Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዝርዝር ይዘት ይፋ ሆነ. Finfinneen kan Oromiyaati male kan federala miti. Seerii kun ga'ee Oromoof maluu waan ibsuu hin qabu, Finfinnee yoo Oromoof hin deebine Oromiyaan Federala Ethiopia keessa ba'uu qabdi.

   የሚፈናቀሉ የክልሉን አርሶ አደሮች ????????

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2009 (ኤፍ. ቢ. ሲ) የኢፌዲሪ የሚንስትሮች ምክር ቤት ቤት የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክሮበት ህግ ሆኖ እንዲወጣ ለምክር ቤቱ አስተላለፈ።

ምክር ቤቱ ህገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ያስቀመጣቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ህግ መመለስ የሚያስፈልግ በመሆኑም የህገ መንግስቱን መንፈስ ተከትሎ ዝርዝሩ እንዲሰራ ተደርጓል።

ለዚህ እንዲረዳም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካሂዶና በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በዝርዝር ታይቶ በመንግስት ተቋማት ተመክሮበትና ህግ ሆኖ እንዲወጣ ምክር ቤቱ ወስኗል።

በዚህም መሰረት ከአገልግሎት አቅርቦት ልዩ ጥቅም አኳያ፣ ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ልዩ ጥቅሞች አኳያ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሃል የምትገኝ በመሆኗ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ማዕከል በማድረግ የኦሮሚያ ክልል ያለውን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አንቀጾች እንዲቀረጹና እንዲካተቱ ተደርጓል።

ልዩ ጥቅሙ የሚመለከታቸው ጉዳዮች 

ከአገልግሎት አቅርቦት ልዩ ጥቅም አኳ

በአዋጁ መሰረት ልጆቻቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር ለሚፈልጉ የክልሉ ተወላጆች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲያደራጅ ይደረጋል።

አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ በከተማዋ የሚሰጠው የጤና አገልግሎት በከተማዋ ዙሪያ ያሉ የክልሉ ተወላጆችን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል፤ ከዚህ ባለፈም ከአማርኛ በተጓዳኝ አፋን ኦሮሞ በከተማ አስተዳደሩ የስራ ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል።

የኦሮሞ ህዝብን ማንነት የሚያንጸባርቁ አሻራዎች በከተማዋ በቋሚነት እንዲኖሩ በከተማዋ፥ አደባባዮች፣ ጎዳናዎች፣ ሰፈሮች እና የመሳሰሉት ቦታዎች እንደ አስፈላጊነቱ በቀድሞ የኦሮሞ ስማቸው እንዲጠሩ ይደረጋል።

የከተማው አስተዳደርም የኦሮም ህዝብን ባህልና ታሪክ የሚያንፀባርቁ የባህልና ታሪክ ማዕከላት፣ ቲያትር፣ ኪነ ጥበባትና የመዝናኛ ማዕከላት የሚገነቡበትና የሚተዋወቁበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በአዋጁ ተደንግጓል።

የከተማዋ መጠሪያዎች “ፊንፊኔ” እና “አዲስ አበባ” በህግ ፊት እኩል እንደሚያገለግሉም በአዋጁ ሰፍሯል።

ከመሬት አቅርቦት፣ ከውሃ አገልግሎት አቅርቦት፣ ከፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻዎች የማስወገድ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የስራ እድል አቅርቦት፣ በመንግስት ወጪ ከሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አቅርቦት እንዲሁም ከገበያ ማዕከላት አቅርቦትና አርሶ አደሩ ለልማት ተነሺ ሲሆን፥ በቂ ካሳ የማግኘትና በዘላቂነት የማቋቋም አገልግሎትን ያካተተ እንዲሆን ተደርጓል።

የመሬት አቅርቦትን በተመለከተም ተቋማት ለክልሉ የተለያዩ መንግስታዊ ስራዎች እና ህዝባዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ህንጻዎች የሚሰሩበትን መሬት ከሊዝ ነጻ እንዲያገኙ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች፥ ምርቶቻቸውን የሚሸጡባቸውን የገበያ ማዕከላት አቋቁሞ ለአርሶ አደሮች እና ማህበሮቻቸው እንዲያቀርብ ይደረጋል። 

በልማት ተነሺ ለሆኑና በከተማዋ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ከመኖሪያቸው ሲፈናቀሉ በቂ ካሳና በዘላቂነት የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ በዚህ ዙሪያ የተሰሩ የቀደሙ ስራዎች ተፈትሸው ጉድለቶች እንዲስተካከሉና ስራዎችን የሚያስተባብር፣ የሚመራና የሚያስፈጽም ጽህፈት ቤትም ይደራጃል።

የኦሮሚያ ክልል በከተማው ስለሚኖረው የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ልዩ ጥቅም አኳያ

አዋጁ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ያሉ ከተሞችና ቀበሌዎች ደህንነቱ ሳይጠበቅና ቁጥጥር ሳይደረግበት ከተቀመጠው ደረጃ በላይ ወደ ክልሉ በተጣሉ ወይም በፈሰሱ ቆሻሻዎች ምክንያት በሰው፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ አካባቢ ላይ ለደረሰው ጉዳት በህግ አግባብ ከአስተዳደሩ ካሳ የማግኘት መብት እንዳላቸውም አስቀምጧል።

ከዚህ ባለፈም የአዲስ አባበ ከተማ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማከሚያና ማስወገጃ ቦታዎች እንዲሁም መልሶ መጠቀሚያ ስፍራዎች፥ አስተዳደሩና ክልሉ በጋራ ባጠኗቸው ቦታዎችና ሳይንሳዊ መስፈርቶችን ባሟሉ ሁኔታዎች እንዲተዳደሩ እንደሚደረግም በአዋጁ ተጠቅሷል።

ተቋማትን ከማደራጀት አኳያ

በልማት ምክንያት የሚፈናቀሉ የክልሉን አርሶ አደሮች በተመለከተ ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግስት የሆነና ከከተማ አስተዳደሩና ከኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት የተውጣጣ የጋራ ምክር ቤት የሚቋቋምም ይሆናል።

ምክር ቤቱ ከኦሮሚያ ልዩ ጥቅም አንጻር የሚነሱና ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ፥ በአዋጁ የተዘረዘሩ ልዩ ጥቅሞች ተግባራዊ እንዲሆኑ በመከታተልና በመገምገም ድጋፍ ያደርጋል።

አባላቱም ከአስተዳደሩ እና ከክልሉ ምክር ቤት እኩል የሚወከሉ ሆነው፥ አጠቃላይ የምክር ቤቱ አወቃቀር፣ ተግባርና ዝርዝር ጉዳዮች የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ እንደሚወሰን በአዋጁ ተጠቅሷል።

የኦሮሚያ ክልል ልዩ ጥቅምን ለማስጠበቅ የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በማጸደቅ ሂደት ላይ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።

 

1.     http://www.oromoparliamentarians.org/Dhaamsa_bara_haaraa/Finfinneen%20kan%20Oromooti.htm Magaaloon Nannoo Oromoiyaa yoom ilee kan Oromooti.

 1. http://www.oromoparliamentarians.org/Dhaamsa_bara_haaraa/Finfinneen%20Oromiyaa%20jala%20buluu%20qabdi.htm

3.     http://www.oromoparliamentarians.org/Dhaamsa_bara_haaraa/Finfinne%20Wixinee%20labsii%20soba%20hadinu.htm    “Wixinee Labsii Magaalaa Finfinnee Wayyaaneen Qopheeffatte Wal-geenyee Haa Didnu!  

 1. https://www.youtube.com/watch?v=MrWs8yJh5mY
 2. http://www.oromoparliamentarians.org/dhimma_adda_addaa/Godiina%20Adda%20Oromiya%20by%20Dr.%20Getachew%20Jigi.htm
 3. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Amnesty%20Report%20o…
 4.  https://www.amnesty.nl/…/because-i-am-oromo-sweeping-repres…
 5. https://www.amnesty.nl/…/files/public/because_i_am_oromo.pdf
 6. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Prof.%20Asafa%20Jala… 
 7. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Baratoota%20Oromoo%2…
 8. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Protests%20Grow%20ov… 
 9. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Daraartuu%20Abdataa.…
 10. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Sochii%20Oromoo%20ba…
 11. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Baratoota%20Oromoo%2…
 12. http://www.oromoparliamentarians.org/…/17%20Oromo%20Journal…
 13. http://www.oromoparliamentarians.org/…/wallaga%20university…
 14.  http://www.oromoparliamentarians.org/…/Oromo%20Students%20A…
 15.  http://www.oromoparliamentarians.org/…/Finfinnee%20by%20TPL… 
 16. http://www.oromoparliamentarians.org/…/Godina%20Adda%20Orom… 
 17. https://www.oromiamedia.org/2015/09/omn-maaster-pilaanii-finfinnee-irratti-qorannoo-qoratame-ilaachisuun-gaafii-fi-deebii-dr-gizaachoo-teessoo-waliin-taasifame/
 18. www.oromoparliamentarians.org  kan bara 2014 – 2015 ilala

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved