Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጠየቁ

 

"የኦሮሞ ህዝብ በሰላማዊ "አጋንኔት" "አሸባሪ" "ጋኔል" "ጋንግስተር" "ጠንቋይ" ነው።" "ልክ እናስገባቸዋለን"


ታኀሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ የወሰደውን እርምጃ በጽኑ አውግዘዋል። የኦሮሞ ህዝብ በአጋንንት ተመስሎ ተሰድቧልና ተሳዳቢው ባለስልጣን ይቅርታ ይጠይቅ ብለዋል።

መንግስት ለሞቱት ዜጎች ሃላፊነቱን እንዲወስድና ለህዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ አሳስበዋል።በአዲስ አበባ የሚገነቡት ፎቆች የማን ናቸው? ሲሉም ጠይቀዋል።አርጅተናል አልቻልንም ስልጣናችንን እናስረክብ ያሉ አመራሮችም አሉ። ሰፊ ሰአት በሚሸፍነው ስብሰባ የሚከተሉት ሃሳቦች ቀርበዋል።
የመጀመሪያው ባለስልጣን በአሁኑ ሰአት እየተደረገ ያለዉን በሁለት አቅጣጫዎች እመለከተዋለሁ ይላሉ። አንደኛው የኦሮሚያ መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት 3 ሳምንታት ያክል በነበረዉ ግጭት ህዝቡ ላይ ትልቅ ጉዳት አድርሰዋል። መቼስ ጆሮአችን እየሰማና አይናችን እያየ ስለሆነ ሰዎቹ ጉዳት የደረሰባቸው ለህዝብ ጥቅም በመጮሃቸው ነዉ። በአሁኑ ሰአት እየተደረገ ያለዉ ነገር ጥሩ አይደለም። ተማሪዎች የሚያደርጉት ተቃውሞ 1997 ዓም የጀመረና እኛ ዩኒቨርሲቲ ጨርሰን ከወጣን በሁዋላም የቀጠለ ነዉ። የአሁኑን ተቃውሞ የተለዬ የሚያደርገዉ እየተቃወመ ያለዉ ተማሪው ብቻ አለመሆኑ ነው። አሁን እየተቃወመ ያለዉ ህዝቡ ነዉ። ጥያቄው የተማሪዎች ብቻ ሳይሆን የህዝቡ ጥያቄ ሆኗል።
ባለስልጣኑ ንግግራቸውን በመቀጠል መከላከያ ሰራዊት ህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉ በደል በጣም የሚያስቆጣና መንግስት ያለመኖሩን የሚያሳይ ነዉ። ኦህዴድ ኦሮምያን እያስተዳደረ ከሆነ እዉነትም ለሃገሩና ለህዝቡ የሚቆረቆር ከሆነ ህዝቡን እየጨፈጨፈ ያለዉን ሰራዊት ከክልሉ ያስወጣ። ቤቶችን አቃጥለዋል። ነዋሪዎችን ከቤታቸው እየጎተተ በማዉጣት በጥይት ገድለዋቸዋል። በመንግስት ሆስፒታሎች ዉስጥ በመግባት ሰራተኞችን እየደበደቡ ነው። እናት በልጆቿ ፊት በጥይት ተገድላለች፡፡ እንደዚህ አይነቱ ክስተት በሀገራችን የመጀመሪያ ነዉ። ከጣሪያ ላይ ዲሽ በማዉረድ omn ትከታተላላችሁ ተብሎ እየተሰባበረ ነው። ህዝቡ መረጃዎችን ከየት ያግኝ ብለዋል።
ተናጋሪው ንግግራቸውን ይቀጥላሉአምቦ ላይ ፣ወለጋና ሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች ላይ እየተፈጸም ያለዉ omn ስለተላለፈ ነዉ እንጂ አዲስ ነገር አይደለም፤ በአይናችን እያየነዉ ያለነዉ ነዉ። በሚያስተዳድር አካልና በሚተዳደረዉ ህዝብ መካከል ትልቅ ችግር አለ፤ህዝቡ ላይ የደረሰበትን በደል መሪዉ ካላወቀ ህዝቡ የራሱ መንግስት አለዉ ለማለት ከባድ ነዉ። ሌላዉ አካል እንደፈለገ አፉን የሚከፍትበት ከሆነ ምን መንግስት አለ ይባላልህዝቡ ችግር ደርሶብናል በሚልበት ሰአት ጦሩን አስታጥቆ የሚያስጨጭፍ ከሆነ በአሁኑ ሰአት የኦሮምያ መንግስት ለህዝቡ ምን እያደረገ ነዉ ያለዉህዝቡ የሚያደርገው ተቃዉሞ ትክክል ነዉ። የራሱ ሀብት እየተዘረፈበት ነዉ ይህን ጉዳይ ይሄ ትውልድ ካልተቃወመው ለሚመጣዉ ትውልድ ምን ጥሎለት ሊሄዲ ነዉ ይላሉ።


ባለስልጣኑ ንግግራቸውን በመቀጠል ስለራሳችን ክልልና ስለራሳችን ሀብት መከራከርና መቃወም ያለብን ባለቤቶቹ ነን። ዛሬ ችግር ተፈጠረ ብላችሁ ከምትሰበስቡን ችግሩ ከመነሳቱ በፊት ለምን አልሰበሰባችሁንም? ስለማያገባን ነዉየኦህዴድ ትልቁ ችግር የህዝቡን ጥያቄ ያዳምጣል እንጂ መልስ የሚሰጠዉ ሌላ አካል መሆኑ ነው። የእዉቀት ችግር ይሁን፣ የስልጣን ችግር ይሁን አይታወቅም። የሚያስተዳድረዉ አካል ያለበትን ችግር የማይዉቅ ከሆነ ፣ለህዝቡ ጥያቄ መልስ መስጠት እስካልቻለ ድራስ የኦሮሚያ ችግር ነገም ቢሆን የሚቀጥል ይሆናል። በአሁኑ ሰአት ትልቅ ችግር ገጥሞታል። ይህን ችግር መፍታት ካልቻለ ለምን ደክሞኛል ይህቺን አገር ማስተዳደር አልቻልኩም ብሎ ማስተዳደሩን አያቆምም? ” ብለዋል።


ሌላው ባለስልጣን ደግሞ እንዲህ ይላሉ ይሄ መንግስት መጀመሪያ ለማስተር ፕላኑ መልስ ከመስጠቱ በፊት ህይወታቸዉን እያጡ ላሉት ዜጎች መልስ መስጠት አለበት። ስለዚህ በአፋጣኝ የታጠቀዉ ሠራዊት ከአካባቢው ማዉጣት አለበት። ደሙ እየፈሰሰ ላለው ህዝብ መታሰብ አለበት። የኦህዴድ ተወካዮች ዛሬም እንደ ትናንቱ ስህተት እየሰሩ ነዉ ።ትናንትና ዋሽቶ ከነበረ ዛሬም ያንን እየደገመ ነዉ ያለዉ። ህዝባችን እያለቀብን ነዉ ያለዉ። ሌላዉ አካል የሚናገራዉ ሌላ፣ ኦህዴድ የሚናገረዉ ሌላ። ህዝቡን ከማታለል ያለዉን ነገር በግልጽ ለምን ተናግሮ ችግሮችን ለመፍታት አይሞክርም ተናጋሪው ንግግራቸውን በመቀጠልበአሁኑ ሰአት ኦህዴድ ላይ ትልቅ ጥርጣሬ አለኝ። ዛሬ እሱ እያለ ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈፀም ከሆነ ነገ እንዴት አምነነዉ አብረን ልንሰራ እንችላለንአሁን ስህተት ሰርቶ ከሆነ ስህተቱን ተናግሮ ህዝቡን ይቅርታ በመጠየቅ፣ እልቂቱ ቁሞ የታጠቀዉ ሰራዊት ከአካባቢው ወጥቶ ሰላም መዉረድ አለበት። ብለዋል።


ቀጣዩ ተናጋሪ ደግሞ እኔ ብዙ ጥያቄዎች አሉኝ ይላሉ።በአሁኑ ሰአት ኦሮምያን ማነው የሚያስተዳድራትከትላንትና በፊት በሚዲያ እንደሰማነዉ ከሆነ አጋንንቶችን ልክ እናስገባቸዋለን ተብሎአል። እኛ ምን ለማምጣት ነዉ እዚህ የምንሰበሰበዉ? ትልቅ ሀገር ትልቅ ህዝብ አጋንንት ከተባለ የኦህዴድ መኖር ምንዋጋ አለዉበዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ጥያቄ ሲያቀርቡ ለምን የዩኒቨርሲቲዉ ዳይሬክተር መልስ አልሰጣቸውምየሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ጥያቄ ሲያቀርቡ ለምን መልስ አልተሰጣቸውም? ለምን የጥያቄዎቹ መልስ ጥይት ሆነዲሞክራሲ ተብሎ ለምን ህዘቡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ በጥይት ይገደላል ? አንደኛዉን ለምን እንደ ደርግ አቋሙን ግልጽ አድርጎ አይገድልምእኔ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ መናገር የምፈልገዉ፦እዉነትም ለኦሮሞ ህዝብ ቁመናል የምትሉ ከሆነ፣ ህዝቡን እየጨረሰ ያለዉን ጦር በአስቸኳይ ከክልሉ አስወጡ። ህዝባችንን በሌላ አካል አታስጨርሱብን። ቀጣዩ ተናጋሪ ባለስልጣን ደግሞ እንዲህ ይላሉ በአሁኑ ሰአት ገንፍሎ የወጣው የህዝብ ቁጣ እንደሚባለዉ ነው። ይህም የሆነው የመጨርሻ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነዉ። ስራዉ ከመጀመሩ በፊት መንግስት ህዝቡን ማወያየት ነበረበት። ልማት ቢለማ ለህዝቡ ነዉ ፣የሚያለማዉም ህዝቡ ስለሆነ የህዝብ ፍቃደኝነት ያስፈልጋል። ’50 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ ምን ያመጣል? ልክ እናስገባቸዋለን፣ በግድም ቢሆን እናስፈጽመዋለን ብለውናል። ለህዝቡ እቆማለሁ የሚል ሰው እንዴት እንደዚህ ይላል ብሎ የጠየቀ አካል ባለመኖሩ በጣም ነዉ የሚያሳዝነዉ። ሌላዉ አካል እንደዚህ ሊናገረን የቻለዉ ኦህዴድ በከፈተለተ መንገድ በመጠቀሙ ነዉ። የመከላከያ ሠራዊት የአገሩን ዳር ድንበር ያስከብራል እንጂ ህዝቡን አይጨርስም፣ ከየት እንደመጡ አናዉቅም፤ አማርኛ አይችሉ። ኦሮምኛ አይችሉ። ከሌላ ቦታ አማጥቶ ህዝባችንን እያስጨረሰ ስለሆነ ይህ ጉዳይ ቶሎ መቆም ይኖርበታል። ብለዋል።


ሌላው ተናገሪ ደግሞ የመድረኩን አስፈላጊነት በማንሳት ንግግራቸውን ይቀጥላሉ መድረኩ በጣም አስፈላጊ ነዉ፣ ከቤቱ ብዙ ሀሳቦች ተነስተዋል። እኔ በተጨማሪነት የምስጠዉ ሀሳብ፣ ይህ ሁሉ ጥፋት የአመራራችን ዉጤት ነዉ። ህዝባችን የሚያነሳዉ ጥያቄ ትክክለኛና የመብት ጥያቄ ነዉ። አሁን ብዙ ሰዉ ተገድሏል።ህዝባችን ለምን በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊሲ ይጨፈጨፋልበጋምቤላ በተከበረዉ የብሄር ብሄረሰቦች በአል ላይ ተግኝቼ ነበር። በወቅቱ የሱዳን ፕሬዝዳንት ይገኛሉ ተብሎ ነበር። እሳቸዉ የሚመጡት ከጎንደር ተቆርሶ ለሱዳን ለሚሰጠዉ ለም መሬት የስምምነት ፊርማ ለመፈርም ነው ተብሎ
ተነግሮን ነበር። ይህ ጉዳይ በጣም አሳዝኖኛል። ምክንያቱም ስለሚመለከተኝ ነዉ።የክልላችን ጉዳያ ደግሞ በበለጠ ይመለከተኛል። ኦሮሚያ የኛ ናት። እንደ አንድ ኦሮሞ ያገባኛል። በማስተር ፕላኑ ምክንያት የተነሳዉ የህዝብ ተቃዉሞ ከተጀመረ 1 ወር ሊሞላ ነዉ የጭለሞ ጫካ ተቃጥሏል፤ብዙ ጥፋቶችና ዉድመቶች እየተፈጸሙ ነዉ። ይህን መንግስት በአፋጣኝ ሊያቆመዉ ይችል ነበር ሲሉ ገልጸዋል።


ሌላ ተናገሪ ደግሞ ይቀጥላሉ የዚህ ችግር መንስዔ የኦህዴድ የማስፈጸም አቅም ማጣት ነዉ ።ኦህዴድ የህዝባችንን ክብር ለማስጠበቅ አልቻለም እኛም እንደ ኦህዴድ አመራሮች ተዋርደናል። ህዝባችንንም አዋርደናል። በግለሰቦች ደረጃ ህዝባችንን እያሰደብን ነዉ።ወደዳችሁም ጠላችሁም ትፈጽማላችሁ እየተባልን ነዉ። በዲሞክራሲ ትተዳደራለች በሚባል አገር ዉስጥ ግለሰቦች ህዝባችንንና እኛን እያዋረዱን ነዉ። ስለልማት ማዉራት በአሁኑ ሰአት ምንም ዋጋ የለዉም። ማውራት ያለብን ስለሰዉ ልጅ ክብር ነዉ ።በአጋዚና በፌዴራል ፖሊስ ህጻን ሽማግሌ ሳይባል እየተጨፈጨፈ ነዉ፡፡ 50 ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ ስለተዋረደ ነዉ ይህ ሁሉ ችግር ሊመጣ የቻለዉ። በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉት ባለ 12 እና 20 ፎቆች የማን ናቸዉየኦሮሞ ህዝብ በመሬቱና በሃብቱ ላይ የበይ ተመልካች ሆኗል።የእነዚህ ሁሉ ድርጅቶች ዋርዲያ የኦሮሞ ልጅ ነዉ። እሱ ዘበኛ የሚሆነዉ ባለቤቶቹ ከዉጭ እስከሚመጡ ድረስ ነዉ። ሲመጡ ይባረራል።የኦሮሚያን መሬት ዘርፎ የተልፈሰፍሱ የኦህዴድ አመራሮች እያሉ የሚሰድቡን እነሱ እነማን ናቸዉ? ይሉና ይህን ችግር ለማስቆም ከተፈለገ opdo እንደ ድርጅት እራሱን ማስከበር ያኖርበታል፤ በመንግስት ሚዲያዎቶች ህዝባችንን የሰደበዉግለሰብም በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ አለበት ሲሉ አጠቃለዋል።


ቀጣዩ ተናጋሪ ባለስልጣን ደግሞ እንዲህ ይላል እኔ opdo ወይም ኢህአዴግ አገሪቷን ሲቆጣጠር 6 ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ ከዛ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲ ጨርሼ እስክወጣ ድረስ ኦሮሞ በመሆናችን ስንደበደብ፣ ስንታሰር፣ ስንገደል እና ከቤታችን ስንባረር ነበር። ያን ሁሉ ሲያስፈጽም የነበረዉ ኦህዴድ ነዉ። ስለዚህ አሁን የምንወያየዉ ኦህዴድ ምን ለዉጥ ያመጣል ብለን ነዉአቅም ካለዉ አሁኑኑ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ከክልላችን ይዉጣ የማስተር ፕላኑ እቅድ ይሰረዝ። ለሞቱትና ለተጎዱት ቤተሰብ ካሳ ይከፈል
ሌላው የኦህዴድ አባል ደግሞ ይሄ ችግር በማስተር ፕላኑ ሳይሆን በኦሮሚያ መንግስት ላይ ባለ ንቀት የመጣ ነዉ። ኦሮሚያ የሚተዳደረዉ በክልሉ ሳይሆን በፌዴራል መንግስት ነዉ። ለዚህም ነዉ ህጻናትንና ሽማግሌዎችን በአደባባይ የሚጨፈጨፉት።ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ይላል አማራ፣ ኦህዴድም ተንቋል በማለት ተናግረዋል።


ቀጣዩ ተናጋሪ ባለስልጣን ደግሞ አሁን እዚህ ኦህዴድን ወክለን የምንወያየዉ ምን ልናመጣ ነዉ ? 25 አመታት ጉዞዋችን ለህዝባችን ያመጣነዉ ሀዘንና መከራ ብቻ ነዉ። ስለዚህ አሁን የምንሰራዉ ነገር ያስጨንቀኛል። ይህን ሁሉ መከራ 40 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝባችን መሸከም ስላቃተው የመጣ ነው ብለዋል። ሌሎችም በርካታ ተናጋሪዎች ተመሳሳይ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን፣ አንደኛው ባለስልጣን


አሁንም የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን ብለን ሌላ ጥፋት እየፈጸም ነዉ፤ እሱም 50 ብር የቀን አበል ሰዎችን እያታለልን ነው። የሴቶች ሊግ፣ የወጣቶች ሊግ እየተባለ የሚደረገዉ ዉይይት ተጨማሪ ጥፋት ነውና በአስቸኳይ ይቁም ብለዋል።
ሙሉ ትርጉሙ እንደደረሰን በልዩ ዝግጅት እንደምንለቀው ለመግለጽ እንወዳለን።

Source: ESAT

Yaada Guulaala:

Mootuuman wayyane TPLF Oromoo akkasiti tufatee akka binanesati ajeessa jiruu kun Angoo gadii dhisuu qaba.

Hanga Abban biyuuma Oromoo Mirkana'uuti qabsoon iti fufa !!
Sababin isaa Mootumman Gaafi kana gadii kana uumatii gaafacha jiruu deebisuuf amalee feedhu hin qabuu sobee uumata sosoba jira waan ta'ee qabsoo hanga mirgi Oromoo kabajamuti itti fufuu qaba.

1.   Feederala biyyati keessa ajeeja ajeecha Oromoo kan dabarsaa jiran fi yakka ajjechaa warii raawatan hundi seerati dura dhiyachuu qabuu,

2.   Waraan Federla Oromoo ajeesa jiruu haalaa duree tokko malee Oromiyya keessa ba'uu qaba.

3.    Maaster Pilani Oromoo buqisuuf qoopha'ee labsiin haqamuu qaba,

4.   Seeri Caafeen Oromiyya wayee Magaaloota Oromiyya basse gutuun isaa atataman haqamuu qaba;

5.   Bulchitoon Aannalee hundati Feederla fi Agazii fudhatan uumataa reebaa jiran Zoon 18, Bulchisa Magala Gurguduu 309fi Magaloota 564, Ganda 6,712 uumataa Oromoo darara jiran atataman seerati, hadhiyatian,

6.   Lubuu badee fi qamaa hiratan hundafi mootummaan maatii isaanf kassa kafaluu qaba.

7.   Namoon hidhaman tokko utuu hin haafin hikamuu qabuu,

8.   Baratoon Barumsa irra ari'ataman tokko alati utuu hin hafiin nagan mana barumsati deebiyuu qabuu,

9.    Mootumman warana Federla bobosa uumataa qabeenya uumataa samsise seeran hunda isaa kafaluu qaba.

10.               Finfinnen Tessoo Oromiyaa waan tateef kana booda Oromiyya jalati buluu qabdii;

11.               Mootumman Kun hanga gaafii Baratoon Ijoole Oromoo gaafacha jira hunda seeran atatan deebi hin laatin Qabsoo uumataa cimee itti fufu qaba. 

12.               Namoon Oromoo irrati akka barbadan balaqaman akka Abayi Tshaye"ልክ እናስገባቸዋለን" fi Getachew Reda "የኦሮሞ ህዝብ በሰላማዊ "አጋንኔት" "አሸባሪ" "ጋኔል" "ጋንግስተር" "ጠንቋይ" ነው።" warii jeedhan Atataman seeraf dhiyyatan adabamuu qabuu,

22:12:2015

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved