Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

ግድያን ህጋዊ ያረደገው የወያኔ ሰባዊ መብት ኮሚሽን፣

by Melkamu Temesgen

"የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርትከሰኔ 2008 . እስከ መስከረም 2009 . መጨረሻ ድረስ በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ አማራና በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ 669 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ 1018 ሰዎች ላይ የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ደርሶባቸዋል፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ብሏል። ይህ አኃዝ የታሰሩትን፣ ፣ታፍነው ተወስደው የት እንደደረሱ ያልታወቁትን፣በየእስር ቤቶች ስገረፉ የሞቱትን፣አከለ ጎዶሎ የሆኑትን፣አሁንም በስቃይ ላይ የሚገኙትን አያጠቃልልም።

የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር በሚወስነው አንቀፅ 6 ስር፤በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ውስጥ የተደነገጉት ሰብአዊ መብቶች በማንኛውም ዜጋ፣ በመንግሥት አካላት፣ በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በሌሎች ማኅበራት እንዲሁም በባለሥልጣኖቻቸው መከበራቸውን ማረጋገጥ፣ በመንግሥት የሚወጡ ሕጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ እንዲሁም ትዕዛዞች በሕገ መንግሥቱ ከተረጋገጡ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ጋር የማይቃረኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የሰብአዊ መብት መጣስ ቅሬታዎች ሲቀርቡለት ወይም በራሱ አነሳሽነት ምርመራ ማካሔድ የሚሉት ተጠቅሰዋል።

ይህ ኮሚሽን ግን ቅሬታ ሰምቶ፣ ለተበደሉት ለመከራከር የቆመና ለዚህም ተግባር የተቋቋመ ሳይሆን ተበደልን የሚሉትን ለማደንና በተበዳዮች ላይም የሚደርሰውን የበደል በደል ሸፋፍኖ የትግራይ "ዘመናዊ ንጉሶችን" መንግሥት የሚያሞካሽ የወያኔ ፖለቲካ ሠራተኞች ጥርቅም ነው።

በኢፊዲሪ ሕገ መንግስት ምዕራፍ ሦስት፥ ክፍል አንድ ስር ከተዘረዘሩትሰብአዊ መብቶች ውስጥ የተወሰኑትን ስንመልከት፤ አንቀፅ 14- “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፥ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው አንቀፅ 15- “ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው። ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም አንቀፅ 16- “ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው እንዲሁም አንቀፅ 17- “በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ማንኛውም ሰው ነፃነቱን አያጣም የሚሉትን እናገኛለን።

ከላይ በኮሚሽኑ ሪፖርት እንደተገለፀው፣ በአራት ወራት ውስጥ ብቻ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በሕግ ከተደነገገው አግባብ ውጪ 669 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ 1018 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ብዙ ሺህ ሰዎች ደግሞ በነፃነት የመኖር መብታቸውን ተገፍፈዋል። በዚህ መሰረት፣ በኢፊዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 14 15 16 እና 17 ላይ የተደነገጉት ሰብአዊ መብቶች ተጥሰዋል። 
በኢፊዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 14 15 16 እና 17 ስር የተደነገጉት ሰብዓዊ መብቶች የሚጀምሩትማንኛውም ሰው…” በሚለው ሐረግ ነው። ምክንያቱም፣ የሀገሪቱ ዜጎች በጅምላ አንዱ ወይም ሌላ ተብለው ከመፈረጃቸው በፊት ሰብዓዊ ፍጡራን ናቸው። በመሆኑም፣ ሁሉም የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፥ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አላቸው። ስለዚህ፣ የመብት ጥሰቱን የተፈፀመው በግለሰብ ሆነ በመንግሥት አካላት፣ በፖለቲካ ድርጅት ሆነ በመንግስት ባለሥልጣናት ልዩነት የለውም። በተመሣሣይ፣ ሕይወታቸውን ያጡት፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ ወይም ከቀያቸው የተፈናቀሉት ሰዎች፤ አመፅ ጠሪዎች ሆኑ ፀጥታ አስከባሪዎች፣ አርሶ አደሮች ሆኑ ወታደሮች፣ ፖሊሶች ሆኑ ፖለቲከኞች፣ወዘተ ልዩነት የለውም። ነገር ግን፣ የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበውን ሪፖርት በዝርዝር ከተመለከትነው ከዚህ የሕገ መንግስት መርህ እና በአዋጅ ከተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም። ዛሬ ለእንስሳት ህይወት እንኳን ከፍተኛ ግምት ሰጥተዉ በህይወት እንድኖሩ የመከላከል ተግባሮች እየተደረጉ ባለበት ዘመን ህዝብን ገድሎ ያለመጠየቅ አስነዋሪና አረመኔነት ነው።በመሠረቱ ህዝቡ ስለመብቱ መከበር በለፉት ጊዜያቶች ውስጥ በደረገው ተቃውሞ ወቅት በተቃውሞው በቀጥታ ከተሳተፉትም ውጭ የነበሩ ብዙ ወገኖቻችን ተገድለዋል፣በጥይት ቆስለዋል፣ታስረዋልም።

ለምሳሌ ያህል፣ ቁስለኞችን አከማችሁ ተብለው የተገደሉና የታሰሩ ነበሩ፤ልጆቻቸውን ለመከላከል ሳይሆን ጩሄት ሰምተው የደረሱላቸው እናቶች ጭምር ተረሽነዋል፣በጥይት ተመተው የወደቁት ወንድሞቻቸው ነፍስ ልትወጣ ስትል፣ቀና ልያደርጓቸዉ ጎንበስ ያሉ እህትማማች ህፃናት በአነጣጥሮ ተኳሽ ተቀጭተዋል፣አንድ እናትና አባት በአንድ ቀን ሶስት ልጆቻቸውን አጥተዋል።የወያኔዎች "ሰባአዊ መበት ኮሚሽን" ለዚህ ሁሉ የሰጠው ግምገማ "ተመጣጣኝ ዕርምጃ " መወሰዱን ነው።

ለዚህ ደግሞ በሪፖርቱ ውስጥ የተካተቱትን አንዳንድ .ነገሮች በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ፣ ኮሚሽኑ በሪፖርቱየሁከቱ መንስዔ በአብዛኛው የመልካም አስተዳደር እጦት እና ምጣኔ ሃብታዊ (ኢኮኖሚያዊ) ችግር መሆናቸውን ገልጿል። እነዚህን መንስዔዎች ሕጋዊና ሕገ ወጥ የፖለቲካ ኃይሎች አባብሰዋቸዋል ብሏል። በተለይ በኦሮሚያ የተከሰተውን አስመልክቶ ደግሞበክልሉ የተፈጠረውን አለመረጋጋትና ተቃውሞን የመሩ በመንግስትም በአሸባሪነት የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶች በሕግ መጠየቅ እንዳለባቸው አሳስቧል። በሌላ በኩል ደግሞየተፈጠረውን ሁከት ለመግታት የፀጥታ ኃይሎች በአንዳንድ ስፍራዎች ሕጋዊና ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅመዋል፣ በሌሎች ደግሞ ተቃራኒው እንደተፈፀመ በሪፖርቱ አስረድቷል።

ወያኔ ሰባአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽኔር አዲሱ /እግዛብሔር .."ዜጎች ስለ ሰባአዊ መብቶች ዕውቀት ስላሌላቸው ሀገሪቱ ሞጋችና ስለ መብት ደፍሮ የሚጠይቅ፣ ዜጋ አላፈራችም " በማለት መናገሩን ገልጬ በኤፕርል 9/2017ትንሽ ብዬ ነበር።በትክክልም
የትግራይ ልጆች "እየገደሉና በጥይት እየቆሉ ሞጋችና የመብት ጠያቂ ዜጎችን እየፈለጉ ነው" ማለት ነው።

ከላይ እንደተገለፀው፣ የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደውን እርምጃሕጋዊና ተመጣጣኝ እንደነበረ ገልጿል። በሕግ ከተደነገገው አግባብ ውጪ 669 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተው፣ 1018 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በነፃነት የመኖር መብታቸው ተገፍፎ፣ በዚህ ምክንያት በኢፊዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 14 15 16 እና 17 ላይ የተደነገጉት ሰብአዊ መብቶች ላይ ጥሰት ተፈፅሞ ሳለ፣ በማንኛውም አግባብ ቢሆን የመንግስት እርምጃሕጋዊና ተመጣጣኝ ነበር ሊባል አይችልም።"በነፃነት መኖር "የሚትለዋ ቃል ይህ ህዝብ አልገባውም እንጅ እነሱን የሚመለከት አንቀጽ አለመሆኑን የትግራይ ልጆች ቀደም ስልም በተግባር ገልፀውታል።በአዋሳ 100 ባላይ ወገኖቻችንን ረሽነው፣አልተጠየቁም፣በጋምቤላ 400 አኙዋኮችን ገድለው ዛሬ በመሬታቸው ላይ ጌቶች ሆኔዋል።በኦጋዴን ከሺህዎች ባላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈጽመው ዛሬ በጋዝ ምርት ባለድርሻ ለመሆን ሁሉም ነገር እየተመቻቸላቸው ነው።ስለዚህ እነዚህ
ሰዎች "ለማልማትም ይገድላሉ፣ለመዝረፍም ይረሽናሉ፣" ማለት ነው።

በመቀጠልየሁከቱ መንስዔ በአብዛኛው የመልካም አስተዳደር እጦት እና ምጣኔ ሃብታዊ ችግር ነው የሚለውን እንመልከት። በመሰረቱ፣ የችግሩ ዋና መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት ከሆነ፣ ከሁሉም በፊት ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል የመንግስት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ነው። በሁለተኝነት የተጠቀሰውምጣኔ ሃብታዊ ችግር ደግሞ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 40 41 43 እና 44 ላይ የተደነገጉት ዴሞክራሲያዊ መብቶች አለመከበራቸውን ይጠቁማል። ስለዚህ፣ በተጠቀሱት አከባቢዎች ሁከትና አለመረጋጋት የተከሰተው የመንግስት አካላት ከሕብረተሰቡ ለሚነሳው የእኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ተገቢ የሆነ ምላሽ ባለመስጠታቸው ነው።
"
ፍትሃዊ ተጠቃሚነት" ከነዘህ ሰዎች በፍጹም አይጠበቅም። ቃሉን ወያኔዎች እጅግ በጣም የሚፈሯት ቃል ነች።

ዴሞክራሲ ስነሳ "ጀማሪ ነን፣" ይላሉ። የሳባአዊ መብት ጥሰትን "በህዝቡ ኃላ ቀርነት" ያሳብባሉ።ፍትሃዊ እኩል ተጠ
ቃሚነት አለመኖሩን ለነሱ እራሳቸው እየተገለፀላቸው በመምጣቱ ይህንን ቃል አይወዱትም።ከዛሬ ሃያ አምስት አመት በፍት ምናልባት ከአንድ ክላሽንኮቭ ውጭ ምንም "የኔ ነው"የሚሉት ያልነበረው ጦረኛ ዛሬ ሚስትና ልጆቹ ጭምር ድንቅ የቤት መኪና አላቸው፣ ሁለትና ሶስት ቪላ ቤት ብርቃቸው አይደለም፣ከደደቢትና ከቴምቤን አልማዝና ወርቅ አፍሰው የመጡ ይመስል በለሙሉ ባለሥልጣን እንቬስቴሮች ናቸው፣ባለ ትራክቴሮችና በለ ፋብርካዎቹ "ምርጥ ዘሮች" የነሱ ንግድ "ሁሌ ሲያብብ የሌላው ሁሌም የሚጠወልግ"
"
ትናንሽ እግዛብሔሮች" ሁሌም ለመግደል መብት ያቸላው ናቸው።

ለተጠቀሱት ችግሮች በቅድሚያ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው እነሱ መሆን ሲገባቸው፣ እንደተለመደው ሌላውን ወገን ይወነጅላሉ።በየደረጃው ያሉ የፌደራልና የክልል መንግስት አካላት ናቸው ለደረሰው በደል ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው።። ነገር ግን፣ የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በዋናነት ተጠያቂ ያደረገው የችግሩ መንስዔ የሆነውን የመንግስት አስተዳደራዊ ሥርዓት ሳይሆንችግሩን አባብሰዋል ያላቸውን የፖለቲካ ኃይሎች ነው።


ሥዩም ተሾመ አድማስ ላይ ከወጠዉ መረጃ ጋር ተቀናጅቶና በማሳጠር የቀረበ ነው።

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved