆዳቸው ይዘው ከመቀመጥ በአዳባባይ አውጥተው የመዘርገፍ ድፍረቱ አላቸው፡፡ በዘመናዊ ትምህርት የታነጹና ከማንኛውም አቅጣጫ የሚመጣን ፖለቲካዊ ፍልሚያ ለመመከት የሚችል እውቀቱም ሆነ ችሎታ አላቸው፡፡ ውሸታምን ለማጋለጥና ሌባን ሌባ ለመለት የማያወላውል ድፍረት አላቸው፡፡ እውነትን ከተቀበረበት ፈልቅቆ አውጥቶ የማጋለጥ ፓሽን/ደቢ ጃብዱ/ አላቸው፡፡ ለጊዚያዊ መከራና ጉዳት የመምበርከክ ዝንባሌ አይታባቸውም፡፡ ሩህሩህ ቢሆኑም በዚህ ባህሪያቸው እነደ በፊተኞቹ ኦሮሞዎች ሌሎች ሊጠቀሙባቸው የሚያደርጉትን ሙከራ በአጭር የመለየትና የመከላከል ባህርቸው የመጠቀና የረቀቀ ነው፡፡ በኦሮምያ ጉዳይ ላይ መብታቸውን ለማንም ላለማካፈል ቆርጠው የተነሱ መሆናቸውን በየቦታው የሚያንጸባርቁት ሲሆን፤የሌሎችን በነሱ ሃብት የበላይነት በደማቸው ይፋለማሉ፡፡

እነኚህኞቹ በብዛት የነቁና በኦሮሞነታቸው ኩሩ፡ ናቸው፡፡ ለረዢም ዘመናት በአባቶቻቸው ላይ የተፈጸመው የስነልቦና ጫናን ቀንበር በጣጥሰው የወጡና አካፋን አካፋ፤ ባለጌን በግላጭ * የማለት ድፍረቱ አላቸው፡፡ ከመሰረቱም አባቶቻቸው የሞቱበትን የነጻነት ትግል ለመጨረሻው ከግብ ለማድረስ የወሰኑ ሲሆን ይህ መብታቸው ግን ባልተሸራረፈ መልኩ ለመጨበጥ የሚያደርጉት ትግል የመጨረሻው ፈረቃ ላይ ያሉ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡

እነኚህኞቹ ከጉምቱዎቹ የመማር ፍላጎታቸው ከፍተኛ ቢሆንም፤ እንደ ጉምቱዎቹ ለተቃራኒዎቻቸው ይሉኝታ ይዞአቸው የመላላት ስሜት አያሳዩም፡፡ ከሌሎች የኢትዮጲያ ህዝቦች ጋር አብሮ የመኖር ፍላጎታቸው ከዚህ በፊት ከተፈጸመባቸው ጭቆናና ከሃበሻ ገዢዎች መሰሪነት የተነሳ ተሙዋጦ የለቀ በመሆኑ ይህ ምርጫ የራሳቸውን መብትና የሃገር ባለቤትነት በመጀመሪያ ከጨበጡ በኋላ መሆን እነዳለበት ሰይነጋገሩ ያመኑበት ሃቅ ነው፡፡ ለዚህም ኦሮሞነትን በቅድሚያ የሚሉበት ውስጠ ሚስጥራዊ ፍላጎታቸው ነው፡፡ የኔን ለኔ፤ያንተን አልነካብህም፤ የሚል አስተሳሰብ አላቸው፡፡ የኛን ለኛ፤ የናንተን በጋራ ለሚሉወቸው ሰሜንተኞች በሬሳዬ ላይ ብቻ የሚል መልእክት አስተላልፈው እተዋደቁ ይገናሉ፡፡ እስከ መጨረሻው ለመፋለምም ቁርጠኝነቱ አላቸው፡፡

እነኚህኞቹ በሳይንስና ቴክኖሎጂ አለም በተራቀቀበት ዘመን የሚገኙ በመሆናቸው ጠላታቸውን በልጦ ለመገኘት የግድ በቅርበት ከጠላታቸው ኢላማ ስር መቀመጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ይህን የረቀቀ ችሎታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም በተቻላቸው መጠን የኢንተረኔት ኢቲክስን ይከተላሉ፡፡

እነኚህኞቹ ‹‹ገመድ አፍ በተባሉባት›› ሃገር የገዢዎቻቸውን ቋንቋ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ለምርምር፤ ለክርክር፤ የመጠቀም ሃይላቸው በጣም የመጠቀ ነው፡፡ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ በአማርኛ ቋንቋ ስለ ኦሮሞ መብትና የነጻነት ትግል ጽፋው ያስረዱ ናቸው፡፡ እነኚህኞቹ ቋንቋው በመጨቆኛነት የተስፋፋ ቢሆንም፤ ይህን ወደላ ፤በራሱ ዱላ ያሉ ይመስላል፡፡

እነኚህኞቹ የአባቶቻውን ትልቁየእኩልነት መሳሪያ መማር መሆኑንከነ ታደሰ ብሩ ፤ከሜጨና ቱለማ፤ ኦነግ የተግባር አላማዎች ወስደው መደራጀት ቢከለከሉም ልጆቻቸውን ለማስተማርና ለትግል ለማብቃት ቆርጠው የተነሱ ናቸው፡፡ የተማረ ኦሮሞ ራሱን ነጻ ያወጣል የሚል የእምነት ጽናት አላቸው፡፡ ቢቻል ሃገራችን ነጻ ማውጣት አሊያም ልጆቻችን ለትግል አንጸን ማሳደግ ከሚለው የአባቶቻቸው እምነት የተቀረጹ ናቸው፡፡

የመጨረሻ ፈረቃ የኦሮሞ ልጆች

ውድ አንባቢያን የዛሬውን የሞቲ ብያን አፋልጉን መልእክት የራሳቸው ጽሁፍ በማጋራት እቀረብኩ፤ በማንነት ላይ ያተኮረውን ጽሁፋቸውን በሚቀጥለው ሳምነት እቀጥልበታለሁ፡፡

ሞቲ ብያን አፋልጉን፡፡

By Degebassa Feyissa

Link :

http://www.oromoparliamentarians.org/Dhaamsa_bara_haaraa/Dhaamsaa%20guyya%20guyya%20Facebook%20GPO.htm

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved